Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ከኢፕድ ጋር በጋራ ያዘጋጁት የፎቶግራፍ አውደርዕይ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተክፈተ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና የ80 አመት ጉዞውን የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተክፈተ።

ቢሮው ላለፉት 80 አመታት የወሳኝ ኩነት ቢሮ በሚል ስያሜ እንደ ሞት፣ ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ የመታወቂያና ሌሎች አገልግሎቶችን ለከተማዋ ነዋሪዎች ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በዚህ አመት አሰራሩን ለማዘመን በአዲስ መልክ "የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ" በሚል ተደራጅቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አንጋፋ ልምዱን በመጠቀም ኤጄንሲው በ80 አመታት ውስጥ ለከተማዋ ነዋሪዎች በምን መልኩ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር የሚያሳዩ ታሪካዊ ፎቶግራፎች የተካተቱበትን የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ አዘጋጅቷል።

የፎቶግራፍ አውደ ርዕዩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የከተማ አስተዳደሩ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተከፍቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በተመሳሳይ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጀውን ጨምሮ ለሌሎች ተቋማትም ተመሳሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ማዘጋጀቱ ይታወቃል።

በሞገስ ተስፋ
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓም
ለመዲናዋ የመንግሥት ሠራተኞች ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ ተደርጓል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በ2015 በጀት ዓመት ለአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን የበጀት ዓመቱን የሥራ እንቅስቃሴ አስመልክተው ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ከሠራተኞች ጥያቄ ሲነሳ እንደነበር ጠቅሰዋል።

የከተማ አስተዳደሩ አመራር ውይይት አድርጎ አቅም በፈቀደ መጠን ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የቤት ኪራይ ድጎማ መደረጉን ገልጸዋል። ይህም ሠራተኞች ያላቸውን የክፍያ ምጣኔ ታሳቢ ያደረገና እስከ አንድ ሺህ 500ብር እንደሆነ ጠቁመው፤ ይህ አሁን ያለውን መሠረታዊ የቤት ኪራይ ክፍያ ጥያቄ የሚፈታ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ችግሩን ማቃለል ያስቻለ ነው ብለዋል።

ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ሠራተኛው የሚያነሳቸው ጥያቄዎች እንዳሉ የገለጹት ኃላፊዋ፤ በሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤት ካፍቴሪያዎች ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን በተወሰነ መጠን መንግሥት መደጎም መቻል እንዳለበት ታምኖ በ2015 መመሪያ ተዘጋጅቶ…………

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106158
በምስክሮች ላይ በማቆያ ውስጥ ይደርስ የነበረውን ችግር ይፈታል የተባለ ስምምነት ተፈረመ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በሰዎች የመነገድ ወንጀል ተይዘው በሚቀርቡ ተጠርጣሪዎች ላይ ለምስክርነት በሚጠሩ ዜጎች በማቆያ ውስጥ ይደርስ የነበረውን ችግር ይፈታል የተባለ ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የፈረሙት ፍትህ ሚኒስቴር፣ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ሰባት አጋር ድርጅቶች ናቸው።

ስምምነቱ መኖሩ በኢትዮጵያ በምስክርነት የሚቀርቡ በሰው መነገድ ወንጀል እና ተጋላጭ ፍልሰተኞችን በምርመራና በፍርድ ሂደት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሻሻል ይረዳል ነው አጋሮቹ ያሉት።

ተጎጂ ምስክሮች ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲመሰክሩ ከለላና ጥበቃ በማድረግ ለመደገፍ የሚያስችል ነው።
የወንጀል ድርጊቱን ለመቀነስ እንደሚያግዝ፣ በምርመራና በፍርድ ሂደት ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲመሰክሩ እንደሚያስችልም ነው የተነገረው።

የፍትህ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋ ምስክሮች ስፍራ በማጣታቸው ከተጠርጣሪዎች ጋር አብረው እንዲቆዩ ይደረግ ስለነበር ለሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ለድለላና ለተለያዩ ነገሮች ይጋለጡ እንደነበር ተናግረዋል።

ስምምነቱ ችግሮቹን በመፍታት አጥፊዎች ለሕግ ቀርበው እንዲቀጡ ለማድረግ ያስችላል ነው ያሉት።
የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ በበኩላቸው፤ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና በሰዎች መነገድ ወንጀል ግዙፍ ኔትወርክ ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስበት መሆኑን አስታውሰዋል።

ትግበራው ወንጀለኞችን ለማስቀጣት፣ ተጎጂዎች ፍትህ እንዲያገኙና እንዲካሱ እንሰሚያደርግና የተጎጂዎችን ስነልቦና ለመጠበቅ እንደሚያግዝም ነው የተናገሩት።

የጂአይዜድ የፕሮግራም አማካሪ ወ/ሮ የማርያም ደመቀ ከአጋሮች ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የተሻለ የምስክሮች ጥበቃ እንዲኖር በሚደረገው ሂደት አጋሮችን በማስተባበርና የትግበራውን ሂደት ውጤታማነት በመከታተል ድጋፍ ይደረጋልም ብለዋል።

ዘላለም ግዛው
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 በጀት አመት ለአባይ ግድብ ግንባታ ከ682 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አሰባስቧል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት ለአባይ ግድብ 682 ሚሊዮን 562 ሺህ በላይ ብር ከማህብረሰቡ ማሰባሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ህዝቡን በማሰተባበር ለግድቡ ግንባታ ገቢ ላሰባሰቡ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል።

በእውቅናና በምስጋና መረሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ፤ በ2015 በጀት ዓመት ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ 682 ሚሊዮን 562 ሺህ 488 ብር ለግድቡ ግንባታ ገቢ ተሰብስቧል ብለዋል።

ከተማ አሰተዳድሩ የግድቡ መሰረተ ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ አራት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር አሰባስቦ ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድረጉን አቶ ምስክር ገልጸዋል።

በታደሰ ብናልፈው
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓም
አቶ ደመቀ መኮንን ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ውይይት አካሄዱ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃያሺ ዮሺማሳ ጋር ዛሬ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡

ከሁለትዮሽ ውይይቱ በኋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደገለጹት፤ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ለማጠናከር፣ እንዲሁም በቀጠናዊና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የሁለቱ አገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ነው ያሉት አቶ ደመቀ፣ የዛሬው ውይይት ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር ይረዳል።

በንግድ፣ በኢንዱስትሪና በኢንቨስትመንት ዙሪያ በጋራ ለመስራትም ተወያይተናል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ለተጀመረውን የሰላም ሂደት ጃፓን ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቷንም አቶ ደመቀ ገልጸዋል።

የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃያሺ ዮሺማሳ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የተጀመረው የሰላም ሂደትን አድንቀው ሂደቱ ውጤት እንዲያፈራ ጃፓን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል።

በሁለትዮሽና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን በመጥቀስ በጋራ እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

በሞገስ ጸጋዬ
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)መልዕክት ‼️
የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን ተቀብዬ አነጋግሪያለው። ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች:: በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋምም አላት።
በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ።

በአማራ ክልል የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብአዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል እስካሁን በክልሉና በፌደራል የፀጥታ ሃይሎች በኩል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል።

ሆኖም በክልሉ ያለው የፀጥታ መደፍረስና ጥቃት በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በአስቸኳይ ለማስቆም የፌደራል መንግስት ከመደበኛው የህግ ማስከበር ስርአት ባሻገር በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በአፋጣኝ እንዲተገበር ነው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጠየቀው።

ክልሉ ወደ ቀደመ መረጋጋቱ እንዲመለስ ዜጎች ሰላማቸው ተመልሶ አርሶአደሩ ወደ እርሻው ክልሉም ወደ ልማት ስራዎች ፊቱን እንዲያዞር ለማድረግ መንግስት ያለበትን ሃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባልም በሚል የፌደራል መንግስትን ጠይቋል።
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል። ጉባኤው ለሶስት ቀናት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል።

አጀንዳዎቹም የባለፈውን ጉባኤ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ፣ የምክር ቤቱን የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም መገምገም፣ የክልሉን አስፈፃሚ መስሪያቤቶች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም፣ የክልሉን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የዕቅድ አፈፃፀምን መርምሮ ማፅደቅ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዕቅድ አፈፃፀምን መርምሮ ማፅደቅ፣ ለአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስልጣን ርክክብ ማካሄድ መሆናቸው ታውቋል።

ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓም