Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 በጀት አመት ለአባይ ግድብ ግንባታ ከ682 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አሰባስቧል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት ለአባይ ግድብ 682 ሚሊዮን 562 ሺህ በላይ ብር ከማህብረሰቡ ማሰባሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ህዝቡን በማሰተባበር ለግድቡ ግንባታ ገቢ ላሰባሰቡ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል።

በእውቅናና በምስጋና መረሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ፤ በ2015 በጀት ዓመት ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ 682 ሚሊዮን 562 ሺህ 488 ብር ለግድቡ ግንባታ ገቢ ተሰብስቧል ብለዋል።

ከተማ አሰተዳድሩ የግድቡ መሰረተ ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ አራት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር አሰባስቦ ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድረጉን አቶ ምስክር ገልጸዋል።

በታደሰ ብናልፈው
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓም
አቶ ደመቀ መኮንን ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ውይይት አካሄዱ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃያሺ ዮሺማሳ ጋር ዛሬ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡

ከሁለትዮሽ ውይይቱ በኋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደገለጹት፤ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ለማጠናከር፣ እንዲሁም በቀጠናዊና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የሁለቱ አገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ነው ያሉት አቶ ደመቀ፣ የዛሬው ውይይት ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር ይረዳል።

በንግድ፣ በኢንዱስትሪና በኢንቨስትመንት ዙሪያ በጋራ ለመስራትም ተወያይተናል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ለተጀመረውን የሰላም ሂደት ጃፓን ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቷንም አቶ ደመቀ ገልጸዋል።

የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃያሺ ዮሺማሳ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የተጀመረው የሰላም ሂደትን አድንቀው ሂደቱ ውጤት እንዲያፈራ ጃፓን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል።

በሁለትዮሽና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን በመጥቀስ በጋራ እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

በሞገስ ጸጋዬ
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)መልዕክት ‼️
የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን ተቀብዬ አነጋግሪያለው። ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች:: በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋምም አላት።
በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ።

በአማራ ክልል የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብአዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል እስካሁን በክልሉና በፌደራል የፀጥታ ሃይሎች በኩል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል።

ሆኖም በክልሉ ያለው የፀጥታ መደፍረስና ጥቃት በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በአስቸኳይ ለማስቆም የፌደራል መንግስት ከመደበኛው የህግ ማስከበር ስርአት ባሻገር በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በአፋጣኝ እንዲተገበር ነው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጠየቀው።

ክልሉ ወደ ቀደመ መረጋጋቱ እንዲመለስ ዜጎች ሰላማቸው ተመልሶ አርሶአደሩ ወደ እርሻው ክልሉም ወደ ልማት ስራዎች ፊቱን እንዲያዞር ለማድረግ መንግስት ያለበትን ሃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባልም በሚል የፌደራል መንግስትን ጠይቋል።
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል። ጉባኤው ለሶስት ቀናት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል።

አጀንዳዎቹም የባለፈውን ጉባኤ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ፣ የምክር ቤቱን የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም መገምገም፣ የክልሉን አስፈፃሚ መስሪያቤቶች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም፣ የክልሉን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የዕቅድ አፈፃፀምን መርምሮ ማፅደቅ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዕቅድ አፈፃፀምን መርምሮ ማፅደቅ፣ ለአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስልጣን ርክክብ ማካሄድ መሆናቸው ታውቋል።

ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓም
የኦሮሚያ ክልል ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት 166 ሚልዮን ብር ማግኘቱን ገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ አገልግሎት በ2015 በጀት ዓመት ከ166 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የክልሉ ንግድ ቢሮ ገለፀ።

የቢሮው የእቅድና በጀት ዳይክተር አቶ ክፍሌ ታደለ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ክልሉ ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ከ166 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ ክልሉ በበጀት ዓመቱ ከግማሽ ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች በሰጠው አገልግሎት ነው ገቢውን ማስገባት የቻለው።

በዳግማዊት ግርማ (ከሚዛን አማን)
ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

ዛሬ ማለዳ በቀን 67 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችሉ፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የአዲስአበባ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 1.8 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የንጹህ መጠጥ ውሀ፣ የፍሳሽ ማጣሪያ እና የውሀ ላብራቶሪ ፕሮጀክቶችን መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል፡፡

በቀን 67 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችሉ 25 የውሀ ጉድጓዶች ቁፋሮ እና የውሀ መሰረተ ልማት ግንባታን በማጠናቀቅ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች አሟልተን ስራ ያስጀመርናቸው ፕሮጀክቶች የከተማዋን ዕለታዊ ውሃ የማምረት አቅም ወደ 792 ሺህ ሜትር ኪዩብ ከፍ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

ለሕብረተሰቡ የሚሰራጨውን ውሀ ደህንነት የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ዘመናዊ የውሃ እና ፍሳሽ ላብራቶሪ ተቋቁሞ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን አሟልተን ስራ ያስጀመርናቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል የፍሳሽ ማጣሪያ እና 40 ኪሎ ሜትር የተለያዩ መጠን ያላቸው የውሀ ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታ ስራ እንዲጀምር አድርገናል፡፡

እነዚህ ፕሮጀክቶች በ2015 በጀት ዓመት ተጀምረው የተጠናቀቁ ናችው። ከተማችን ፕሮጀክት ጀምራ በተያዘለት ጊዜና በጀት የማጠናቀቅ ባሕሏን ጠብቃ የነዋሪውን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥና የከተማችንን ገጽታ በመገንባት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን ከፍ ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን።
የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!

ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓም