Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጋር ተወያዩ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አኔት ዌበርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ተወያይተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ የሰላም ሂደት፣ የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት ትብብር እንዲሁም የጋራ ጥቅሞቻቸው በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

አቶ ደመቀ ለልዩ ልዑኳ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላምን ለማጽናት እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶች፣ የሽግግር ፍትሕ ሂደትና የመልሶ ማቋቋም እና መልሶ ግንባታ ስራዎች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።

ከዚህም አኳያ መንግስት የሰላም ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆን አሁንም ቁርጠኛ መሆኑን ጠቅሰው የአውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ አጋሮች የመንግስትን አጠቃላይ ጥረቶች እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

ከሱዳን ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ እንደ ጎረቤት አገር የሱዳን ጉዳይ ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኘው በድርድር እና ውይይት ብቻ መሆኑን በጽኑ ታምናለች ነው ያሉት አቶ ደመቀ።

የሰላም ሂደቱ በባለቤትነት መመራት ያለበት በሱዳናውያን እንደሆነ ገልጸው የሰላም ጥረቶች በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ ውስጥ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) አማራጭ ውስጥ ተፈጻሚ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት ከሱዳን ጦርነቱን ሸሽተው የመጡ 70 ሺህ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች መሆኑን ጠቁመው ለሰብአዊ እርዳታ ጥረቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

አቶ ደመቀ አክለውም በኢትዮጵያ ሰላም እንዲጸና እንዲሁም በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ገንቢ ሚና ለመወጣት አሁንም ቁርጠኛ መሆኗን አመልክተዋል።

ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ።
ዑጋንዳ ከኢትዮጵያ የስንዴ ልማት ተሞክሮ በመውሰድ ተግባራዊ እንደምታደርግ ተገለጸ
**************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ያስመዘገበችውን ስኬት እና በግብርናው ዘርፍ ያሳየችውን መሻሻል እንደ ተሞክሮ በመውሰድ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በዑጋንዳ የግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና ዓሣ ሀብት ኮሚሽነር አስታወቁ።

በዑጋንዳ የግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና ዓሣ ሀብት ኮሚሽነር አና ሮዝ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት ስንዴ ከውጭ ስታስገባ የነበረችው ኢትዮጵያ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የስንዴ ምርት ፍጆታዋን በሀገር ውስጥ ከመሸፈን አልፋ ለውጭ ገበያ ማቅረቧ የሚደነቅ ነው።

ዑጋንዳ ይህንና ሌሎች ሀገሪቷ በግብርናው ዘርፍ ያመጣቻቸውን ለውጦች ተግባራዊ ማድረግ ትፈልጋለች።

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በማደግ ላይ ላሉ የዓለም ሀገራትም ምርጥ ተሞክሮ ነው ያሉት ኮሚሽነር አና፤ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ያስመዘገበችውን ስኬት እና የግብርናውን ዘርፍ ለማሻሻል ያከናወነችውን ተግባራት........

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106335
በባህር ዳር ከተማ በ180 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው አረንጓዴ ፓርክ በነሐሴ ወር ይመረቃል
**************
(ኢ ፕ ድ)
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን አረንጓዴ ፓርክ በነሐሴ አጋማሽ እንደሚያስመርቅ ተገለጸ።

የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በነሐሴ ወር አጋማሽ የሚመረቀው አረንጓዴ ፓርክ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ እና ስድስት ሄክታር በሚሆን መሬት ላይ ያረፈ ነው።

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፓርኩን የገነባው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልምድ በመቅሰም ነው ያሉት ዶክተር ድረስ፤ የሚመረቀው ፓርክ የከተማዋ ትልቁ የአረንጓዴ ፓርክ ይሆናል ብለዋል። በፓርኩ ውስጥም የተለያየ ዝርያ ያላቸው ዛፎች፣ የቴአትር……………

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106314
በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚፈልቁ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢንዱስትሪው ለማሸጋገር እየተሠራ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚፈልቁ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢንዱስትሪው ለማሸጋገር እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ የቴክኒክና ትምህርት ሥልጠና ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ የቴክኒክና ትምህርት ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ ለኢትዮጵያ ፐሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ቢሮው ከተልዕኮው አንጻር አንዱ የቴክኖሎጂ ውድድር በማዘጋጀት ቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ ነው።

ያለው ነባራዊ ሁኔታ አዳዲስ ቴክኖሎጂ ከመፍጠር ባሻገር የተቀዱ ቴክኖሎጂዎችን ማበረታታትና ወደ ሥራ ማስገባት አስፈላጊ ነው። የአደጉ ሀገራት ፈጥረዋቸው ያለፏቸውን ቴክኖሎጂዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲቀዱ በማድረግ ለኢንዱስትሪዎች እንዲያሸጋግሩ ማድረግ ይጠበቃል።

እንደ ወይዘሮ ሀቢባ ገለጻ፤ ኢንዱስትሪዎች አንዱን ማሽን ከመቶ በላይ በማባዛት ለገበያ በማቅረብ የአምራቹን ዘርፍ ውጤታማ ማድረግ ያስፈልጋል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ላይ ውስንነት አለ። እስካሁን ከፈለቁ ቴክኖሎጂዎች 56 በመቶ ገደማ የሚሆኑት ብቻ……………

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106334
መንግሥት ለነዳጅ ድጎማ በየወሩ ያወጣ የነበረውን አስር ቢሊዮን ብር ዕዳ ማዳን ተችሏል
*************
(ኢ ፕ ድ)
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መንግሥት በየወሩ ያወጣ የነበረውን የአስር ቢሊዮን ብር የነዳጅ ድጎማ ዕዳ ማስቀረት መቻሉን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ገለፀ።

በበጀት ዓመቱ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የ15 ነጥብ 15 ቢሊዮን ብር ድጎማ መደረጉም ተመላክቷል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሰሀረላ አብዱላሂ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ መንግሥት ላይ ያለውን የዕዳ ጫና ለማቃለል እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደጎም በተጀመረው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ መንግሥት ከዓለም የነዳጅ ሽያጭ ዋጋ ጋር ለማስተካከል በየወሩ ያወጣ የነበረውን የአስር ቢሊዮን ብር ዕዳ ማስቀረት ችሏል።

መንግሥት ድጎማው በተጀመረበት ጊዜ የነበረበትንና በየወሩ ይከፍል የነበረውን የ15 ቢሊዮን ብር ዕዳ ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ መቻሉን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወርሀዊ ዕዳ ነፃ ሆኖ ሁለት ቢሊዮን ብር ወደ ካዝናው ማስገባት ችሏል ብለዋል።

አነስተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የ15 ነጥብ 15 ቢሊዮን ብር ድጎማ ስለ መደረጉም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከድጎማው በፊት ከጎረቤት ሀገራት የነዳጅ መሸጫ ዋጋ 80 በመቶ ያህል ልዩነት የነበረባት ሲሆን፤ በተሠራው ሥራም………….

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106350
ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ የቤተሰብ አባላት የሶላር ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆነዋል
*************
(ኢ ፕ ድ)
በገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማት ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ የቤተሰብ አባላት የሶላር ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆናቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በ2015 በጀት ዓመት በገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማት 175 ሺህ በቤተሰብ ደረጃ አገልግሎት የሚሰጡ ሶላር ቴክኖሎጂዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ስርጭቱን ለመከታተል ታቅዶ 182 ሺህ 448 ለማሳካት ተችሏል።

በስርጭቱም ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ አባወራና እማወራዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማትን በማስፋት የዜጎችን የኢነርጂ ፍላጎት የተሟላ እንዲሆን በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል ያሉት………..

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106343
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን አንድ ሺህ 500 ተማሪዎችን በዛሬው እለት እያስመረቀ ነው።

ተመራቂ ተማሪዎቹ፤ በአውሮፕላን አብራሪነትና ጥገና፣ በበረራ መስተንግዶ፣ በሆቴል ሙያ እና በደንበኛ አገልግሎት ባለሙያነት ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዛሬው እለት ተመርቀዋል።

ከዚህ በፊት የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲው ይህንን ያህል ቁጥር ተማሪዎችን አስመርቆ እንደማያውቅ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ካሴ ይማም እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በሳሙኤል ወንደሰን
ሐምሌ 29 2015 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 በጀት አመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ በአዳማ ከተማ እያካሄደ ነው።
በግምገማ መድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጀት አመቱ በተሟላ ደረጃ ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

አመራሩ ተደራራቢ ሃላፊነትን በመወጣት ረገድ ትልቅ ተሳትፎ ማድረጉን አስታውቀዋል።

ከንቲባዋ፣ የበጀት አመቱ የሃሳብና የተግባር አንድነት የታየበት፣ መገፋፋቶች የቀነሱበትና ወንድማማችነትና እህትማማችነት ጐልቶ የታየበት አመት እንደነበር ገልጸዋል።

የአመራር ውህደትና አንድነት፣ ደጋፍና ክትትል ለህዝብ ጥቅም በትኩረት መስራት የስኬቱ ምንጭ ነበር ያሉት ከንቲባዋ፣ በበጀት አመቱ በዋናና መሰረታዊ ፍላጐት ላይ ያተኮሩ ከ12ሺ በላይ ፕሮጀክቶችን መፈጸም እንደተቻለ ተናግረዋል።

በአዲሱ ገረመው (አዳማ)
ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓም
በአማራ ክልል የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በመፍታት ሰላም ለማስፈን ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልገሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶክተር) በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በመፍታት ሰላምን ለማስፈን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

የክልሉን አንዳንድ አካባቢዎች በመደበኛው የህግ ስርዓት መምራት ባለመቻሉ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ከትናንት ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን አስታውሰዋል።

በአዋጁ መሰረትም የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ተቋቁሞ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።

እዙ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

በዘላለም ግዛው
ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓም