Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚፈልቁ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢንዱስትሪው ለማሸጋገር እየተሠራ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚፈልቁ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢንዱስትሪው ለማሸጋገር እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ የቴክኒክና ትምህርት ሥልጠና ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ የቴክኒክና ትምህርት ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ ለኢትዮጵያ ፐሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ቢሮው ከተልዕኮው አንጻር አንዱ የቴክኖሎጂ ውድድር በማዘጋጀት ቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ ነው።

ያለው ነባራዊ ሁኔታ አዳዲስ ቴክኖሎጂ ከመፍጠር ባሻገር የተቀዱ ቴክኖሎጂዎችን ማበረታታትና ወደ ሥራ ማስገባት አስፈላጊ ነው። የአደጉ ሀገራት ፈጥረዋቸው ያለፏቸውን ቴክኖሎጂዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲቀዱ በማድረግ ለኢንዱስትሪዎች እንዲያሸጋግሩ ማድረግ ይጠበቃል።

እንደ ወይዘሮ ሀቢባ ገለጻ፤ ኢንዱስትሪዎች አንዱን ማሽን ከመቶ በላይ በማባዛት ለገበያ በማቅረብ የአምራቹን ዘርፍ ውጤታማ ማድረግ ያስፈልጋል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ላይ ውስንነት አለ። እስካሁን ከፈለቁ ቴክኖሎጂዎች 56 በመቶ ገደማ የሚሆኑት ብቻ……………

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106334
መንግሥት ለነዳጅ ድጎማ በየወሩ ያወጣ የነበረውን አስር ቢሊዮን ብር ዕዳ ማዳን ተችሏል
*************
(ኢ ፕ ድ)
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መንግሥት በየወሩ ያወጣ የነበረውን የአስር ቢሊዮን ብር የነዳጅ ድጎማ ዕዳ ማስቀረት መቻሉን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ገለፀ።

በበጀት ዓመቱ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የ15 ነጥብ 15 ቢሊዮን ብር ድጎማ መደረጉም ተመላክቷል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሰሀረላ አብዱላሂ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ መንግሥት ላይ ያለውን የዕዳ ጫና ለማቃለል እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደጎም በተጀመረው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ መንግሥት ከዓለም የነዳጅ ሽያጭ ዋጋ ጋር ለማስተካከል በየወሩ ያወጣ የነበረውን የአስር ቢሊዮን ብር ዕዳ ማስቀረት ችሏል።

መንግሥት ድጎማው በተጀመረበት ጊዜ የነበረበትንና በየወሩ ይከፍል የነበረውን የ15 ቢሊዮን ብር ዕዳ ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ መቻሉን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወርሀዊ ዕዳ ነፃ ሆኖ ሁለት ቢሊዮን ብር ወደ ካዝናው ማስገባት ችሏል ብለዋል።

አነስተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የ15 ነጥብ 15 ቢሊዮን ብር ድጎማ ስለ መደረጉም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከድጎማው በፊት ከጎረቤት ሀገራት የነዳጅ መሸጫ ዋጋ 80 በመቶ ያህል ልዩነት የነበረባት ሲሆን፤ በተሠራው ሥራም………….

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106350
ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ የቤተሰብ አባላት የሶላር ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆነዋል
*************
(ኢ ፕ ድ)
በገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማት ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ የቤተሰብ አባላት የሶላር ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆናቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በ2015 በጀት ዓመት በገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማት 175 ሺህ በቤተሰብ ደረጃ አገልግሎት የሚሰጡ ሶላር ቴክኖሎጂዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ስርጭቱን ለመከታተል ታቅዶ 182 ሺህ 448 ለማሳካት ተችሏል።

በስርጭቱም ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ አባወራና እማወራዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማትን በማስፋት የዜጎችን የኢነርጂ ፍላጎት የተሟላ እንዲሆን በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል ያሉት………..

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106343
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን አንድ ሺህ 500 ተማሪዎችን በዛሬው እለት እያስመረቀ ነው።

ተመራቂ ተማሪዎቹ፤ በአውሮፕላን አብራሪነትና ጥገና፣ በበረራ መስተንግዶ፣ በሆቴል ሙያ እና በደንበኛ አገልግሎት ባለሙያነት ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዛሬው እለት ተመርቀዋል።

ከዚህ በፊት የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲው ይህንን ያህል ቁጥር ተማሪዎችን አስመርቆ እንደማያውቅ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ካሴ ይማም እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በሳሙኤል ወንደሰን
ሐምሌ 29 2015 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 በጀት አመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ በአዳማ ከተማ እያካሄደ ነው።
በግምገማ መድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጀት አመቱ በተሟላ ደረጃ ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

አመራሩ ተደራራቢ ሃላፊነትን በመወጣት ረገድ ትልቅ ተሳትፎ ማድረጉን አስታውቀዋል።

ከንቲባዋ፣ የበጀት አመቱ የሃሳብና የተግባር አንድነት የታየበት፣ መገፋፋቶች የቀነሱበትና ወንድማማችነትና እህትማማችነት ጐልቶ የታየበት አመት እንደነበር ገልጸዋል።

የአመራር ውህደትና አንድነት፣ ደጋፍና ክትትል ለህዝብ ጥቅም በትኩረት መስራት የስኬቱ ምንጭ ነበር ያሉት ከንቲባዋ፣ በበጀት አመቱ በዋናና መሰረታዊ ፍላጐት ላይ ያተኮሩ ከ12ሺ በላይ ፕሮጀክቶችን መፈጸም እንደተቻለ ተናግረዋል።

በአዲሱ ገረመው (አዳማ)
ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓም
በአማራ ክልል የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በመፍታት ሰላም ለማስፈን ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልገሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶክተር) በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በመፍታት ሰላምን ለማስፈን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

የክልሉን አንዳንድ አካባቢዎች በመደበኛው የህግ ስርዓት መምራት ባለመቻሉ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ከትናንት ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን አስታውሰዋል።

በአዋጁ መሰረትም የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ተቋቁሞ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።

እዙ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

በዘላለም ግዛው
ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓም
የርዕደ መሬት አደጋን ለመቋቋም እንደሀገር ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባል
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
በስምጥ ሸለቆ የሚከሰቱ የርዕደ መሬት አደጋዎችን ለመቋቋም እንደሀገር የቅድመ ጥንቃቄ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ገለጹ።

ፕሮፌሰር አታላይ አየለ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያና በአካባቢዋ በሚገኙ ሀገራት ከስምጥ ሸለቆ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የርዕደ መሬት ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106405
በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ከ500 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በ2015 በጀት ዓመት በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ከ500 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስቴር የበጀት አመቱን ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ እቅድ ግምገማ ባካሄደበት ወቅት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ እንደገለጹት፤ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ለበርካቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106400
የሰው ሀብት ልማት ለአየር መንገዱ የዕድገት ፍኖተ ካርታ ቁልፍ ምሰሶ ነው
*********
(ኢ.ፕ.ድ)

የሰው ሀብት ልማት ለአየር መንገዱ የዕድገት ስትራቴጂክ ፍኖተ ካርታ አንዱ ቁልፍ ምሰሶ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናገሩ።

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን አንድ ሺህ 551 ተማሪዎችን ትናንትና አስመርቋል።

በምርቃቱ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ የሰው ሀብት ልማት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የእድገት ስትራቴጂክ ፍኖተ ካርታ ቁልፍ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106412
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ 583 ዶክተሮችን አስመረቀ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በቅድም ምረቃናና ድህረ ምረቃ 583 ዶክተሮችን ዛሬ አስመረቀ።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አስፋ፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ድጉማና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በ"ሰብስፔሻሊቲ፣ በነርሲንግ ስፔሻሊቲ፣ በፐብሊክ ሄልዝ፣ በሌሎች ዘርፎች አስመርቋል።

የኮሌጁ ፕሮቮስት ዶክተር ሲሳይ ሰርጉ እንዳሉት፤ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለመስጠት፣ ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት ከመማር ማስተማሩ ጐን ለጐን ችግር ፈቺ ምርምሮችን በመስራት የህክምና አሰጣጡ የዘመነ እንዲሆንና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን እየሰራ ነው።

ኮሌጁ በ35 የስልጠና መርሃግብሮች የህክምና ባለሙያዎችን በማሰልጠን የህክምናው ዘርፍ እንዲዘምን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ሲሳይ፣ ለአገሪቱ የጤና ስርአት መሻሻል የበኩሉን ሚና እየተወጣ ነው ብለዋል።

ከሚሰጣቸው የስልጠና መርሃግብሮች ሰባቱ በዚህ አመት የተጀመሩ መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይነትም ምርምሮችን በመስራት የጤና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል።

ምሩቃን በቀጣይ በኮሌጁ የቀሰሙትን እውቀት በተግባር በመግለጽ ሙያዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ዶክተር ሲሳይ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሌጁ ያስመረቃቸው በህክምና 395፣ በህብረተሰብ ጤና፣ 78፣ በነርስ 110 በድምሩ 583 ሲሆኑ 185ቱ ሴቶች ናቸው።

ከምሩቃኑ መካክል በተሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና 151ዱ በሙሉ ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ ማለፋቸው ተገልጿል።

በሞገስ ተስፋ
ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም
ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ የተሳታፊ ልየታ ሥራ በአስር ቀናት ውስጥ ይጀምራል
*************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ የሚደረገው የተሳታፊ ልየታ ሥራ በአስር ቀናት ውስጥ እንደሚጀምር አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሲዳማ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ምዕራብ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ የተሳታፊዎች ልየታ ሥራ በአብዛኛው ተጠናቋል።
በቤኒሻንጉልና በጋምቤላ ክልሎች ወደ ተሳታፊዎች ልየታ …

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106452