Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ሜታ ኩባንያ በሰው ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ያካበተውን ልምድ በዘርፉ የላቀ እውቀት ያላቸውን የመስኩ ምሁራንን በመላክ ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው ኩባንያው በፌስቡክ፣ በዋትስአፕና በኢንስታግራም የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ያካበተውን ተሞክሮ ለኢንስቲትዩቱ ለማጋራት እና አብሮ ለመስራት የሚያስችል ነው ተብሏል።
የአዲስ አበባ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ ሎት ሦሰት አፈፃፀም 47 ከመቶ ደረሰ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነው የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ ፕሮጀክት የግንባታ ስራ ከተጀመረበት ህዳር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ግንባታቻው እየተፋጠነ ሲሆን አሁን ላይ ከ6 ብሎኮች መካከል የአራት ብሎኮች መዋቅር ስራ ተጠናቆ ጣሪያ የማልበስ ስራና ሌሎች ተግባራት በተለያየ ምዕራፍ ተከፋፍሎ እየተሰራ ይገኛል።

የፕሮጀት ጠቀሜታው እጅግ ጉልህ የሆነው ይህ የማኑፋክቸሪንግ መንደር ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት፣ የስራ ዕድልን ለማስፋትና የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማሳለጥ ሚናው የጎላ ነው።

ግንባታው እየተካሄደ በሚገኝበት አቃቂ ቃሊቲ የምድብ ሶስት (lot3) ግንባታ ፕሮጀክት የግንባታ ቦታውን ለስራ ምቹ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ስራዎች ተከናውነው፣ አሁን ላይ ከ6 ብሎኮች መካከል የአራት ብሎኮች፣ መዋቅር ስራ ተጠናቆ ጣሪያ የማልበስ ስራ እተሰራ ሲሆን ፣ በአፈፃፀም ደረጃ አሁን ላይ 47 ከመቶ በላይ መድረሱን እና የቀሪ ሁለት ብሎኮች መዋቅር ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።

ከምድብ ሶስት ግንባታ ስራ በተጨማሪ በምድብ አንድ ተከፍሎ እየተሰራ የሚገኘው ሌላኛው የግንባታ አካል በተመሳሳይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባ መሆኑን የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።

ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ .ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት ስለመፍጠር ዛሬ ከሰዓት መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
24ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

#PMOEthiopia
የ20 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ መረጃ ተሰብስቧል
********************
(ኢ ፕ ድ)
የ20 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ የአየር ቅየሳ መረጃ መሰብሰቡን የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በመላ ሀገሪቱ 480 ሺህ ስኩየር ኪሎ ሜትር የመሬት ካርታ ቅየሳ ሥራ ተከናውኗል። በአዲሱ በጀት ዓመት 130 ሺህ ስኩየር ኪሎ ሜትር የአየር ቅየሳ መረጃን ለመሰብሰብ መታቀዱ ተመልክቷል፡፡

በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስትቲዩት የአየር ላይ ቅየሳ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ከማሁ አብርሃም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአየር ቅየሳው በከተሞች በ2004 ዓ.ም፣ በገጠር ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ መሰብሰብ ተጀምሯል፡፡ እስካሁንም ለ20 ሚሊዮን የአርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ ምዝገባ ተከናውኗል።

እስከአሁን በሀገሪቱ 480 ሺህ ስኩየር ኪሎ ሜትር መሬት አየር ላይ የቅየሳ ሥራ መከናወኑን አቶ ከማሁ አስታውቀዋል።

በአየር ላይ ካርታ ቅየሳ ሥራው አማራ ክልል መቶ በመቶ ሽፋን አግኝቷል፣ ትግራይ 80 በመቶ፣ ኦሮሚያ ከ60 በመቶ በላይ፣ የቀድሞው ደቡብ 60 በመቶና ጋምቤላ ከአምስት በመቶ በላይ ሽፋን ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።

ውስን ሽፋን ባለባቸው ሌሎች ክልሎች ላይ ተገቢውን የአየር ካርታ ሽፋን ለመስጠት እንደሚሠራ……
https://press.et/?p=108129
ኮርፖሬሽኑ ከ100 በላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ሊገነባ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመጪዎቹ ዓመታት ከ100 በላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የእውቀትና የልምድ ሽግግር በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ገቢ በማስገኘት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው።

«ኮርፖሬሽኑ በመጪዎቹ አመታት ከ100 በላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመላ ሀገሪቱ የመገንባት እቅድ በማውጣት የኢንደስትሪላይዜሽን ሂደቱን ለማሳለጥ እና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ ለማድረግ አቅዷል» ብለዋል።

«ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አሁን ላይ ከአዋጭነት ጥናት ጀምሮ እስከ ተግባር ድረስ ያሉትን ፕሮጀክቶች ለማስፋፋት እና ለመደገፍ ፍላጎት አለው።

በዚህም ባንኮች የአዋጭነት ጥናቶችን እንዲሁም ሌሎች ዘዴዎችን መሠረት በማድረግ ብድር የማግኘት መንገዶችን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ የመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ ፕሮጀክቶችን ውጤታማነት የበለጠ ለማገዝ....

https://press.et/?p=108127