Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት ስለመፍጠር ዛሬ ከሰዓት መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
24ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

#PMOEthiopia
የ20 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ መረጃ ተሰብስቧል
********************
(ኢ ፕ ድ)
የ20 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ የአየር ቅየሳ መረጃ መሰብሰቡን የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በመላ ሀገሪቱ 480 ሺህ ስኩየር ኪሎ ሜትር የመሬት ካርታ ቅየሳ ሥራ ተከናውኗል። በአዲሱ በጀት ዓመት 130 ሺህ ስኩየር ኪሎ ሜትር የአየር ቅየሳ መረጃን ለመሰብሰብ መታቀዱ ተመልክቷል፡፡

በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስትቲዩት የአየር ላይ ቅየሳ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ከማሁ አብርሃም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአየር ቅየሳው በከተሞች በ2004 ዓ.ም፣ በገጠር ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ መሰብሰብ ተጀምሯል፡፡ እስካሁንም ለ20 ሚሊዮን የአርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ ምዝገባ ተከናውኗል።

እስከአሁን በሀገሪቱ 480 ሺህ ስኩየር ኪሎ ሜትር መሬት አየር ላይ የቅየሳ ሥራ መከናወኑን አቶ ከማሁ አስታውቀዋል።

በአየር ላይ ካርታ ቅየሳ ሥራው አማራ ክልል መቶ በመቶ ሽፋን አግኝቷል፣ ትግራይ 80 በመቶ፣ ኦሮሚያ ከ60 በመቶ በላይ፣ የቀድሞው ደቡብ 60 በመቶና ጋምቤላ ከአምስት በመቶ በላይ ሽፋን ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።

ውስን ሽፋን ባለባቸው ሌሎች ክልሎች ላይ ተገቢውን የአየር ካርታ ሽፋን ለመስጠት እንደሚሠራ……
https://press.et/?p=108129
ኮርፖሬሽኑ ከ100 በላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ሊገነባ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመጪዎቹ ዓመታት ከ100 በላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የእውቀትና የልምድ ሽግግር በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ገቢ በማስገኘት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው።

«ኮርፖሬሽኑ በመጪዎቹ አመታት ከ100 በላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመላ ሀገሪቱ የመገንባት እቅድ በማውጣት የኢንደስትሪላይዜሽን ሂደቱን ለማሳለጥ እና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ ለማድረግ አቅዷል» ብለዋል።

«ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አሁን ላይ ከአዋጭነት ጥናት ጀምሮ እስከ ተግባር ድረስ ያሉትን ፕሮጀክቶች ለማስፋፋት እና ለመደገፍ ፍላጎት አለው።

በዚህም ባንኮች የአዋጭነት ጥናቶችን እንዲሁም ሌሎች ዘዴዎችን መሠረት በማድረግ ብድር የማግኘት መንገዶችን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ የመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ ፕሮጀክቶችን ውጤታማነት የበለጠ ለማገዝ....

https://press.et/?p=108127
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ በፍትሐዊነት ላይ የተመሠረተ ዕድገት ለማስመዝገብ ያግዛታል
************************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ በመተባበርና በፍትሐዊነት ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማስመዝገብ ይረዳል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ/ር) በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፤ ብሪክስ በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት እሳት የመጫርና የጦር መሣሪያ የማቀበል ታሪክ የለውም። ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ የቡድኑ አባል በመሆኗ ከአባል ሀገራቱ ጋር በመከባበር፣ በመተባበርና በፍትሐዊነት ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማስመዝገብ ዕድል ታገኛለች።

ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ያላት ተሰሚነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት እያደገ መምጣቱ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ አንዱና ዋነኛው ማሳያ ነው ያሉት ዶክተር ያዕቆብ፤ አባልነቱን በጥንቃቄ በመጠቀም ማደግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የብሪክስ አባል መሆን ትልቅ ስኬት ቢሆንም ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎችም እንዳሉም አንስተው፤ ብሪክስ ከተቋቋመ 10 ዓመት ያስቆጠረ ቢሆንም ይበልጥ መጠናከር ያለበት ቡድን መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ እሳቸው ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሆነች ማለት በአንድ ጊዜ ከምዕራባውያን የንግድና የፖለቲካ ተጽዕኖ ተላቀቀች ማለት አይደለም፡፡

ይልቁንም በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች በአመዛኙ በዓለም ባንክና በምዕራባውያን በሚዘወሩ…

https://press.et/?p=108128
በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮው አረንጓዴ ዐሻራ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል በ2015 ዓ.ም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ከድር ለኢፕድ እንደገለጹት፣ ‹‹ነገን ዛሬ እንትከል›› በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በክልሉ እስካሁን 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል፡፡
በዚህም የዕቅዱን መቶ በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡

በክልሉ በዘንድሮው በአረንጓዴ ዐሻራ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ገልጸው፤ እስካሁን 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች መትከል በመቻሉ ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ ማሳካት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ለችግኞቹ 150 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን አመልክተው፤ ችግኞቹ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ መተከላቸውን ተናግረዋል፡፡ በችግኝ ተከላውም 17 ነጥብ 6 ሚሊዮን የኅብረተሰቡ ክፍሎች የተሳተፉበት መሆኑን .....
https://press.et/?p=108130