Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ዓለም አቀፍ የቀዳማዊ ልጅነት የልህቀት ስትራቴጂ ዓውደ-ጥናት ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የአለምአቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት አሰታወቀ።

መስከረም 27 ቀን 2016 ዓ.ም
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ዛሬ ይከፈታል
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የሪፐብሊኩ ፕሬዘዳንት በሚገኙበት ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

የሪፐብሊኩ ፕሬዘዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት በተገኙበት የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የሚያቀርቡ ይሆናል።

በምክር ቤቱ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የሐይማኖት አባቶች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ።

መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር ስኬታማ ውይይት አካሂዷል
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከመንግሥት፣ ከወጣቶች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ስኬታማ ውይይት ማከናወኑን አስታወቀ።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት ከመምህራን፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአካል ጉዳተኞች፣ ከወጣቶች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል። አሁን ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ከከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

በዚህም መንግሥት በሀገራዊ ምክክሩ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ስለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ግንዛቤ እንዲኖረው ተደርጓል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ኮሚሽኑ የምክክር ሂደቱን ከሚመራበት መሰረታዊ መርሆዎች አኳያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያከናወናቸው ውይይቶች ስኬታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።

“ኮሚሽኑ በተቋቋመበት አዋጅ መሰረት ገለልተኛ ነው። ተጠሪነቱም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው” ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ሀገራዊ

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ...............

https://press.et/?p=110924
ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ሀገራዊ እሴቶቻችንን እንዴት እንጠቀምባቸው?
************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ተከባብረውና ተቻችለው ሀዘናቸውን ሆነ ደስታቸውን እየተጋሩ በጋራ ኖረዋል፡፡

በዘመናት ሂደት በተፈጠሩ የባእዳን ትርክቶች ምክንያት አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ይስተዋላል፡፡

እነዚህ ልዩነቶች እየሰፉ ሄደው ዛሬ ላይ እዚህም እዚያ ግጭቶች ሲፈጠሩ ይስተዋላል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍም ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ የዝግጅት ሥራዎችን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

የዘርፉ ምሁራን ኢትዮጵያውያን አብሮነትን የሚያጠናክሩ፣ ችግሮች ሲፈጠሩም የሚፈቱበት ቱባ ሀገር በቀል እውቀቶች አሉና በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለባቸው እያሳሰቡ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሰጡት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህር አቶ አንዷለም አሰፋ እንደሚሉት፤ የሀገራዊ ምክክር ዋና ዓላማዎች ግንዛቤ መፍጠር፣ የጋራ መግባባት መገንባት እና ለአሳሳቢ ሀገራዊ……..

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=110920
በመዲናዋ እየተሰጠ በሚገኘው ነፃ የሕክምና አገልግሎት ከ112 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
👉በነፃ ሕክምናው ከ28 ሚሊዮን በላይ ብር ወጪ ተደርጓል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እየሰጠ በሚገኘው የክረምት ነፃ የሕክምና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ112 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታወቀ፡፡

ለነዋሪዎች በተደረገ የሜዲካል ሕክምና እስካሁን ከ28 ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ ብር ወጪ መደረጉም ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ጥሩነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከሰኔ ወር ጀምሮ እየሰጠ በሚገኘው የክረምት ነፃ የቅድመ በሽታ የመከላከልና ሕክምና የመስጠት ሥራ 112 ሺህ 624 ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፤ ለሜዲካል ሕክምናውም እስካሁን...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=110960
የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
👉 ከአጠቃላይ ተማሪዎች 3 ነጥብ 2 በመቶዎቹ ብቻ 50 በመቶና ከዛ በላይ አምጥተዋል
👉 ከ 3 ሺ 106 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺ 328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ በትምህርት ዘመኑ ፈተናውን ከወሰዱት 845ሺ በላይ ተማሪዎች ውስጥ 50 በመቶና ከዛ በላይ ያመጡት 27 ሺ267 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

ይህም ከአጠቃላይ ተማሪዎች 3 ነጥብ 2 በመቶ የሚሸፍን ነው።

ተማሪዎችን ካስፈተኑ 3 ሺ 106 ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንድ ሺ 328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ እንዳልቻሉም ገልጸዋል።

በዘንድሮው ዓመት በተፈጥሮ ሳይንስ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 649/700 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533/600 መሆኑንም አስታውቀዋል።

ለአንድ ጊዜ ብቻ ተብሎ የነበረው የሪሚዲያል ፕሮግራምም የሚጠበቀውን ያህል ተማሪ ባለማለፉ በዚህ ዓመትም እንደሚቀጥል ጨምረው ገልጸዋል።

በፋንታነሽ ክንዴ
መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም
ህጋዊ መንገዶችን በማስፋት ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል እየተሰራ ይገኛል
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ብሔራዊ የሰራተኞች ፍልሰት አስተዳደር ቴክኒካል ቡድን የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በምክክር መድረኩ ላይ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሚንስትር ዴታ ዶክተር አሰግድ ጌታቸዉ እንደገለፁት፤ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ህጋዊ መንገዶችን ማስፋት ይገባል።

በመሆኑም ሚኒስቴር መስሪቤቱ በውጭ አገራት ስራ ስምሪት ህጋዊ መንገዶችን ለማስፋት በመስራት ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

ህገወጥ ዝውውርን ለመከላከል በሚሰራው ተግባር የቴክኒክ ብድኑ መቋቋም ሚናዉ የጎላ ነዉ ሲሉ አስረድተዋል።

ዶክተር አሰግድ እንደገለጹትም፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህጋዊ ዝውውርን ለማስፋት በሚሰራው ስራ ዜጎች በዙ ወጪ ማዉጣት ሳይጠበቅባቸዉ የፓስፖርት እና የህክምና ወጪ በማውጣ መሄድ ለስራ ስምሪት መሄድ ይችላሉ።

የበረራ ቲኬት ወጪን የሚሄዱበት አገር የሚገኘዉ አሰሪ ኤጀንሲ የሚሸፍን ሲሆን፤ የጤና እንሹራንስም እንደሚገባ ገልፀዋል።

በአመለወርቅ ከበደ

መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ተከፍቷል
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የሪፐብሊኩ ፕሬዘዳንት በተገኙበት ዛሬ ተከፍቷል።

የሪፐብሊኩ ፕሬዘዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት በተገኙበት የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ እያቀረቡ ይገኛሉ።

በምክር ቤቱ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የሐይማኖት አባቶች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተዳምዋል።

መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም