በክልሉ 27 ቢሊዮን ብር የሚገመት የዜግነት አገልግሎት ተከናውኗል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል በ2016 በጀት ዓመት የመጀመርያ ሩብ ዓመት 27 ነጥብ 67 ቢሊዮን ብር የሚገመት የዜግነት አገልግሎት መከናወኑ የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ገለጸ።
የኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ሃላፊና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አስተባባሪ መሀመድ ናስር አባ ጀማል (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ፤ በ2011 ዓ.ም ጨፌ ኦሮሚያ ማንኛውም ዜጋ በሀገሪቱ ልማት ውስጥ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክትና ማንኛውንም ልማት የመደገፍ ግዴታ እንዳለበት በአዋጅ ደንግጓል።
በዚህም ዜጎች የሚያስፈጓቸው ልማቶች የመንግሥትን በጀት ሳይጠብቅ በራሱ እያከናውኑ ይገኛል ብለዋል።
ዶክተር መሀመድ በክልሉ የ2016 በጀት ዓመት ከተጀመረ በዜግነት አገልግሎት 27 ነጥብ 67 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሥራ በተለያየ ዘርፍ መሠራቱንና በዚህምበ 21 ሚሊዮን ሰዎች መሳተፋቸውን ገልጸዋል።
ክልሉ በ43 ዘርፍ የዜግነት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በተጠናቀቀው ክረምትም በችግኝ ተከላ፣ በትምህርት ቤቶች ግንባታና ደረጃ ማሻሻል ፣ የጤና ተቋማት ግንባታ፣ የደም ልገሳና የአቅመ ደካማዎች ቤት እድሳት ላይ በስፋት መሠራቱን .....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=110984

በክልሉ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተማሪዎች በ2016 የትምህርት ዘመን በትምህርት ገበታቸው ላይ ይሆናሉ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሰለሞን ገብረታትዮሰ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በክልሉ ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ የተዛባውን የትምህርት ሥርዓት በማስተካከልና ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ለማስጀመር የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ይገኛሉ።
በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህም ከነሀሴ 25 እስከ መስከረም 12 የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ የነበረ ሲሆን በመስከረም 16 ጀምሮ የመማር ማስተማር ሂደት ተጀምሯል።
በግጭት ወቅት የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ በአንድ ዓመት ሁለት የትምህርት እርከን…
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=110998

ፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀመረ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማካሄድ ጀመሯል፡፡
ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ቃለጉባዔውን መርምሮ በማጽደቅ ጉባኤውን ማካሄድ የቀጠለ ሲሆን በጉባኤው ያጸደቃቸውን አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው ይጠበቃል።
መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም

‹‹በ2016 ትምህርት ቢጀመርም አሁንም መጻሕፍት አልደረሱንም››-ተማሪዎችና ርዕሳነ መምህራን
****************
(ኢ ፕ ድ)
የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት የተጀመረ ቢሆንም የመማሪያ መጻሕፍት እንዳልደረሳቸው የአዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና ርዕሰ መምህራን ገለጹ።
ከጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር የመጻሕፍት የህትመት ውጤቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
በጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ በለጡ በሪሁ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገረችው፤ ትምህርታቸውን መምህራን በሚሰጧቸው ማስታወሻ እና በቴሌግራም በሚለቀቅ ሶፍትኮፒ እየተማሩ እንደሆነ ገልጻ ምንም አይነት መማሪያ መጻሕፍት እንዳልደረሰ ተናግራለች።
ይህም በመማሪያ ክፍል ውስጥ መምህራን ከሚሰጡት ማስታወሻ ውጪ የተብራራ ጽሁፍ ለማግኘት ብሎም ለሚቀጥለው ትምህርት እራሳቸውን ….
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=110973

በሞተር ብስክሌትና በባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ
***********
(ኢ ፕ ድ)
በሞተር ብስክሌቶችና ሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ክልከላ ከዛሬ ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ያነሳ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
ሆኖም ፍቃዱ የሚመለከተው በቢሮው እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው መስመርና ታፔላ ያላቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎችን ብቻ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።
ሞተር ብስክሌቶችን በተመለከተ ፍቃዱ የሚመለከተው በአዋጁ መሰረት ሰሌዳ ወስደው፣ ሕጋዊ መንቀሻቀሻ ፍቃድና ጂፒኤስ (GPS) ያስገጠሙትን ብቻ መሆኑን ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።
ከትራንስፖርት ቢሮው ሕጋዊ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ቢሮው አሳስቧል።

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
ዛሬ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ልምዳችንን በአገር አቀፍ ልምድ ልውውጥ መድረክ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ ሚኒስትሮች፣ የኦሮሚያና የድሬዳዋ ከተማ አመራሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም የመስኩ ባለሙያዎች በተገኙበት ልምዳችንን ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች አካፍለናል።
ባለፉት 2 ዓመታት ለትውልድ ግንባታ ትኩረት ሰጥተን፣ የአስፈጻሚ ተቋማትን ቅንጅት ፈጥረን፣ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተን በአሰራርና በአደረጃጀት ስራውን መርተናል።
በዚህም ወላጆችንና አሳዳጊዎች በዕውቀት ሕጻናት እንዲያሳድጉ 2500 የቤት ለቤት ተንከባካቢዎችን አሰልጥነን አሰማርተን፣ 56 ጤና ጣቢያዎችንና 46 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን አሸጋግረን፣ 152 መዋለ ህጻናትን እና 156 የመጫወቻ ስፍራዎችን ገንብተን አዲስ አበባ ከተማን የሕጻናት ማደጊያ ምርጥ አፍሪካዊ መዲና ለማድረግ በትጋት በመስራት ያካበትነውን ልምድ አጋርተናል።
ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ለአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች ልምዳችንን ያካፈልን ሲሆን፣ የትውልድ ግንባታ ስራችን የሀገር አቀፍ ትኩረት እንዲሆን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ተወስኗል።
በስራዎቻችን ሁሉ ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደረጉልንን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ማመስገን እወዳለሁ።