‹‹በ2016 ትምህርት ቢጀመርም አሁንም መጻሕፍት አልደረሱንም››-ተማሪዎችና ርዕሳነ መምህራን
****************
(ኢ ፕ ድ)
የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት የተጀመረ ቢሆንም የመማሪያ መጻሕፍት እንዳልደረሳቸው የአዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና ርዕሰ መምህራን ገለጹ።
ከጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር የመጻሕፍት የህትመት ውጤቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
በጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ በለጡ በሪሁ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገረችው፤ ትምህርታቸውን መምህራን በሚሰጧቸው ማስታወሻ እና በቴሌግራም በሚለቀቅ ሶፍትኮፒ እየተማሩ እንደሆነ ገልጻ ምንም አይነት መማሪያ መጻሕፍት እንዳልደረሰ ተናግራለች።
ይህም በመማሪያ ክፍል ውስጥ መምህራን ከሚሰጡት ማስታወሻ ውጪ የተብራራ ጽሁፍ ለማግኘት ብሎም ለሚቀጥለው ትምህርት እራሳቸውን ….
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=110973

በሞተር ብስክሌትና በባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ
***********
(ኢ ፕ ድ)
በሞተር ብስክሌቶችና ሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ክልከላ ከዛሬ ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ያነሳ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
ሆኖም ፍቃዱ የሚመለከተው በቢሮው እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው መስመርና ታፔላ ያላቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎችን ብቻ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።
ሞተር ብስክሌቶችን በተመለከተ ፍቃዱ የሚመለከተው በአዋጁ መሰረት ሰሌዳ ወስደው፣ ሕጋዊ መንቀሻቀሻ ፍቃድና ጂፒኤስ (GPS) ያስገጠሙትን ብቻ መሆኑን ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።
ከትራንስፖርት ቢሮው ሕጋዊ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ቢሮው አሳስቧል።
መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
ዛሬ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ልምዳችንን በአገር አቀፍ ልምድ ልውውጥ መድረክ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ ሚኒስትሮች፣ የኦሮሚያና የድሬዳዋ ከተማ አመራሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም የመስኩ ባለሙያዎች በተገኙበት ልምዳችንን ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች አካፍለናል።
ባለፉት 2 ዓመታት ለትውልድ ግንባታ ትኩረት ሰጥተን፣ የአስፈጻሚ ተቋማትን ቅንጅት ፈጥረን፣ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተን በአሰራርና በአደረጃጀት ስራውን መርተናል።
በዚህም ወላጆችንና አሳዳጊዎች በዕውቀት ሕጻናት እንዲያሳድጉ 2500 የቤት ለቤት ተንከባካቢዎችን አሰልጥነን አሰማርተን፣ 56 ጤና ጣቢያዎችንና 46 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን አሸጋግረን፣ 152 መዋለ ህጻናትን እና 156 የመጫወቻ ስፍራዎችን ገንብተን አዲስ አበባ ከተማን የሕጻናት ማደጊያ ምርጥ አፍሪካዊ መዲና ለማድረግ በትጋት በመስራት ያካበትነውን ልምድ አጋርተናል።
ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ለአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች ልምዳችንን ያካፈልን ሲሆን፣ የትውልድ ግንባታ ስራችን የሀገር አቀፍ ትኩረት እንዲሆን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ተወስኗል።
በስራዎቻችን ሁሉ ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደረጉልንን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ማመስገን እወዳለሁ።

ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ የ25 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ሥምምነት ተፈራረሙ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ የ25 ሚሊየን ዶላር የሚደርስ የድጋፍ ሥምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ድጋፉ በኖርዌይ መንግስት የተለቀቀው ድጋፍ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የደን መጨፍጨፍ እና የደን መራቆትን ለመግታት ብሎም የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የሚውል ነው ተብሏል።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቴዬን ክርስቴንሰን መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ያመላክታል፡፡

አገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኢንቨስትመንት ኤግዚቢሽን በሳይንስ ሙዚየም ተከፈተ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን አገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኢንቨስትመንት ኤግዚቢሽን ከፈቱ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ያላትን ሠፊ የቱሪዝም ሀብት በአንድ አዳራሽ ማሳያት ከባድ ቢሆንም፤ ቱሪዝም ሚኒስቴር ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግንና ሀብታችንን ይበልጥ ለማስተዋወቅ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ኤግዚቢሽኑ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁሶችን ጨምሮ ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ ባህልና እሴቶች ቀርበውበታል።
በአገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኢንቨስትመንት ኤግዚቢሽኑ ከ100 በላይ በዘርፉ የተሰማሩ ሆቴሎች፣ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ የክልል ቱሪዝም ቢሮዎች፣ ባንኮችና የቴክኖሎጂ ተቋማት ተሳትፈዋል።
የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኤግዚቢሽኑ ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ታውቋል።
በጌትነት ተሥፋማርያም

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይአሕመድ መልዕክት‼️
ብዙ ታሪክ፣ ቅርስ ፣ባህል ፣ የተፈጥሮ ስጦታዎች ፣አዕዋፍ ፣የዱር አራዊትና ሊጎበኙ የሚችሉ ድንቅ ሁነቶች እንዳሉን ግምት ውስጥ በማስገባት ከኢኮኖሚው ዘርፍ ዋና ምሦሦዎች አንዱ የቱሪዝም ሴክተሩ ነው። ዛሬ የተከፈተው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን ምቹ መዳረሻ የሚያደርጋትን በናሙና እንዲያዩ ዕድል ይሰጣል። ያለንን ዐቅም ለማውጣት፣ ኢትዮጵያን የብዙ ውበቶች እና ግኝቶች መዳረሻ አድርጎ ለማስተዋወቅ እና ለማገልገል ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀገራችሁ ያላትን ሀብት ማየት፣ ማውጣት፣ ማስተዋወቅ እና ማገልገል ይጠበቅባችኋል።