Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በድሬዳዋ የተገነባው የመገናኛ ናቪጌሽንና ቅኝት መቆጣጠሪያ መሳሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
********
(ኢ ፕ ድ)

ከድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በ5 ነጥብ 5 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ላለፉት 12 ወራት በስፔይን ባለሙያዎች በከፍተኛ መዋዕለ-ንዋይ ሲገነባ የአይሮፕላን አቅጣጫና ርቀት መለኪያ መሳሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

ዘመናዊ መሳሪያው 54 አንቴናዎች ያሉት 360 ዲግሪ በሁሉም አቅጣጫ የሚመጡ አውሮፕላኖችን በመለየትና አቅጣጫቸውን በመቆጣጠር አስተማማኛ በሆነ መልኩ መንገድ ሳይስቱ እንዲያርፉ የሚያስችል ነው።

በአለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት መስፈርት መሰረት ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተለይም የበረራ መነሻና መዳረሻ እየተበራከተ ሲሄድ ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ የመቆጣጠሪያ መሳሪያ እንደሆነ በምስራቅ ማዕከላዊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሽመልስ ተናግረዋል፡፡

በጅግጅጋ፣ በጎዴና ቀብሪደሀር ከሚገኙ አራት ኤርፖርቶች አንዱና ትልቁ የሆነው የድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የዚህ ዘመናዊ መሳሪያ ባለቤት ሆናል።

ከኤክስፖርት ጋር ተያይዞ የበረራ ቁጥሩ እየጨመረ ለመጣው የአውሮፕላኖች ምልልስና ኤርፖርቱ በሚታወቅበት ከፓይለት ተማሪዎች ልምምድ ጋር ተያይዞ የሚደረገውን የአየር ትራንስፖርት እንቅስቃሴ አስተማማኝ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡

በአሁን ሰዓት የድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የበረራ ተማሪዎች ማሰልጠኛ ከመሆኑ በተጨማሪ በቀን እስከ 44 የሚደርሱ መደበኛ በረራዎችን፣ በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል አቋርጠው የሚያልፉ አለም አቀፍ በረራዎችን ያሰተናግዳል።

ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
“በስኬታማነቱ በአፍሪካ ተጠቃሽ የሆነ ሀገራዊ ምክክር እንዲሆን አስበን እየሠራን ነው”
- አምባሳደር መሀሙድ ድሪር የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር
*******
(ኢ ፕ ድ)

በስኬታማነቱ በአፍሪካ ተጠቃሽ የሆነ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ አስበን እየሠራን ነው ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር ገለጹ፡፡

ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከሀገራዊ ምክክሩ አሳታፊነትና አካታችነት፣ ከአጀንዳዎቹና ካለን ሕዝብ ብዛት፣ አኳያ በአፍሪካ በስኬታማነቱ ተጠቃሽ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ ታስቦ እየተሠራ ነው።

በአፍሪካ ስኬታማ ሀገራዊ ምክክር ያደረጉ ሀገራት ምክክሩን ያደረጉት በቁንፅል ጉዳዮች ላይ መሆኑን ገልጸው፤ ለአብነት ያህል የኬንያን የሀገራዊ ምክከር ሂደት በድህረ ምርጫ የተከሰቱ ሁከቶችን ለማርገብና መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማጽናት የተካሄደ በመሆኑ አጀንዳዎቹ ውስን መሆናቸውን አውስተዋል፡፡

በአንጻሩ ‹‹በኢትዮጵያ የሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር እንደ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይሄ ነው አጀንዳው፤ ይሄ መሆን አለበት የምንልበት አግባብ ባይኖርም እስካሁን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113162
በ10 ከተሞች በ523 ሚሊዮን ዶላር የመጠጥ ውሃና አካባቢ ንጽህና ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው
******
(ኢ ፕ ድ)

በውጭ ድርጅቶች ድጋፍ በ10 ከተሞች በ523 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የመጠጥ ውሃና የአካባቢ ንጽህና (ሳኒቴሽን) ላይ ትኩረት ያደረጉ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኑረዲን መሐመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዓለም ባንክ፣ በፈረንሳይ ልማት ድርጅት እና ማቺር ፈንድ በተባለ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ የመጠጥ ውሃና የአካባቢ ንጽህና (የሳንቴሽን) ችግር ላለባቸው 10 ከተሞች ችግሮቻቸውን የሚፈቱ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ።

እንደ ኃላፊው ገለፃ፤ በዓለም ባንክ 445 ሚሊዮን ዶላር፣ የፈረንሳይ ልማት ድርጅት 18 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም 60 ሚሊዮን ዶላር ማቺር ፈንድ በተባለ ድርጅት ፋይናንስ አድራጊነት.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113169
ክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች የማጓጓዝና የማቋቋም ሥራ እያከናወነ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)
የመንግሥት ሠራተኞች እንዳይጉላሉ ልዩ ውሳኔ በመወሰን ከሀዋሳ ወደ ክልሉ የማጓጓዝና የማቋቋም ሥራ እያከናወነ መሆኑን ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገለጸ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግሥት ከሀዋሳ ወደ ተመደቡበት ስድስቱ የክልሉ ማዕከላት የሚንቀሳቀሱ የመንግሥት የሚጋጥማቸው ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማቃለል ውሳኔ አሳልፏል። በውሳኔው መሠረትም የዕቃ ማጓጓዣ ፣ ቤት መፈለጊያ እንዲሁም በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች እንዳይቸገሩ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ሠራተኞችን የማጓጓዝ ሥራ እየሠራ ነው።

የቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በአራት ክልሎች ከተከፈለ በኋላ በቀመር ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚደርሰው የሠራተኛ ቁጥር በላይ መቀበል አለብን ብለን እየሠራን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113167
ለኢንተርፕራይዞች ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር ተፈጥሯል
*****
(ኢ ፕ ድ)

በ2016 በጀት ዓመት ሶስት ወራት ለኢንተርፕራይዞች ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የሀገር ውስጥ የገበያ ትስስር መፈጠሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ብርሃኑ ረዳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለሁለት ሺህ 319 ኢንተርፕራይዞች ከሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የሀገር ውስጥ የገበያ ትስስር መፍጠር ተችሏል።

በሩብ ዓመቱ ለኢንተርፕራይዞች አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር የሀገር ውስጥ የገበያ ትስስር ለመፍጠር መታገዱን ገልጸው፤ ለሁለት ሺህ 319 ኢንተርፕራይዞች ከ ሁለት ነጥብ 202 ቢሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113181
አሕጉራትን እያስተሳሰረ ያለው “የቻይና ቀበቶ"
******
(ኢ ፕ ድ)
ቻይና እ.አ.አ. በ 2013 ይፋ ያደረገችው “ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ” እስያን፣ አውሮፓንና አፍሪካን በየብስ፣ በአየርና በውቅያኖስ በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር ያለመ ነው። ይህም የዓለም ሀገራትን በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች ለማቀራረብ የተቀረጸ ፕሮጀክት መሆኑ ነው የሚገለጸው።

ከ151 ሀገራት የተውጣጡ ከ10 ሺህ በላይ ተወካዮችና 41 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተሳተፉበት ሦስተኛው የ “ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ” ጉባዔ በቅርቡ በቻይና ተካሂዷል። መድረኩ የፕሮጀክቱ 10ኛ ዓመት የተከበረበትም ጭምር ነው።

ለመሆኑ ይህ የቻይና ግዙፍ የትብብር ማዕቀፍ ባለፉት 10 ዓመታት በተለይም ለአፍሪካውያን ምን አስገኝቷል? ከምዕራባውያን የትብብር ማዕቀፎችስ በምን ይለያል ?

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ዳዊት ሃዬሶ (ዶ/ር) “የዓለምን ኢኮኖሚ ለመምራት ወደፊት እየተጠጋች ያለች ሀገር ናት” የሚሏት ቻይና፣ ዘላቂ የሆነ የጋራ ዕድገት ማስመዝገብ የሚቻለው ከአጋር ሀገራት ጋር በጋራ ማደግ ሲቻል ነው በሚል መርህ አህጉራትን የሚያስተሳስረውን “ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ” ቀርጻ ላለፉት 10 ዓመታት ስትተገብረው መቆየቷን ይናገራሉ።

ኢኒሼቲቩ ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞች አሉት የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፣ ባለፉት 10 ዓመታት የአፍሪካ ሀገራትን ተጠቃሚ አድርጓል ባይ ናቸው። ከኢትዮጵያ ብንነሳ ከአዲስ አበባ – ጅቡቲ ያለው የባቡር መንገድ የተገነባው በዚህ ኢኒሼቲቭ ድጋፍ ነው። ግንባታው ከዚህ በፊት ተሳቢ መኪኖች በአነስተኛ መጠን እየተመላለሱ.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113182
የአፍሪካ ሀገራት በማዕድን ውጤቶች ላይ ዕሴት በመጨመር ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ አለባቸው
*****
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ ሀገራት ከድህነት ለመውጣት ያስቀመጡትን አጀንዳ 2063ን ለማሳካት በማዕድን ዘርፉ ጥሬ እቃዎችን ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ በመላክ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው ተገለጸ።

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በማእድን ዘርፉ ላይ በማተኮር በጋራ ያዘጋጁት የውይይት መድረክ ትናንት ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚደንት አብርሃም ደበበ (ዶ/ር)፤ ኮሚሽኑ በእውቀት ግንባታ፣ በፈጠራና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባዋል። አዳዲስ ምርምሮችን በማፍለቅ ምርት ከውጭ ማስገባት .....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113183
በገበታ ለትውልድ በመገንባት ላይ ያሉና የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ ሰፊ ዕድል ይፈጥራሉ‼️

በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ የተገነቡ፣ በመገንባት ላይ ያሉና የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ ሰፊ ዕድሎች እየፈጠሩለት ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በያዝነው የፈረንጆች አመት በመጀመሪያዎቹ 7 ወራት የዓለም ቱሪዝምን በመሳብ 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የዓለም አቀፉ ቱሪዝም ተቋም አስታወቀ፡፡ ተቋሙ 2023 ከጥር እስከ ሐምሌ ያለውን የሀገራትን የቱሪዝም ፍሰት ከ2019 ጋር በማነጻጸር ይፋ አድርጓል፡፡

ኢትዩጵያ በያዝነው 2016 ዓ.ም መጀመሪያ ሁለት ቅርሶቿን በዩኔስኮ መዝገብ አካትታለች።

በተያዘው 2016 በጀት ዓመት አንድ ሚሊዮን የውጭ ሀገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ከሚመጡ የውጭ ሀገራት ዜጎች ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ኢፕድ መዘገቡ ይታወሳል።

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
161 የፌዴራል ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ግዢ ለመፈጸም ዕቅድ አቅርበዋል
****
(ኢ ፕ ድ)

ከ169 የፌዴራል ተቋማት 161 ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ግዢ ለመፈጸም ዕቅድ አቅርበዋል።

የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ኤሌክትሮኒክስ ግዢ ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ዉይይት እያደረገ ይገኛል።

በዉይይቱ ላይ የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ እንደገለጹት በተያዘዉ በጀት ዓመት 161 ተቋማት ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ያቀርባሉ።

በ2016 ዓ.ም የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ግዢ ሙሉ ለሙሉ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም ጠቁመዋል።

በግዢ ስርዓቱ ሲያጋጥም የነበረዉን ሌብነት ከማስቀረቱም በተጨማሪ ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ ነዉ ብለዋል።

በመጀመሪያወዉ ሩብ ዓመትም 2802 ጨረታዎች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ መዉጣታቸዉ ተጠቁሟል። 3,800 የሚጠጉ የንግዱ ማህበረሰብም በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግዢ እየፈጸመ እንደሆነም ተገልጿል።

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
ጥቅምት 27 ቀን 2016  ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️