Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ ከአምስት ሺህ በላይ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ተያዘ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ አምስት ሺህ 426 ሕገ-ወጥ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ወልድያ የፍተሻ ጣቢያ ላይ ተያዘ።

ከአሸባሪዎች ተልዕኮ ተቀብሎ በመሃል ሀገር በአዲስ አበባ እና በአካባቢው የሽብር ተግባር ለመፈፀም መነሻውን ቆቦ ከተማ ያደረገው ተጠርጣሪ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አማ 28239 በሆነ ሀይሩፍ መኪና ላይ ጥይት ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በማጓጓዝ ላይ እንዳለ የወልድያ ፍተሻ ጣቢያን ለማለፍ ሲሞክር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተሽከርካሪው ላይ ባደረገው ጥብቅ ፍተሻ 5 ሺህ 4 መቶ 26 ሕገ-ወጥ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት መያዙን አስታውቋል።

ጥይቱን አስጭኖ ሲያጓጉዝ የነበረው ተጠርጣሪ እና የመኪናው ሾፌርም ከነ-ኤግዚብቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል ።

አሸባሪዎች በተደጋጋሚ በመሀል ሀገር በአዲስ አበባና አካባቢው የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የሚወጥኑት የሽብር ዓለማ በየጊዜው በፀጥታና ደኅንነት አካላት ፈጣን ሕጋዊ እርምጃ እየከሸፈ እንደሚገኝ የገለፀው ፖሊስ እነዚህ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎች በሽብር ቡድኑ እጅ ቢገቡ ኖሮ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ይችሉ እንደነበር አስታውቋል።

ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመቆጣጠር በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ኬላዎች ላይ የሚደረገው ፍተሻ ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፖሊስ ገልጿል።

ኀብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ተገቢውን ቅንጅት በማድረግ በየትኛውም ደረጃ የሚወጠኑ የሽብር ተግባራትን ለመቆጣጠር የዜግነት ድርሻውን ይወጣ ዘንድ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባሕር ዳር ገቡ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባሕር ዳር ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሕር ዳር ሲገቡ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️

በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ አዲስ የተገነባውን ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያን ዛሬ ወደ ሥራ አስገብተናል። አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ ፍትሐዊ የልማት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ እንዲሁም ምቹ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው።

የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም
የማራቶን ባለክብረወሰኑ አትሌት በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የወቅቱ የማራቶን የአለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነው ኬንያዊው አትሌት ኬልቪን ኪፕተም በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል።

በአደጋው ከ24 አመቱ አትሌት ጋር ሩዋንዳዊው የአትሌቱ አሰልጣኝ ጋርቫይስ ሀኪዚማና ህይወቱ ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኪፕተም በ2024 ፓሪስ ኦሊምፒክ ኬንያን ለመወከል ከተመረጡ አትሌቶች አንዱ ሲሆን፣ በዘንድሮው አመት የቺካጎ ማራቶን 2:00:35 በሆነ ሰአት በሌላኛው ኬንያዊ አትሌት ተይዞ የቆየውን የማራቶን ክብረወሰን ማሻሻሉ ይታወቃል።

የኬንያ ተቃዋሚ መሪ እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ሀገሪቱ "እውነተኛ ጀግና" አጥታለች እናም የኬንያ አትሌቲክስ እያለቀሰ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የአለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሴባስቲያን ኮ ፣ ኪፕቱም “የማይታመን ውርስ ትቶ የሄደ የማይታመን አትሌት ነው ፣ በጣም እንናፍቀዋለን” ብለዋል ።

የትራፊክ አደጋውን በተመለከተ ኪፕቱም እያሽከረከረ እንደነበር እና ተሽከርካሪው ፍጥነቱን መቆጣጠር እንደተሳነው ተጠቁሟል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በመኪና ውስጥ ሶስተኛ ተሳፋሪ የነበረችው ግለሰብ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች።

የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም
ከ15 ሺ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል
***********************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዳማ ዲስትሪክት በተያዘው በጀት አመት በመጀመሪያው ስድስት ወራት ከ15 ሺ በላይ አዲስ የኃይል ጠያቂ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

ዲስትሪክቱ አዳማ እና አዳማ ዙሪያ እንዲሁም ሞጆ እና ቢሾፍቱን ጨምሮ በርካታ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙበት አካባቢ ሲሆን ከ698 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ጨምሮ ከ293 ሺ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡

አገልግሎቱ አካባቢው ላይ ያለውን የኃይል ተደራሽነት ከማስፋቱ ባሻገር አካባቢው ላይ የኃይል መቆራረጥ ሲኖር በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል ስካዳ የተባለ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ በማዋል የአስቸኳይ ጥገኛ ስራዎችን ከሲስተም ጋር በማገናኘት እየሰራ ይገኛል፡፡

አዳማ ላይ ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ያለ በመሆኑ የኃይል አቅርቦቱን ለማሳደግ ከጉራጃ ማሪያም የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወጪ በማድረግ ከተማዋ ላይ ያለውን የኃይል ጭነት በማቃለል የኃይል አቅርቦቱን ተደራሽ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡

ዲስትሪክቱ ደንበኞች ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ተጠቅመው የፍጆታ ሂሳባቸውን እንዲከፍሉ ከማድረግ አኳያ ከባንኮች እና ከቴሌ ጋር በትብብር በመስራት አሁን ላይ 92 በመቶ የሚሆኑትን ደንበኞች ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ተጠቅመው መክፈል እንዲችሉ ተደርጓል፡፡

በቀጣይ በዲስትሪክቱ ያለውን የኃይል አቅርቦት በማሻሻል ተጨማሪ ደንበኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም የኃይል መቆራረጡን ለመቀነስ እንዲያስችል የዲስትሪቡሽን ኔትወርክ ማሻሻያ ጥናት እየተካሄደ ሲሆን የማሻሻያ ስራው ሲጠናቀቅ አካባቢው ጥራት ያለውና አስተማማኝ የሃይል አቅርቦት ሊኖር እንደሚችል የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት አስታውቋል።

የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም
አጀንዳ 2063፤ ምን አሳካ፣ ምን ቀረ?
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአፍሪካ ኅብረት 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር የአፍሪካውያን አንድነትና ብልጽግና መገለጫ የሆነውን አጀንዳ 2063ን ይፋ አድርጓል፡፡

አጀንዳ 2063 አፍሪካውያንን በመሠረተ ልማት የማስተሳሰር፣ የሥራ አጥ ቁጥርን የመቀነስ፣ አፍሪካውያን ተመሳሳይ መገበያያ ገንዘብ እንዲኖራቸው የማድረግ፣ የአፍሪካ ኅብረትን ማጠናከር፣ ነፃ የንግድ ቀጣናዎችን መመሥረት እና ሌሎች በርካታ ግቦችን የሰነቀ ነው፡፡

አጀንዳ 2063 ይፋ ከተደረገ ጀምሮ ምን ምን እቅዶች ተሳኩ፣ ቀሪ ሥራዎች ምንድን ናቸው፣ ከኢትዮጵያስ ምን ይጠበቃል?

የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የፖሊሲ ጉዳዮች አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ(ዶ/ር) እንደሚሉት አጀንዳ 2063 ለአፍሪካውያን እድገትና ይህ ካልሆነ ግን አፍሪውያን ያለሙትን ብልጽግና እውን የማድረግ ጥረታቸውን ለማሳካት ይከብዳቸዋል፤ ሕዝቦቻቸውንም ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ብሎም ከግጭት ለማላቀቅ አይችሉም። አንድነት የሚረዱ በርካታ ግቦችን የያዘ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120635