"የዓድዋ ድል መታሰቢያ ታላቁ የዓድዋ ገድል የደመቀበት ተበታትነው የነበሩ የታሪክ ማስረጃዎች የተሰበሰቡበትና የተረሱት የታወሱበት ነው"
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ታላቁ የዓድዋ ገድል የደመቀበት ተበታትነው የነበሩ የታሪክ ማስረጃዎች የተሰበሰቡበትና የተረሱት የታወሱበት ነው ብለዋል።
በዓድዋ ጦርነት ኢትዮጵያውያን ልዩነትን ወደ ጎን በመተው በአንድነት ወደ ዓውደ ውጊያው ተምመዋል ያሉት ከንቲባዋ በዚህም የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነት ቀንዲል የሆነውን የዓድዋ ድልን አስመዝግበዋል ብለዋል።
መታሰቢያው የታሪክና ትርክት ክፍተትን ከመሙላት ባለፈም ስብራትን የሚጠግን እንደሚሆን እናምናለን ብለዋል።
የዓደዋ ድል መታሰቢያ ጀግኖችን በሚገባቸው ከፍታ ያስቀመጠ መሆኑን ጠቅሰው ትውልዱ በአንድነት ሆኖ ማሸነፍንና የሀገር ፍቅርን የሚማርበት መሆኑንም ገልፀዋል።
የዓድዋ ድል መታሰቢያ መላ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቋንቋ እንዲግባቡ የማድረግ ኃይል ያለው መሆኑን በመግለጽ ትናንትን ከዛሬ ዛሬን ከነገ የሚያስተሳስር ድልድያችን በመሆኑ የመጪው ትውልድ ስጦታችን ነው ብለዋል።
በማርቆስ በላይ
የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
እንደ "አድዋው ዘማቾች" ከሰሜንም ፣ ከደቡብም ፣ ከምስራቅና ከምዕራቡም ጥሪያችንን አክብራችሁ በዚህ ታሪካዊ ፕሮግራም ላይ ለታደማችሁ እንዲሁም ለፕሮግራሙ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ አካላት ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ::
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን
ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር ።

ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ ከአምስት ሺህ በላይ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ተያዘ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ አምስት ሺህ 426 ሕገ-ወጥ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ወልድያ የፍተሻ ጣቢያ ላይ ተያዘ።
ከአሸባሪዎች ተልዕኮ ተቀብሎ በመሃል ሀገር በአዲስ አበባ እና በአካባቢው የሽብር ተግባር ለመፈፀም መነሻውን ቆቦ ከተማ ያደረገው ተጠርጣሪ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አማ 28239 በሆነ ሀይሩፍ መኪና ላይ ጥይት ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በማጓጓዝ ላይ እንዳለ የወልድያ ፍተሻ ጣቢያን ለማለፍ ሲሞክር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተሽከርካሪው ላይ ባደረገው ጥብቅ ፍተሻ 5 ሺህ 4 መቶ 26 ሕገ-ወጥ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት መያዙን አስታውቋል።
ጥይቱን አስጭኖ ሲያጓጉዝ የነበረው ተጠርጣሪ እና የመኪናው ሾፌርም ከነ-ኤግዚብቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል ።
አሸባሪዎች በተደጋጋሚ በመሀል ሀገር በአዲስ አበባና አካባቢው የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የሚወጥኑት የሽብር ዓለማ በየጊዜው በፀጥታና ደኅንነት አካላት ፈጣን ሕጋዊ እርምጃ እየከሸፈ እንደሚገኝ የገለፀው ፖሊስ እነዚህ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎች በሽብር ቡድኑ እጅ ቢገቡ ኖሮ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ይችሉ እንደነበር አስታውቋል።
ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመቆጣጠር በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ኬላዎች ላይ የሚደረገው ፍተሻ ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፖሊስ ገልጿል።
ኀብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ተገቢውን ቅንጅት በማድረግ በየትኛውም ደረጃ የሚወጠኑ የሽብር ተግባራትን ለመቆጣጠር የዜግነት ድርሻውን ይወጣ ዘንድ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።
የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባሕር ዳር ገቡ
***
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባሕር ዳር ገብተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሕር ዳር ሲገቡ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️
በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ አዲስ የተገነባውን ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያን ዛሬ ወደ ሥራ አስገብተናል። አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ ፍትሐዊ የልማት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ እንዲሁም ምቹ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው።