የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️
በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ አዲስ የተገነባውን ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያን ዛሬ ወደ ሥራ አስገብተናል። አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ ፍትሐዊ የልማት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ እንዲሁም ምቹ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው።
የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም

የማራቶን ባለክብረወሰኑ አትሌት በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የወቅቱ የማራቶን የአለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነው ኬንያዊው አትሌት ኬልቪን ኪፕተም በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል።
በአደጋው ከ24 አመቱ አትሌት ጋር ሩዋንዳዊው የአትሌቱ አሰልጣኝ ጋርቫይስ ሀኪዚማና ህይወቱ ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።
ኪፕተም በ2024 ፓሪስ ኦሊምፒክ ኬንያን ለመወከል ከተመረጡ አትሌቶች አንዱ ሲሆን፣ በዘንድሮው አመት የቺካጎ ማራቶን 2:00:35 በሆነ ሰአት በሌላኛው ኬንያዊ አትሌት ተይዞ የቆየውን የማራቶን ክብረወሰን ማሻሻሉ ይታወቃል።
የኬንያ ተቃዋሚ መሪ እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ሀገሪቱ "እውነተኛ ጀግና" አጥታለች እናም የኬንያ አትሌቲክስ እያለቀሰ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የአለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሴባስቲያን ኮ ፣ ኪፕቱም “የማይታመን ውርስ ትቶ የሄደ የማይታመን አትሌት ነው ፣ በጣም እንናፍቀዋለን” ብለዋል ።
የትራፊክ አደጋውን በተመለከተ ኪፕቱም እያሽከረከረ እንደነበር እና ተሽከርካሪው ፍጥነቱን መቆጣጠር እንደተሳነው ተጠቁሟል።
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በመኪና ውስጥ ሶስተኛ ተሳፋሪ የነበረችው ግለሰብ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች።

ከ15 ሺ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል
***********************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዳማ ዲስትሪክት በተያዘው በጀት አመት በመጀመሪያው ስድስት ወራት ከ15 ሺ በላይ አዲስ የኃይል ጠያቂ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡
ዲስትሪክቱ አዳማ እና አዳማ ዙሪያ እንዲሁም ሞጆ እና ቢሾፍቱን ጨምሮ በርካታ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙበት አካባቢ ሲሆን ከ698 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ጨምሮ ከ293 ሺ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡
አገልግሎቱ አካባቢው ላይ ያለውን የኃይል ተደራሽነት ከማስፋቱ ባሻገር አካባቢው ላይ የኃይል መቆራረጥ ሲኖር በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል ስካዳ የተባለ ቴክኖሎጂ ስራ ላይ በማዋል የአስቸኳይ ጥገኛ ስራዎችን ከሲስተም ጋር በማገናኘት እየሰራ ይገኛል፡፡
አዳማ ላይ ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ያለ በመሆኑ የኃይል አቅርቦቱን ለማሳደግ ከጉራጃ ማሪያም የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወጪ በማድረግ ከተማዋ ላይ ያለውን የኃይል ጭነት በማቃለል የኃይል አቅርቦቱን ተደራሽ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
ዲስትሪክቱ ደንበኞች ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ተጠቅመው የፍጆታ ሂሳባቸውን እንዲከፍሉ ከማድረግ አኳያ ከባንኮች እና ከቴሌ ጋር በትብብር በመስራት አሁን ላይ 92 በመቶ የሚሆኑትን ደንበኞች ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ተጠቅመው መክፈል እንዲችሉ ተደርጓል፡፡
በቀጣይ በዲስትሪክቱ ያለውን የኃይል አቅርቦት በማሻሻል ተጨማሪ ደንበኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም የኃይል መቆራረጡን ለመቀነስ እንዲያስችል የዲስትሪቡሽን ኔትወርክ ማሻሻያ ጥናት እየተካሄደ ሲሆን የማሻሻያ ስራው ሲጠናቀቅ አካባቢው ጥራት ያለውና አስተማማኝ የሃይል አቅርቦት ሊኖር እንደሚችል የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት አስታውቋል።

አጀንዳ 2063፤ ምን አሳካ፣ ምን ቀረ?
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአፍሪካ ኅብረት 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር የአፍሪካውያን አንድነትና ብልጽግና መገለጫ የሆነውን አጀንዳ 2063ን ይፋ አድርጓል፡፡
አጀንዳ 2063 አፍሪካውያንን በመሠረተ ልማት የማስተሳሰር፣ የሥራ አጥ ቁጥርን የመቀነስ፣ አፍሪካውያን ተመሳሳይ መገበያያ ገንዘብ እንዲኖራቸው የማድረግ፣ የአፍሪካ ኅብረትን ማጠናከር፣ ነፃ የንግድ ቀጣናዎችን መመሥረት እና ሌሎች በርካታ ግቦችን የሰነቀ ነው፡፡
አጀንዳ 2063 ይፋ ከተደረገ ጀምሮ ምን ምን እቅዶች ተሳኩ፣ ቀሪ ሥራዎች ምንድን ናቸው፣ ከኢትዮጵያስ ምን ይጠበቃል?
የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የፖሊሲ ጉዳዮች አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ(ዶ/ር) እንደሚሉት አጀንዳ 2063 ለአፍሪካውያን እድገትና ይህ ካልሆነ ግን አፍሪውያን ያለሙትን ብልጽግና እውን የማድረግ ጥረታቸውን ለማሳካት ይከብዳቸዋል፤ ሕዝቦቻቸውንም ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ብሎም ከግጭት ለማላቀቅ አይችሉም። አንድነት የሚረዱ በርካታ ግቦችን የያዘ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120635

ዋቢ ሸበሌ ወንዝን በመጠቀም በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ቤርዓኖ ወረዳ እየተሠራ ያለውን የመስኖ ግብርና ሥራ ዛሬ ተመልክተናል። የግብርና ዘርፍ ስብራታችንን ለመጠገን የጀመርነው ጉዞ ውጤታማ ስለመሆኑ አካባቢው አንዱ ማሳያ ነው።
የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም
ዋቢ ሸበሌ ወንዝን በመጠቀም በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ቤርዓኖ ወረዳ እየተሠራ ያለውን የመስኖ ግብርና ሥራ ዛሬ ተመልክተናል። የግብርና ዘርፍ ስብራታችንን ለመጠገን የጀመርነው ጉዞ ውጤታማ ስለመሆኑ አካባቢው አንዱ ማሳያ ነው።
የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም
ኮሚሽኑ ነጻ የስልክ ቁጥር እና ድረ ገጽ አስተዋወቀ
************
(ኢ.አ.ድ)
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆንበትን ነጻ የስልክ ቁጥር እና ድረገጽ አስተዋወቀ።
ኮሚሽኑ ተደራሽነትን ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ስራ ማስጀመሪያና ማስተዋወቂያ ፕሮግራም አከናዉኗል።
በስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ የመጀመሪያ ምዕራፍ ስራዎችን አጠናቆ ከትግራይና ከአማራ ክልሎች ዉጭ የአጀንዳ መሠብሰብ ስራ ሊጀምር ነዉ።
የተሳታፊ ልየታ በተከናወነባቸዉ ወረዳዎች በሙሉ በክልል ደረጃ የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ እንደሚከናወን ገልጸዉ አገራችንን ለበርካታ አመታት አለመግባባት የፈጠሩ ለግጭት ምክንያት የሆኑ አጀንዳዎች ወደ ኮሚሽኑ መጥተዉ ታዛቢዎች ባሉበት ለዋናዉ ምክክር እንደሚመረጡ ጠቁመዋል።
ኮሚሽኑ በመገናኛ ብዙሀን በኩል ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለመሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዉ ለዚህም የሚዲያ ተቋማትን አመስግነዋል።
ህብረተሰቡ ስለ ኮሚሽኑ ማንኛዉንም መረጃ ሲፈልግ በ 8112 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ወይም http://ethiondc.org.et የኮሚሽኑን ድረ ገጽ በመመልከት መረጃ ማግኘት እንደሚችልም በመድረኩ ተገልጿል።
በመዓዛ ማሞ

#ዲፕሎማሲያችን_ለብሔራዊ_ጥቅማችን
"ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን" በሚል መሪ ሃሳብ የተከፈተው የዲፕሎማሲ አውደ ርዕይ በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ ይገኛል።
አውደ ርዕዩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።
በዛሬ ማለዳ መርሀ ግብር የኮከበ ጽባህ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሳይንስ ሙዚየም ተገኝተው አውደ ርዕዩን ጎብኝተዋል።
በሳሙኤል ወንድወሰን