ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመለከቱ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የፌዴራል መንግሥት ልዑክ ከትናንት ጀምሮ በክልሉ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ከክልሉ መንግሥት አመራሮች ጋር እየመከሩ ነው።
ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ የሚገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
እንደ አሚኮ ዘገባ፤ የአዲሱን የዓባይ ድልድይ የግንባታ ሂደት የተመለከቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው ብሔራዊ ባንክ እያስገነባው ያለውን ሕንጻም በቦታው ተገኝተው አስጀምረዋል።
በመጨረሻም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታን ተመልክተዋል።
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም

"ኢትዮጵያን ለማዳከም በተሠሩ ሴራዎች ከቀይ ባሕር እንድትገለል ተደርጋለች"
- የታሪክ ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል
*******
(ኢ.ፕ.ድ)
ለዘመናት የኢትዮጵያን ኃያልነትና መልማት የማይፈልጉ አካላት በሠሩት ሴራ ከቀይ ባሕር ተገልላ እንድትቆይ መደረጉን የታሪክ ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል ገለጹ፡፡
ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከጥንት ጀምሮ ሐበሻ በቀይ ባሕር ላይ በሚካሄዱ ንግዶችና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የበላይነት ነበራት፡፡ በአረብ ሀገራት የሚገኙ ጎሳዎች ግጭት ሲፈጥሩ እንኳን እየመጡ የሚዳኙት በሐበሻ ንጉሥ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ለዘመናት የኢትዮጵያን ኃያልነትና መልማት የማይፈልጉ አካላት በሠሩት ሴራ ለበርካታ ዓመታት ከቀይ ባሕር ሁለንተናዊ እቅስቃሴ ተገልላ እንድትቆ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ የነበራትን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኃያልነት የማዳከም ፍላጎት ....https://www.facebook.com/share/p/ibgaF3fiEQt2Gp2q/?mibextid=2JQ9oc

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በ100 ሚሊየን ብር በጅግጅጋ ያስገነባው የዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በ100 ሚሊየን ብር ወጪ በጅግጅጋ ከተማ ያስገነባው የዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት የዳቦ ፋብሪካዉ በሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድና በቀዳሚ እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።
ፋብሪካው በቀን 300 ሺህ ዳቦና 420 ኩንታል ዱቄት የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡
ዛሬ በጅግጅጋ የተመረቀው ፋብሪካ ስምንተኛው ሲሆን÷ በአዲስ አበባ ከተመረቀው ውጭ ሁሉም ተመሳሳይ የማምረት አቅም እንዳላቸውም ተጠቅሷል፡፡
በጽሕፈት ቤቱ አማካኝነት የሚገነቡት የዱቄትና የዳቦ ፋብሪካዎች በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወኑ ናቸው ተብሏል፡፡
ተጨማሪ ፋብሪካዎች በደሴ፣ ነቀምቴ፣ አሶሳና ሠመራ ከተሞች በግንባት ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን÷ የደሴው በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በተለያዩ ከተሞች 12 የዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካዎችን ለመገንባት እየሠራ ሲሆን በጅግጅጋ የተገነባውን ጨምሮ ስምንት ፋብሪካዎችን ወደ አገልግሎት መግባታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ዉሀ ፕሮጀክትን ጎበኙ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬዉ እለት በሶማሊ ክልል 2ኛዉን ዙር የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ዉሀ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና ከሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በዛሬዉ እለት 2ኛዉን ዙር የጅግጅጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ዉሀ ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴን መመልከታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ለታለመለት የነዳጅ ድጎማ 28 ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል
***
(ኢ.ፕ.ድ)
አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደጎም የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ለታለመለት የነዳጅ ድጎማ 28 ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴር መስራ ቤቱን የ2016በጀት ዓመት የስድስት ወራት አጠቃላይ እቅድ አፈጻጻሙን ያቀረቡት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ኡርጌሳ ባይሳ የድጎማ ስርዓቱ ተግባራዊ መደረግ መንግስት የነበረበትን 180 ሚሊዮን ብር በማቃለል ወደ117.5 ሚሊዮን ብር ማውረድ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የድጎማ ስርዓቱ ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ 199 ሺ333 ተሸከርካሪዎች የስርዓቱ ተጠቃሚ ሲሆኑ ባለፉት ስድስት ወራት ሁለት ሚሊዮን 19 ሺህ 455 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው.መረጃ ያሳያል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️
ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን የጂግጂጋ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካን አስመርቀናል። ይህ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው ፕሮጀክት በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት እየተሰሩ ካሉ ደሃ ተኮር ስራዎች አንዱ ሲሆን በመላው ሀገራችን እየተሰሩ ካሉ 12 መሰል ፋብሪካዎች ስምንተኛው ነው። ለዘላቂ ልማት በምናደርገው ስራ እና ህዝባችንን ለመደገፍ ባለን ጥረት የተገኘ አንድ ርምጃ ነው።