Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

ዛሬ ጠዋት ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረን ጎብኝተናል።

ከተማችንን ጽዱ፣ ውብና አረንጓዴ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የአረንጓዴ ልማት ስራ የህጻናት መጫዎቻዎችን፣ መናፈሻዎችን እንዲሁም የተለያዩ ለአካባቢው ነዋሪዎች ግልጋሎት የሚሰጡ ስራዎችን የሚያካትት፣ ከ200 ሺሕ ካሬ በላይ ሽፋን ያለው እና ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ ድረስ 9.5 ኪ ሜ የሚረዝም ሲሆን ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለህዝብ ክፍት እናደርጋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
"በመዲናዋ የቅርስ መስፈርት የማያሟሉ ቤቶችንና አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት የቀደመ ስያሜያቸው እንዲቀጥል ይደረጋል"
- የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን
****
(ኢ ፕ ድ)

በአዲስ አበባ የመልሶ ግንባታና ኮሪደር ልማት የቅርስ መስፈርት የማያሟሉ ቤቶችንና አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት የቀደመ ስያሜና አገልግሎታቸው እንዲቀጥል እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አሰታወቀ።

የሀገር ሃብትና ቅርሶችን የመጠበቅ የመንከባከብና የመጠገን ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጿል።

በመዲናዋ የኮሪደር ልማት ሥራ ቅርሶችና መሰረተ ልማቶችን የመንከባከብ፣ የመጠበቅና የማደስ ሥራ በማከናወን በነበሩበት እንዲቀጥሉ መደረጉን የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መግለፃቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት የኢትዮጵያን ሃብትና ቅርሶች በመጠበቅ፣ በመንከባከብና በመጠገን ለትውልድ እንዲተላለፉ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው።

የቅርስ ጥበቃና መስህቦችን የማስፋት ስራ በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች እየተከናወነ ሲሆን በአዲስ አበባም ቅርሶችን የመጠበቅ፣ የመንከባከብና የመጠገን ስራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በመዲናዋ የአራዳ፣ ጉለሌ፣ ቂርቆስ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የአዲስ አበባ ቀደምት የምስረታ አካል በመሆናቸው የኪነ-ሕንፃና መልክዓ ከተማነትን የሚያሳዩ መታሰቢያዎች መኖራቸውን አንስተዋል።

ከዚህ ቀደም በመዲናዋ የቅርስ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁሉ የተመዘገቡ መኖራቸውን አስታውሰው ዓለም አቀፍ የቅርስ ምዝገባ ተሞክሮን መነሻ በማድረግ በተዘጋጀ መመሪያ መሰረት በአዲስ መልክ የቅርስ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በፊት የተመዘገቡ በቅርስነት የሚቀጥሉ ሲኖሩ በመመሪያው መሰረት መስፈርቱን የማያሟሉ ደግሞ አይቀጥሉም ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም በአዲስ አበባ የመልሶ ግንባታና ኮሪደር ልማት መጠበቅ ያለባቸው ቅርሶች እንዲጠበቁ መደረጉን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል።

በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች ከማህበራዊ ትውስታ፣ ዘመናዊነትና መዝናኛነት ጋር በተገናኘ የቆዩ ቤቶች ሁሉ ቅርስ ሊሆኑ አይችሉም ብለዋል።

ከዚህ ቀደም መርካቶ የቃኘው ሻለቃ ሆቴል፣ ቤላ የነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ ቤትና ፒያሳ የአድዋ ሆቴል የቅርስነት መስፈርት ሳያሟሉ ተመዝግበው እንደነበርም አስታውሰዋል።

በመሆኑም በመልሶ ግንባታና ኮሪደር ልማት ቅርሶች ተለይተው በቅርስ ምዝገባ መስፈርት ተመዝግበው እንዲጠበቁ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በየትኛውም ዓለም ልማትና ቅርስ ጥበቃ ሚዛኑን ጠብቆ እንደሚጓዝ ጠቁመው ቅርስ ጥበቃና ልማትን ማጣጣም ግዴታ ነው ሲሉም ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አስረድተዋል።

በመሆኑም የቅርስ ጥበቃና የልማት ስራዎች ተመጋግበው እንዲሄዱ በማድረግ የቅርስ መስፈርት የማያሟሉ ቤቶችንና አካባቢዎችን በመልሶ ልማት የቀደመ ስያሜና አገልግሎታቸው እንዲቀጥል ይደረጋል።

በኮሪደር ልማት ሥራው ቅርሶችና መሰረተ ልማቶችን የመንከባከብ፣ የመጠበቅና የማደስ ሥራ በማከናወን በነበሩበት እንዲቀጥሉ መደረጉን ከንቲባዋ መናገራቸው ይታወሳል።

መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያን ጎበኙ
******
(ኢ ፕ ድ)

በቅርቡ የኢትዮ ቴሌኮም የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቦርዱ አባላት ጋር በኩባንያው የተለያዩ የቦታዎች ላይ ጉብኝት አድርገዋል።

ጉብኝታቸውም በአድዋ የድል መታሰቢያ በሚገኘው የኩባንያው ኤክስፒሪየንስ ማዕከል በመጀመር በፕሪሚየም አገልግሎት ማዕከል፣ ሞጁላር ዳታ ሴንተር እና የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የኮኔክቲቪቲ ተደራሽነትና ጥራት ከማሻሻል ባሻገር የዲጂታል ሶሉሽኖችንና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ የህዝቡን ህይወት ለማቅለል በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ በጉብኝቱ ተገልጿል፡፡

በቴሌኮም እና በዲጂታል መሠረተ ልማት አቅም የተፈጠረውን አስቻይ ሁኔታ በመጠቀም የመንግስት ተቋማት አሰራሮቻቸውን በማዘመን ፈጣን፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት ማቅረብ እንዲችሉ የተገነቡ የዲጂታል አቅሞችን እንዲያውቁትና እንዲጠቀሙበት ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ዕውን ለማድረግ እያደረገ ያለውን ጥረት እና አስተዋጽኦ በማድነቅ ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቦርዱ ተገቢውን ድጋፍ እና አመራር እንደሚሰጥ መገለፁን ከኢትዮ ቴሌኮም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

በአዲስ አበባ የተጀመረው የልማት ኮሪደር አላማና አሁን ያለበት ደረጃ ለተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮቹ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለቀጣይ ትውልድ ቋሚ ቅርስ በሚሆን መልኩ መገንባቱ እንዳስደሰታቸው በጉብኝቱ ገልጸዋል።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ የጋራ ታሪካችንን በልኩ ሰንዶ የያዘ፣ አንድነታችንን የሚያጸና ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንና የልማት ኮሪደር አላማ ከተማዋን ማስዋብ መሆኑን መረዳታቸውን ተናግረዋል።

ከልማት ተነሺዎች የሚነሳ ቅሬታ ከፍተኛ አመራሩ አዳምጦ መመለሱን አሁንም አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ገዢው ፓርቲ የሰራቸውን የልማት ስራዎች በማየት እውነታውን መመስከር በፖለቲካ ስርዓታችን ውስጥ አዲስ ባህል በመሆኑ ይህ አዲስ አስተሳሰብና ተግባር ሊዳብር መግለፃቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓም
ገንዘብ ተመላሽ ማድረጊያ ጊዜ ለመጨረሻ ሶስት ቀናት ተራዘመ
****
(ኢ ፕ ድ)
የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች ገንዘቡን ተላሽ የማድረጊ ጊዜ ከሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተጨማሪ ሶስት ተከታታይ ቀናት መራዘሙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰታወቀ።

ባንኩ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች ገንዘቡን በአካል ቀርበው ወይም ዲጂታል የክፍያ ዘዴን በመጠቀም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ተመላሽ እንዲያደርጉ ለ2ኛ ጊዜ ዕድል መሰጠቱ ይታወሳል።

በተደረገው ጥሪ መሰረትም፤

👉 ያለአግባብ ከተወሰደው ገንዘብ ውስጥ ከባለፈው ሳምንት ተጨማሪ 117 ሚሊዮን 612 ሺህ ብር በመሰብሰብ የተከፈለ አጠቃላይ ገንዘብ 86 በመቶ ደርሷል፣

👉 ያልተመለሰ ገንዘብ ወደ ብር 112 ሚሊዮን 389 ሺህ 455 ዝቅ ብሏል፣

👉 ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው ክፍያ የጨረሱ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 10 ሺህ 857 ከፍ ብሏል፣

👉 የወሰዱትን ገንዘብ መመለስ ያልጀመሩ ግለሰቦች ቁጥር ወደ 222 ዝቅ ብሏል፣ ከነእዚህ ግለሰቦች የሚጠበቅ ገንዘብም ወደ አራት ሚሊየን ብር ነው፣

በሌላ በኩል የጊዜ ገደቡ መጠናቀቁን ተከትሎ አንድ አንድ ግለሰቦች ወደ ተለያዩ ተቋማት ያስተላለፉትን ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ እክል የገጠማቸው መሆኑን በመግለጽ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የወሰዱትን ገንዘብ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ወደ ከፈቱት የዲጂታል ሒሳቦች አስተላልፈው ወደ ባንክ ለመመለስ የተቸገሩ ግለሰቦች ወደ ማንኛውም ቅርንጫፍ ቀርበው ዝርዝር ሁኔታውን እንዲያሳውቁ ለማስቻል ቀኑ ተራዝሟል።

በመሆኑም ከሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተጨማሪ ሶስት ተከታታይ ቀናት ስለተራዘመ በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፎች በመቅረብ ወይም የዲጂታል የክፍያ ዘዴዎችን በመጠቀም ገንዘቡን ተመላሽ  እንታደርጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጨረሻ ጥሪ አቅርቧል።

መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ዓባይ ግድብ- የጋራ ጥረት ፤ የጋራ ድል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን እንዳትጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎች ቢኖሩም በታሪክ የሚወሳና የትውልድ አሻራ የሆነውን የዓባይ ግድብን በልጆቿ ብርቱ ጥረት ወደ ማጠናቀቂያው አድርሳለች።

ጀግኖቿ ዓድዋ ላይ እንደፈጸሙት ጀብዱ የዛሬው ትውልድ ደግሞ በዓባይ ግድብ ድሉን በመድገሙ ብዙዎች ዓባይን “ዳግማዊ ዓድዋ” ሲሉ ይደመጣሉ።

“የሁለት ውሃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ” የተሰኘው ሰነድ እንደሚያመላክተው፤ በዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ 11 ሀገራት ይገኛሉ። እነዚህ ሀገራት በተፋሰሱ ውስጥ በተለያየ የኃይል መጠንና የውሃ አጠቃቀም ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በዓባይ ተፋሰስ ውስጥ ከሚገኙት ወንዞች መካከል ኢትዮጵያ በዓባይ፣ በተከዜ (አትባራ) እና ባሮ (አኮቦ) ወንዞች አማካኝነት ከፍተኛውን የውሃ አቅርቦት ታበረክታለች።

በሌላ በኩል በተፋሰሱ የውሃ አቅርቦት ላይ ምንም አስተዋጽኦ የሌላት ግብጽ ውሃውን በመጠቀም ረገድ ረጅም ርቀት ሄዳለች። ግብጽ ላለፉት በርካታ ምዕተ ዓመታት ወንዙን በበላይነት ለመቆጣጠር የተለያዩ ስልቶችን....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=124660
“አዲሱ ትርክት ብዝሃነትን ያቀፈና አብሮነትን መሠረት ያደረገ መሆን አለበት”
– አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የሰላም ሚኒስትር
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
አዲሱ ትርክት ብዝሃነትን ያቀፈ አብሮነትን መሠረት ያደረገ መሆን አለበት ሲሉ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ገለጹ።

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እንደገለጹት፤ አዲሱ ትርክታችን ብዝሃነትን ያቀፈ ወንድማማችነትንና አብሮነትን መሠረት ያደረገ መሆን አለበት።

ባለፉት ጊዜያቶች በሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ የተጠቀምንባቸው ትርክቶች የፈጠሩት ችግር አለ ያሉት ሚኒስትሩ፤ በተለይም አንድነትን ማዕከል ያደረጉ ልዩነትን የማይቀበሉና ልዩነትን ማዕከል ያደረጉ የፖለቲካ ትርክቶች ነበሩ ብለዋል።

ትርክቶቹ ልዩነትን ተቀብሎ በማስተዳደር በኩል ችግር እንደነበረባቸው ጠቅሰው፤ በልዩነቶች ላይ ብቻ ያጠነጠነና ዜጎች በጥላቻ እንዲተያዩ ያደረገ ትርክት ነግሶ እንደነበር ገልጸዋል።

የበፊቶቹ ትርክቶች ያስከተሉትን ጉዳት በአግባቡ ያየ፣...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=124674
የክልል የፍትሕ ተቋማት የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ በቂ ትብብር አያደርጉም
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የክልል የፍትሕ ተቋማት ችግር የተገኘባቸውን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያስችል በቂ ትብብር እንደማያደርጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የይግባኝና የውሳኔ ማስፈጸም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ደነቀ ሻንቆ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ተቋሙ በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት ከተለያዩ አካላት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ተቀብሎ ምርመራ ያካሂዳል።

አቤቱታ የቀረበባቸው ተቋማት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተደጋጋሚ ውትወታና ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ያሉት አቶ ደነቀ፤ ይህ ሳይሳካ ሲቀር ግን ተቋሙ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ጉዳዩ የሚመለከተው ግለሰብ በሕግ ተጠያቂ የሚሆንበት፣ በሚዲያ የሚጋለጥበትና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በልዩ ሪፖርት የሚቀርብበት አግባ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=124690
የንግድ ባንክ የሲስተም ችግርና የሕግ አግባቡ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዕለተ ዓርብ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ላይ ባጋጠመው የሲስተም ማሻሻያ ክፍተት ምክንያት የባንኩ ደንበኞች ከገንዘብ መስጫ ማሽኖች እንዲሁም ከሞባይል ባንኪንግ ከ801 ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ያላግባብ መውሰዳቸውን ባንኩ አስታውቋል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በሰጡት መግለጫ፤ በእለቱ ከተፈጠረው የሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ ባንኩ ሊያጣው ከነበረው 801 ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር 623 ሚሊዮኑን ማስመለስ መቻሉን ሰሞኑን አስታውቀዋል። ባንኩ በሕገወጥ መንገድ ዘጠኝ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር ወስደው የጠፉ የ567 ሰዎችንም ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ለመሆኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያጋጠመው ችግር ከሕግ አንጻር እንዴት ይታያል? ስንል የሕግ ባለሙያ የሆኑትን አቶ ቸርነት ወርዶፋን ጠይቀናል።

አቶ ቸርነት ወርዶፋ እንደሚገልጹት፤ ከባንኩ በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዱት ሰዎች የባንኩ ደንበኛና የሂሳብ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=124703
ጠንካራ መገናኛ ብዙኃንን ለመገንባትና የባለሙያዎችን ብቃት ለማሳደግ ሰፊ ጥረት ያስፈልጋል
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
ጠንካራ መገናኛ ብዙኃንን ምህዳር ለመፍጠርና የባለሙያዎችን ብቃት ለማጎልበት መንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት ሰፊ ጥረት ሊያደርጉ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።

የምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ታምራት ኃይሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ነፃና ጠንካራ መገናኛ ብዙኃን ለመፍጠር በመገናኛ ብዙኃን መካከል ያለው ትብብር እና የጋዜጠኞችን አቅም ማሳደግ ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን ይገባል።

እንደ አቶ ታምራት ገለጻ፤ ምክር ቤቱ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፀጥታ ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስተካከል የግጭት አፈታት ዘገባና የሰላም ጋዜጠኝነትን እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በርከት ላሉ ጋዜጠኞች በየጊዜው ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል ።

መንግሥትና የተለያዩ አካላት የመገናኛ ብዙኃን አቅም በማሳደግ ረገድ በተጠናከረ ሁኔታ ሊሰሩ እንደሚገባ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=124717