Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“የዓባይ ግድብ የኢትዮጵያን መልማት የማይፈልጉ አካላትን ሃሳብ የቀለበሰ ነው” – ኢንጂነር ጥላሁን ኤርዱኖ (ዶ/ር)
***********************
(ኢ ፕ ድ)
የዓባይ ግድብ የኢትዮጵያን መልማት የማይፈልጉ አካላትን ሃሳብ በመቀልበሰ ልማትን ማረጋገጥ የቻለ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው ሲሉ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህር ጥላሁን ኤርዱኖ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሰርቬይንግና ካርታ ኢንጂነሪንግ መምህር ጥላሁን ኤርዱኖ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዓባይ ግድብ የኢትዮጵያን መልማት የማይፈልጉ አካላት ሃሳብ የቀለበሰ ነው፡፡

ግድቡ ኢትዮጵያ በሰላም መቀጠል ከቻለችና አንድነቷ ከጠነከረ ልማት ታስባለች በሚል የተዛባ አመለካከት የኢትዮጵያን ልማት ሲያደናቅፉ የቆዩ ሀገራትን እሳቤ ማምከን ችሏል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የነበሩበትን በርካታ ጫናዎች እንዲሁም ፈተና ተቋቁሞ ለዚህ ደረጃ መድረሱ በተባበበረ ክንድ የትኛውንም አይነት ዓላማ ከግብ ማድረስ እንደሚቻል በተግባር የተገለጸበት ነው ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ለወደፊት ለሚቀረጹ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መሳካት መንገድ የሚከፍት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ዶክተር ጥላሁን አክለውም፤ የግድቡ እውን መሆን ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ጎን ለጎን....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124783
“የግድቡ መጠናቀቅ በኃይል እጥረት ወደኋላ የቀሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲያንሰራሩ ያደርጋል”
– አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የዓባይ ግድብ መጠናቀቅ በኃይል አቅርቦት ላይ ያለውን ችግር በመፍታት ወደኋላ የቀሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲያንሰራሩና እንዲጠናከሩ እንደሚያደርግ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀⵆ የኃይል አቅርቦት ውስንነት ከፍተኛ የሰው ኃይል መያዝ የሚችሉ ኢንዱስትሪዎች የሥራ ዕድል እንዳይፈጥሩ ሲያደርግ መቆየቱም ተገልጿል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ከኢፕድ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ አምራች ኢንዱስትሪው ተግዳሮቶቹ የተለያዩ ቢሆኑም በቂ የሆነ የኃይል አቅርቦት አለመኖር፣ የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል፡፡
እነዚህ ችግሮች ደግሞ ኢንዱስትሪዎቹ በበቂ ሁኔታ ማምረት እንዳይችሉ አድርጓቸዋል፤ አሁን ላይ የግድቡ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረስ ግን ችግሮቹን ለመፍታት ትልቅ አቅም ነው፡፡

በቂና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ቢያገኙ የማስፋፋት ሥራ በመሥራት ምርታቸውን በእጥፍ ለማሳደግ የተዘጋጁ አምራች ኢንዱስትሪዎች አሉ ያሉት አቶ ታረቀኝ፤ የኃይል አቅርቦት ውስንነት ከፍተኛ የሰው ኃይል መያዝ የሚችሉ ኢንዱስትሪዎች የሥራ ዕድል እንዳይፈጥሩ ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል፡፡

የዓባይ ግድብ መጠናቀቅ በኃይል አቅርቦት ላይ ያለውን ችግር ፈትቶ ወደኋላ የቀሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124805
“ሕብረታችን በሌሎችም የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች የኃይል ማመንጫ ግንባታዎች ላይ መደገም አለበት”
– አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በዓባይ ግድብ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሳየውን ሕብረት በሌሎችም የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች የኃይል ማመንጫ ግንባታዎች ላይ መድገም እንዳለበት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ከኢፕድ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የዓባይ ግድብ በሕዝብ ቁጭት ተገንብቶ አፈፃፀሙም 95 በመቶ ደርሷል፡፡

በቀጣይም በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ በተመሳሳይ መልኩ ሕብረቱን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል፡፡

ለጊዜው ግድቡ ሙሉ ለሙሉ እስኪያልቅ እና መቶ በመቶ ኃይል ማመንጨት እስከሚጀምር፤ የሕዝቡ ድጋፍ በተጀመረበት መንፈስ መቀጠል አለበት ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ግድቡን ማነፅ ቢያልቅም፤ ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች መኖራቸውን አስታውሰዋል፡፡

አካባቢውን በአረንጓዴ ልማት መሸፈን እና የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ጊዜ የሚሠጠው.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124803
ለዓባይ የተፈጸመ የፅዳት ሠራተኞቹ ገድል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በዓለም ረጅሙ ወንዝ ነው። የመርዘሙን ያህል ለዘመናት ሳይከበር ኖሯል። በልኩ የተሰፋ ስራ አልነበረውም። ዓባይ የማበል ምልክት ተደርጎ ለዘመናት ተተርኮበታል።

ማደሪያ የሌለው ግንድ ይዞ ዟሪም ተብሎ ያውቃል። በመኖር ዘመኑ ከሀገሩ በላይ ለጎረቤት ሀገራት አድልቷል። በርሀብና ችግር የተጠቁ ወገኖቹን ትቶ እነሱን አጉርሷል።

እነዚያን ሀገራት የጠቀመውን ያህል ለሀገሩ ሊሆን አልተቻለውም ነበር።

ከመኖር ብዛት ሳይሆን ከስራው ጥልቀት ታይቶ አንቱ የሚባልበት ጊዜ ደረሰ። ከዘመናት ሳይጠቅሙ ኑሮ በኋላ ግን መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ቀን ወጣለት። ግንባታው ከተጀመረም 13 መጋቢቶች አልፈው ዘንድሮ 13ኛው ላይ እንገኛለን።

ጅማሮው ለኢትዮጵያውያኑ የክፍለዘመኑ ትልቁ ዜና ነበር። አሁን ትልቋን ኢትዮጵያን ያለ ዓባይ ማሰብ የማይቻልበት ዘመን ተወልዷል። ብዙ ህልሞች በእርሱ ትራስነት ታልመዋል።

ጭስ ያሞጨሞጨው አይናቸው በግድቡ እንደሚታከም ተስፋ የጣሉ እናቶች ብዙ ናቸው። እንደ ኢትዮጵያ ላሉቱ ሀገራት እንደ ዓባይ ያለ ትልቅ ተቋም አንድምታው ሰፊ ነው። የዓባይ ግድብ በራስ አቅም ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124791
የዓባይ ግድብ ግንባታ መታሰቢያ ቴምብር ይፋ ሆነ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የዓባይ ግድብ 13ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀዉን የመታሰቢያ ቴምብር በዓሉን በማስመልከት በተዘጋጀዉ የፓናል ዉይይት መድረክ ላይ ይፋ አደረገ።

የአባይ ግድብ የመታሰቢያ ቴምብሩን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ እና የአባይ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) በጋራ መርቀዋል።

የመታሰቢያ ቴምብሩ ከዛሬ ጀምሮ ለ192 የአለም አገራት እንደሚሠራጭ ተገልጿል።

በመዓዛ ማሞ
#የዓባይ_ግድብ_ዕውነታዎች ‼️

ከ13 ዓመት በፊት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ነበር የተጀመረው። የኢትዮጵያዊያን አንድነትና የይቻላል መንፈስ የታየበት ሀገራዊ ፕሮጀክትም ነው።

ለመጪው ትውልድም የይቻላል መንፈስን ሲያንጸባርቅ የሚኖር ፕሮጀክት ነው።

የዓባይ ግድብ በአሁኑ ወቅት በሁለት ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት ኃይ በማመንጨት ላይ ነው፣

👉ግድቡ ሲጠናቀቅ 78 ደሴቶች ይፈጠራሉ፤

👉በግድቡ ሐይቅ በዓመት ከ10 ሺህ ቶን በላይ አሳ ማምረት የሚያስችል ነው፣

👉የዓባይ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይልን በማመንጨት ከአፍሪካ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፣

👉ለቀጠናው ህዝቦች ትስስር፣ ለገጽታ ግንባታ፣ ለአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ ቁልፍ ሚና እንዳለው፣

👉ለግድቡ እስካሁን ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ ከህዝቡ ተሰብስቧል፣

👉በዘንድሮው ስምንት ወራት ብቻ 931 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል፣

👉የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ሽፋኑን 75 በመቶ ለማዳረስ ያግዛል፣

የዓባይ ግድ ሀገራዊ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት 13ኛ ዓመት በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል

ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124790
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ጸደቀ
******
(ኢ ፕ ድ)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሶስተኛ አመት የስራ ዘመን 19ኛ መደበኛ ስብሰባ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅን በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

አዋጁ ሁለት ዓመት የውል ዘመን ያለው፣ በሁሉም የቤት መኖሪያዎች ላይ የሚተገበርና የዋጋ ተመኑ በመንግስት የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ አለመረጋጋትና ፍትሃዊነት የሌለው የዋጋ ጭማሪን በመቆጣጠር በቤት አቅርቦት ላይ የሚስተዋለውን ችግር በማረጋጋት መፍትሄ የሚሰጥ ስርዓት ዘርግቷል።

አዋጁ የአከራይና ተከራይ መብትን በሚዛናዊነት የሚያገለግል፣ ህጋዊነትን የሚያጸና፣ ግልጸኝነትን የሚያረጋግጥ እና ስርአቱን ከደላሎች ተጽእኖ የሚያላቅቅ መሆኑም ተጠቁሟል።

በዘላለም ግዛው

መጋቢት 24 2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ሥራ ኮሌጅ የምጣኔ ሀብት መምህር ብርሃኑ ደኑ (ዶ/ር) የአባይ ግድብ መጠናቀቅ ለአገሪቱ የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አብራርተዋል‼️

👉 የዓባይ ግድብ የተጋረጡበትንም ፈተናዎች ተሻግሮ ወደ ማጠናቀቅ መቅረቡ ከምንም በላይ ትልቅ ስኬት ነው፣

👉 ብዙዎች ይህ ግድብ እውን እንዳይሆን በብዙ ጥረው የነበረ መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም፣

👉 በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የምናያቸው የበለጸጉ ሀገሮች ሁሉ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል የተደራጁ ናቸው፣

👉 በኢትዮጵያውያኑ ጥንካሬ የተገነባውና ሊጠናቀቅ ጫፍ ላይ የደረሰው ግድብ ሲጠናቀቅ ኢኮኖሚያዊ እድገቱ ወደፊት ለማስፈንጠር ሚናው የጎላ ነው፣

👉 ኢትዮጵያ ልታድግ የምትችልበትን፣ ምርታማነት የሚጨምርበትን፣ የሥራ እድል የሚከፈትበትንም ዕድል ይፈጥራል፣

👉 በአገልግሎት መስጫ፣ በኢንዱስትሪና በግብርናው ዘርፍ የኤሌክትሪክ ኃይል በከፍተኛ ደረጃ አስፈላጊ ነው፣

ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124870
አዋጁ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ ዜጎች እፎይታን የሚሰጥ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ መጽደቅ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ ዜጎች እፎይታ የሚሰጥ መሆኑ ተገለጸ።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የአዋጁን አላማ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ ማብራሪያ እንደተናገሩት፤ ከመኖሪያ ቤት ኪራይ ጋር የተያያዙ ችግሮች ዜጎችን ለከፋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየዳረጉ ሲሆን፤ ለኑሮ ውድነት መጨመርም አንዱ ምክንያት እየሆነ ነው።

እስካሁን ባለው አካሄድ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋና የመቀመጫ ጊዜ የሚወሰነው በደላላ እና በአከራይ ተጽእኖ ብቻ ነውያሉት ሚኒስትሯ፤ በዚህ ረገድ መንግሥትም ጣልቃ በመግባት ፍትሐዊ አሰራር ለመዘርጋት እድሉ አልነበረውም ብለዋል።

ይህም በተለይ በከተሞች አካባቢ የመንግሥት ሠራተኛውና ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ በከፍተኛ ችግርና መሳቀቅ ውስጥ እንዲኖር አስገድዶታል ሲሉም አስረድተዋል።

ሚኒስትሯ እንደገለጹት፤ አዋጁ የተከራይና አከራይ ግንኙነትን በሕጋዊ መንገድ ለመምራት ብሎም ግልጽነት የሰፈነበት አሰራር በመዘርጋት ዜጎች ተሳቀው የማይኖሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል ነው።

አዋጁም የበርካታ ሀገራት ተሞክሮን በመውሰድ ዋጋ የሚጨምረው ማነው፤ አንዴትስ መጨመር አለበት፤ የሚለውን ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124928
ግብጽ የዓባይ ግድብ መጠናቀቅ ለተፋሰሱ ሀገራት ታሪክ የሚቀይር ይሆናል የሚል ፍርሃት አላት
**************
(ኢ ፕ ድ)
ግብጽ የዓባይ ግድብ መጠናቀቅ ለተፋሰሱ ሀገራት ታሪክ የሚቀይር ይሆናል የሚል ፍርሃት አላት ሲሉ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር መኮንን አያና አስታወቁ።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር መኮንን አያና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ግብጾች የሚያስፈራቸው ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የግድብ ግንባታ ካጠናቀቀች ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን መንገድ ይከተላሉ፤ የግብጽ የበላይነትም አይኖርም የሚል ነው።

በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ በዓድዋ ላይ የነበረው ስኬት በዓባይ ግድብ ከተደገመ ለናይል ተፋሰስ ሀገራት ታሪክ የሚቀይር ይሆናል የሚል ትልቅ ፍርሃት አለባቸው።

የዓባይ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ከተቀመጠ 13 ዓመት ሆኖታል ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ ግድቡ ብዙ ፈተናዎችን አልፏል። ይሁን እንጂ ባለፉት 13 ዓመታት ውስጥ የመጣበት ሂደት ውጤታማና በስኬት የተሞላ ነው። ካሉ ፈተናዎች አንጻር ለመጠናቀቅ መቃረቡ አስደሳች ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዓድዋ ድል አፍሪካን አንድ እንዳደረገችና ከጭቆና ነጻ እንዳወጣች ሁሉ በግድብ ግንባታ ውጤታማ በመሆን...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124935
በአማራ ክልል በሰባት ወራት ለዓባይ ግድብ ከ 32 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በአማራ ክልል ለዓባይ ግድብ ግንባታ በሰባት ወር ውስጥ ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የክልሉ የህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተናኘ አበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ንግድ ባንክ በተገኘው መረጃ ከክልሉ ነዋሪዎች በሰባት ወር ውስጥ ከ32 ሚሊዮን 329ሺ ብር በላይ በቦንድ ግዢ ተሰብስቧል።

ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ በተያዘው በጀት ዓመት ከቀድሞ ዓመታት በተለየ መልኩ ዕቅዱን ከፍ በማድረግ 70 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ አቅዶ እንደነበር አስታውሰው፤ ሆኖም በክልሉ በነበረው ችግር የታሰበውን ያህል መስራት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

ግድቡ የተጀመረበትን 13ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም 40 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ልዩ እቅድ ታቅዶ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ያሉት አቶ ተናኜ፣ ከክልሉ ወጣቶች እና ሴቶች አደረጃጀቶች ጋር በጋራ በመሆን እቅዱን....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124937
በክልሉ ዘንድሮ 889 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
በክልሉ በበጀት ዓመቱ 889 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ገለጹ። ክልሉ በሌማት ትሩፋትም አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን አስታውቋል።

የቢሮ ኃላፊው አቶ ማስረሻ በላቸው በተለይ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በክልሉ ባሉ ሶስት ሺ 886 የችግኝ ጣቢያዎች አማካኝነት ሀገር በቀልና የውጭ ዝርያ ያላቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ያካተተ የዘር ዝግጅት ተደርጓል።

ኃላፊው እንዳሉት ችግኞቹ የሚተከሉት በሚያዝያና ሐምሌ ወር ላይ ጀምሮ ነው።

አሁን ባለው ሁኔታ ዝግጅቱ በቅርቡ በግምገማ ወደ 26 ሚሊዮን ችግኞች ዝግጅት ተደርጓል። ይህም በየቀኑ ይጨምራል።

አሁን ላይ 40 ሚሊዮን የደንና ጥምር ደን 71 ሚሊዮን የቡና ችግኞች ለሚያዝያና ሐምሌ ተከላ ዝግጅት ተደርጓል። የተለያዩ የደን ዝርያ ያላቸው ሁለት መቶ 60 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ችግኞች በግብርናው ዘርፍ ይተከላሉ።

በሌላ በኩል የሌማት ትሩፋት ስራው ከክልል ምስረታው ጋር አብሮ መጀመሩን የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ እንደ ሀገር የተያዘው የሌማት ትሩፋት በወተት፣ በዶሮ ስጋ፣በማርና በአሳ ላይ እየተሰራ.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124934
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሰላሳ ዓመታት የተከናወኑ አበይት ሥራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ ተከፈተ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሰላሳ ዓመታት የተከናወኑ ሥራዎችን የሚያስቃኝ ዓውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ተከፍቷል።

አውደርዕዩ "የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጉዞ" በሚል እስከ መጪው ዓርብ ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።

በአውደ ርዕዩ በክልል ደረጃ የሚገኙ ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የሽገር ከተማ አስተዳደር ተሳትፈዋል። አውደ ርዕዩ በክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ የተዘጋጀ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዓርብ ይቆያል።

በሳሙኤል ወንደሰን
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም