Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በክልሉ በስምንት ወራት ከአንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል
******************
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ስምንት ወራት ለአንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠር መቻሉን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቶሎሳ አጀማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በተያዘው በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ ለአንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለአንድ ነጥብ 79 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል በመፍጠር የእቅዱን 98 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡

በዓመቱ ለሦስት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ አስፈላጊ ዝግጅት ማድረጉን ጠቅሰው፤ ለዚህም ቢሮው በከተማና በገጠር የሥራ ፈጠራን የሚያበረታቱ ዕቅዶችን አቅዶ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡

ቢሮው ለሥራ አጥ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጦ እየሠራ እንደሚገኝ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ለዚህም ከሰርተፍኬት ባሻገር ጥራት ያለውና ውጤታማ ስልጠና

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124989
የግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ
***************
(ኢ ፕ ድ)
የህዝበ ተወካዮች ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመን 20ኛ መደበኛ ስብሰባ የግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ በዛሬው አጽድቋል፡፡

አዋጁ የግል ዳታ ጥበቃን በተመለከተ ዝርዝር ድንጋጌዎችን የሚያስቀምጥና የግል ዳታ ጥበቃ ተቆጣጣሪ ተቋምን የሚሰይም በመሆኑ ጠንካራ የግል ዳታ ጥበቃ ስርዓት እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የግል ዳታ በሚሰበሰብበትና በሚቀናበርበት ወቅት ጥሰት እንዳይፈጠር ለመቆጣጠርና የወንጀሉ ፈጻሚዎችን አስተማሪ በሆነ አግባብ መቅጣት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅም ነው ተብሏል ፡፡

ከዳታ ማቀናበር ስራዎች ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመቀነስና በኢትዮጵያ የግል ዳታ ጥበቃ ሰርዓት ዓለምአቀፋዊ ደረጃዎችንም በጠበቀ መልኩ ለመገንባትም ዋሳኝ መሆኑም ተነስቷል፡፡

በዳግማዊት አበበ
መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
የዓባይ ግድብ በዓለም ካሉት ውብ የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ ይሆናል
********************
(ኢ ፕ ድ)
የዓባይ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ ቦታው በዓለም ላይ ካሉት ውብ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ይሆናል ሲሉ ከፍተኛ የቱሪዝም ባለሙያው ዶክተር አያሌው ሲሳይ ገለጹ።

የቱሪዝም ባለሙያው ዶክተር አያሌው ሲሳይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የዓባይ ግድብ የሚያርፍበት ቦታ የውሃውን ይዞታ ጨምሮ አንድ ሺህ 740 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ይሸፍናል።

ግድቡ የሚይዘው 74 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ ወደ ኋላ 246 ኪሎ ሜትር ይረዝማል።

በዚህም እያንዳንዳቸው ከአምስት ሔክታር በላይ ስፋት ያላቸው 70 ደሴቶች ይፈጠራሉ፡፡
ይህም የዓባይ ግድብ ሲጠናቀቅ አካባቢው በዓለም ካሉት ውብ የቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ ያደርገዋል፡፡

ትልቁ ደሴት ሁለት ሺህ 800 ሔክታር ስፋት እንደሚኖረው መረጃዎች ያመለክታሉ ያሉት ዶክተር አያሌው፤ የዓባይ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ ቦታው በዓለም ላይ ካሉት ውብ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ውስጥ አንዱ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ዓባይ ተራ ወንዝ ብቻ ሳይሆን የስልጣኔ እና የባህል ምልክት ነው። ይህም ግድቡን በቀላሉ ለዓለም ሕዝብ ማስተዋወቅ ያስችላል ያሉት ዶክተር አያሌው፤ ይህም ቱሪስቶች ከዓባይ ወንዝ ጋር የተያያዘውን ውበት እና የበለፀገ ባህልና ታሪክን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125001
"ወጣቶች ከትንሽ በመነሳት ለሀገር የሚተርፍ የፈጠራ ሥራ ማከናወን ይገባቸዋል"-ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
******
(ኢ ፕ ድ)
ወጣቶች ትልቅ አስብው ከትንሽ በመነሳት ለሀገር የሚተርፍ የፈጠራ ሥራ ማከናወን ይገባቸዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ስታርታፕ ብሔራዊ ሁነት በዓድዋ መታሰቢያ ተከናውኗል።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወጣቶች ውስጣቸው ያለውን ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳብ ወደተግባር በማዋል ገቢ መፍጠር እንዳለባቸው አመላክተዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ 900 ስታርትአፕ መኖራቸውን ጠቁመው በጅማሮ ላይ ያለውን ዘርፍ በጋራ በማሳደግ ውጤታማ መሆን ይገባል ብለዋል።

የኢንተርኔት ዋጋ፣ የቢሮ ኪራይ፣ የኤሌክትሪ ዋጋው ከሌሎች ጋር ሲነጻጸር ለስታርትአፖች ውድ ቢሆንም በጋራ በመደጋገፍ ስኬታማ መሆን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በመድረኩ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሥራ ፈጣሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም

መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

“ስታርት አፕ ኢትዮጵያ” ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ የተመቸ ከባቢን በመፍጠር ችግር ፈቺ የስራ መስኮችን ለመክፈት ያለመ ነው። ወጣቶችን በፈጠራ ሃሳብ የተሞሉ የሀገራችን አንቀሳቃሽ ሞተሮች መሆናቸውን በመቀበል ሀሳባቸውን ወደ ተግባር የሚለውጡበት የዘርፉ ፖሊሲ ድጋፍም እጅግ አስፈላጊ ነው። ካሉት ወቅታዊ ተግዳሮቶች ባሻገር ያለፉት ስድስት አመታት ስራችን የተለያዩ ማነቆዎችን በመፍታት ሰፋፊ ዕድሎች ለማስገኘት መንገድ የተከፈተበት ነበር።

መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
መሠረታዊ ለውጥ የሚሻው የፖስፖርት አገልግሎት
*************
(ኢ ፕ ድ)
በቅጥር ግቢው ሰፊ መጋዘን መሳይ አዳራሽ አለ፡፡ በስማቸው ፊደል ተራ ተሰባስበው የስማቸውን መጠራት በጉጉት የሚጠባበቁ ደንበኞች በግቢውም በአዳራሹም በርካታ ናቸው፡፡

ለተሰብሳቢዎቹ ድምጻቸውን ጎላ ያደረጉ የአገልግሎቱ ሠራተኞችም በየተራ ስም ይጣራሉ፡፡

ጉዳያቸውን ያሳኩ ፓስፖርታቸውን ይዘው ፊታቸው ሲፈካ፤ ተራ ያልደረሳቸው ደግሞ እየተማረሩ ሲጠባበቁ ይታያሉ፡፡

አናት የሚበሳውን ፀሐይ ተቋቁመው ተራ የሚጠባበቁ አዛውንቶች፣ ሕፃናት የያዙ ወላጆች እና ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ሲጉላሉ የሚስተዋልበት ትዕይንት ጎተራ እና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኘው የኢምግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ግቢ ውስጥ ተመልክተናል፡፡

ጉዳይን ፈጽሞ መመለስ እንደልዩ ዕድል የሚቆጠርበት በዚህ ትዕይንት በዋና መሥሪያ ቤቱም ሆነ በቅርንጫፉ ግቢና ደጃፎቹ በርከት ያሉ ተገልጋዮች ምሬት ሲያሰሙ መስማት የተለመደ ነው፡፡

በርግጥ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ ሥርዓት ተዘርግቷል፤ የአሠራር ሥርዓቱም በመጠኑ መሻሻል ታይቶበታል፤ ይሁን እንጂ አሁንም ከሕዝብ ፍላጎት ጋር የአገልግሎት አሰጣጥን ማጣጣም፣ ሙሉ አሠራሩንም ማዘመን ፣ ታትሞ የደረሰ ፓስፖርት እንዳለውም ቅልጥፍ.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125054
አዋጁ ሃይማኖታዊ በዓላት አከባበርና የጋራ ድሎችን እውቅና ለመስጠት ያስችላል
******************
(ኢ ፕ ድ)
የሜዳይ፣ ኒሻን ሽልማት አዋጅ የሃይማኖት እና የድል በዓላትን አከባበር እንዲሁም በጋራ የተሳኩ ድሎችን እውቅና መስጠትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የሕግ አማካሪ አለምአንተ አግደው ገለጹ፡፡

የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሜዳይ፣ ኒሻን ሽልማት ረቂቅ አዋጅ ላይ የአስረጂ መድረክ አካሂዷል፡፡

በአስረጂ መድረኩ ላይ የተገኙት የሕግ አማካሪው አለምአንተ፤ የሃይማኖት እና የድል በዓላትን አከባበር፣ የማህበራዊ እሴቶችን እና በጋራ ያሳካናቸውን ድሎች እውቅና መስጠትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በተቋም ግንባታ እና በሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ገልፀው፣ ለሀገር አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰዎችን በመሸለም ሌሎች የሚበረታቱበት ሥርዓት የመፍጠር እሳቤ እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡

ትውልድን ለማነሳሳት እና አርአያ በመሆን ሌሎች እንዲነሳሱ በማድረግም ፋይዳው የጎላ መሆኑን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125065
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ብሔራዊ ሁነት” ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች ‼️

👉ስታርት አፕ በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ፣ ገቢ የሚያመነጭ እንዲሁም ለአንድ ጉዳይ መፍትሔ ያለው ፈጠራ ነው፣

👉ስታርት አፖችን መደገፍ ከቻልን የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ፣

👉 በዓለም ላይ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ያላቸው አንድ ሺህ 200 ስታርት አፖች አሉ፣

👉ከአምስት ዓመታት በፊት በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ 50 ስታርት አፖች ነበሩ፤ አሁን ላይ ግን 900 ደርሰዋል፣

👉ወጣቶች አዲስ ፈጠራ ሲጀምሩ በቅድሚያ ሥራውን መውደድ፣ ሥራውን በራሱ መቻላቸውን ማረጋገጥ፣ ፈጠራው ተፈላጊና በገበያ ላይ ሊሸጥ የሚችል መሆኑን ማወቅ አለባቸው፣

👉ወጣቶች ትልቅ አስበው ከትንሽ በመነሳት ለሀገር የሚተርፍ የፈጠራ ሥራ ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፣

👉 የስታርታፕ አውዱ ጅማሮ ላይ ቢሆንም ችግሮች ግን የሉበትም ማለት አይደለም፣

👉ከለውጡ በፊት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የፋይናንስ አገልግሎት የሚያከናውን ወንጀለኛ ሆኖ ይጠየቅ ነበር፣

👉አሁን ላይ ግን በርካታ ተቋማት በዘርፉ ተሰማርተው ገንዘብ እያንቀሳቀሱ ይገኛል፣

👉 መንግሥት ስታርት አፖችን መደገፍ ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘቡ የተለያዩ ማበረታቻዎችን እያደረገ ነው፣

ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125052
“ክልሎችን በአፈጻጸምና በውጤት ማቀራረብ ቀጣይ ተልዕኳችን ነው”
- አቶ አደም ፋራህ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ክልሎችንና ከተማ አስተዳደሮችን በግንዛቤ፣ በአፈጻጸምና በውጤት ማቀራረብ የቀጣይ ተልዕኳችን ነው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም ፋራህ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተካሄደው ድጋፋዊ የመስክ ምልከታ ሪፖርት ውይይት ላይ እንደገለጹት፤ የመስክ ምልከታው በቀጣይ ሊሚከናወኑ ተግባራት ግብዓት የተገኘበት፣ የአመራሩንና የማኅበረሰቡን ችግር የሚፈታ ነው፡፡

የመስክ ምልከታ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የአፈጻጸም ልዩነት እንዳለ የተለየ መሆኑን ገልጸው፤ በግንዛቤ፣ በአፈጻጸምና በውጤት የማቀራረብ ሥራ የቀጣይ ተልዕኮ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የፌዴራልና የክልል መንግሥታትን ቅንጅት ለማረጋገጥ እና በሁሉም አካባቢዎች የተቀራረበ አፈጻጸም እንዲኖር የተቀናጀ ሥራ እንደሚሰራ አመልክተው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከክልል አቻ ተቋማት ጋር እቅድ የማናበብ፣ አፈጻጸምን በጋራ የመገምገምና የተሻለ ተሞክሮን በመቀመር ልምድ እንዲለዋወጡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በመስክ ምልከታው የታዩትን ክፍተቶች ለመፍታት ጥረት መደረጉን ገልጸው፤ በቀጣይም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተገኘውን ግብዓት የእቅዳቸው አካል በማድረግ ተግባራዊ መፍትሄ የሚሰጡበትን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125053
ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር አንድ ነጥብ 72 ቢሊየን ዶላር የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈራረመች
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊየን ዶላር የፍይናንስ ድጋፍና የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የብድርና የድጋፍ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትንና እድገትን ለማምጣት ለታቀዱ ስድስት ፕሮጀክቶችን ለመተግበር እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ድጋፍና የብድር ስምምነቱ ለምግብ ዋስትና መርሐግብርን ለመደገፍ፤ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ለማጠናከር፤ በቆላማ አካባቢዎች ለሚገኙ አርብቶ አደርና አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ኑሮንና የአየር ንብረትን የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ፤ ለሀይል አቅርቦት ማሻሻያ፣ ለሁለተኛው የከተማ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እንደሚውል ተገልጿል።

መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም