Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

“ስታርት አፕ ኢትዮጵያ” ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ የተመቸ ከባቢን በመፍጠር ችግር ፈቺ የስራ መስኮችን ለመክፈት ያለመ ነው። ወጣቶችን በፈጠራ ሃሳብ የተሞሉ የሀገራችን አንቀሳቃሽ ሞተሮች መሆናቸውን በመቀበል ሀሳባቸውን ወደ ተግባር የሚለውጡበት የዘርፉ ፖሊሲ ድጋፍም እጅግ አስፈላጊ ነው። ካሉት ወቅታዊ ተግዳሮቶች ባሻገር ያለፉት ስድስት አመታት ስራችን የተለያዩ ማነቆዎችን በመፍታት ሰፋፊ ዕድሎች ለማስገኘት መንገድ የተከፈተበት ነበር።

መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
መሠረታዊ ለውጥ የሚሻው የፖስፖርት አገልግሎት
*************
(ኢ ፕ ድ)
በቅጥር ግቢው ሰፊ መጋዘን መሳይ አዳራሽ አለ፡፡ በስማቸው ፊደል ተራ ተሰባስበው የስማቸውን መጠራት በጉጉት የሚጠባበቁ ደንበኞች በግቢውም በአዳራሹም በርካታ ናቸው፡፡

ለተሰብሳቢዎቹ ድምጻቸውን ጎላ ያደረጉ የአገልግሎቱ ሠራተኞችም በየተራ ስም ይጣራሉ፡፡

ጉዳያቸውን ያሳኩ ፓስፖርታቸውን ይዘው ፊታቸው ሲፈካ፤ ተራ ያልደረሳቸው ደግሞ እየተማረሩ ሲጠባበቁ ይታያሉ፡፡

አናት የሚበሳውን ፀሐይ ተቋቁመው ተራ የሚጠባበቁ አዛውንቶች፣ ሕፃናት የያዙ ወላጆች እና ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ሲጉላሉ የሚስተዋልበት ትዕይንት ጎተራ እና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኘው የኢምግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ግቢ ውስጥ ተመልክተናል፡፡

ጉዳይን ፈጽሞ መመለስ እንደልዩ ዕድል የሚቆጠርበት በዚህ ትዕይንት በዋና መሥሪያ ቤቱም ሆነ በቅርንጫፉ ግቢና ደጃፎቹ በርከት ያሉ ተገልጋዮች ምሬት ሲያሰሙ መስማት የተለመደ ነው፡፡

በርግጥ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ ሥርዓት ተዘርግቷል፤ የአሠራር ሥርዓቱም በመጠኑ መሻሻል ታይቶበታል፤ ይሁን እንጂ አሁንም ከሕዝብ ፍላጎት ጋር የአገልግሎት አሰጣጥን ማጣጣም፣ ሙሉ አሠራሩንም ማዘመን ፣ ታትሞ የደረሰ ፓስፖርት እንዳለውም ቅልጥፍ.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125054
አዋጁ ሃይማኖታዊ በዓላት አከባበርና የጋራ ድሎችን እውቅና ለመስጠት ያስችላል
******************
(ኢ ፕ ድ)
የሜዳይ፣ ኒሻን ሽልማት አዋጅ የሃይማኖት እና የድል በዓላትን አከባበር እንዲሁም በጋራ የተሳኩ ድሎችን እውቅና መስጠትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የሕግ አማካሪ አለምአንተ አግደው ገለጹ፡፡

የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሜዳይ፣ ኒሻን ሽልማት ረቂቅ አዋጅ ላይ የአስረጂ መድረክ አካሂዷል፡፡

በአስረጂ መድረኩ ላይ የተገኙት የሕግ አማካሪው አለምአንተ፤ የሃይማኖት እና የድል በዓላትን አከባበር፣ የማህበራዊ እሴቶችን እና በጋራ ያሳካናቸውን ድሎች እውቅና መስጠትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በተቋም ግንባታ እና በሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ገልፀው፣ ለሀገር አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰዎችን በመሸለም ሌሎች የሚበረታቱበት ሥርዓት የመፍጠር እሳቤ እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡

ትውልድን ለማነሳሳት እና አርአያ በመሆን ሌሎች እንዲነሳሱ በማድረግም ፋይዳው የጎላ መሆኑን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125065
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ብሔራዊ ሁነት” ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች ‼️

👉ስታርት አፕ በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ፣ ገቢ የሚያመነጭ እንዲሁም ለአንድ ጉዳይ መፍትሔ ያለው ፈጠራ ነው፣

👉ስታርት አፖችን መደገፍ ከቻልን የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ፣

👉 በዓለም ላይ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ያላቸው አንድ ሺህ 200 ስታርት አፖች አሉ፣

👉ከአምስት ዓመታት በፊት በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ 50 ስታርት አፖች ነበሩ፤ አሁን ላይ ግን 900 ደርሰዋል፣

👉ወጣቶች አዲስ ፈጠራ ሲጀምሩ በቅድሚያ ሥራውን መውደድ፣ ሥራውን በራሱ መቻላቸውን ማረጋገጥ፣ ፈጠራው ተፈላጊና በገበያ ላይ ሊሸጥ የሚችል መሆኑን ማወቅ አለባቸው፣

👉ወጣቶች ትልቅ አስበው ከትንሽ በመነሳት ለሀገር የሚተርፍ የፈጠራ ሥራ ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፣

👉 የስታርታፕ አውዱ ጅማሮ ላይ ቢሆንም ችግሮች ግን የሉበትም ማለት አይደለም፣

👉ከለውጡ በፊት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የፋይናንስ አገልግሎት የሚያከናውን ወንጀለኛ ሆኖ ይጠየቅ ነበር፣

👉አሁን ላይ ግን በርካታ ተቋማት በዘርፉ ተሰማርተው ገንዘብ እያንቀሳቀሱ ይገኛል፣

👉 መንግሥት ስታርት አፖችን መደገፍ ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘቡ የተለያዩ ማበረታቻዎችን እያደረገ ነው፣

ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125052
“ክልሎችን በአፈጻጸምና በውጤት ማቀራረብ ቀጣይ ተልዕኳችን ነው”
- አቶ አደም ፋራህ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ክልሎችንና ከተማ አስተዳደሮችን በግንዛቤ፣ በአፈጻጸምና በውጤት ማቀራረብ የቀጣይ ተልዕኳችን ነው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም ፋራህ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተካሄደው ድጋፋዊ የመስክ ምልከታ ሪፖርት ውይይት ላይ እንደገለጹት፤ የመስክ ምልከታው በቀጣይ ሊሚከናወኑ ተግባራት ግብዓት የተገኘበት፣ የአመራሩንና የማኅበረሰቡን ችግር የሚፈታ ነው፡፡

የመስክ ምልከታ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የአፈጻጸም ልዩነት እንዳለ የተለየ መሆኑን ገልጸው፤ በግንዛቤ፣ በአፈጻጸምና በውጤት የማቀራረብ ሥራ የቀጣይ ተልዕኮ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የፌዴራልና የክልል መንግሥታትን ቅንጅት ለማረጋገጥ እና በሁሉም አካባቢዎች የተቀራረበ አፈጻጸም እንዲኖር የተቀናጀ ሥራ እንደሚሰራ አመልክተው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከክልል አቻ ተቋማት ጋር እቅድ የማናበብ፣ አፈጻጸምን በጋራ የመገምገምና የተሻለ ተሞክሮን በመቀመር ልምድ እንዲለዋወጡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በመስክ ምልከታው የታዩትን ክፍተቶች ለመፍታት ጥረት መደረጉን ገልጸው፤ በቀጣይም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተገኘውን ግብዓት የእቅዳቸው አካል በማድረግ ተግባራዊ መፍትሄ የሚሰጡበትን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125053
ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር አንድ ነጥብ 72 ቢሊየን ዶላር የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈራረመች
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊየን ዶላር የፍይናንስ ድጋፍና የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የብድርና የድጋፍ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትንና እድገትን ለማምጣት ለታቀዱ ስድስት ፕሮጀክቶችን ለመተግበር እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ድጋፍና የብድር ስምምነቱ ለምግብ ዋስትና መርሐግብርን ለመደገፍ፤ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ለማጠናከር፤ በቆላማ አካባቢዎች ለሚገኙ አርብቶ አደርና አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ኑሮንና የአየር ንብረትን የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ፤ ለሀይል አቅርቦት ማሻሻያ፣ ለሁለተኛው የከተማ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እንደሚውል ተገልጿል።

መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
መጪው የኢድ አልፈጥር በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል - የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽቤት
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ለመጪው የኢድ አልፈጥር በአል መዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት በዓሉን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

የጽህፈት ቤቱ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በሰጡት መግለጫ፣ የ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ህዝበ ሙስሊሙ በሰላምና በደስታ እንዲከበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአውቶሜሽንና ኢነርጂ ማኔጅመንት ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዘሪሁን አበበ በበኩላቸው ከኮሪደር ልማቱ ጋር በተገናኘ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንዳያጋጥም ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ጽዳት ኤጀንሲ ምክትል ሃላፊ አቶ ሙላት ተገኝ በበኩላቸው በዓሉ ከእርድ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ አከባቢዎችን የማጽዳት ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡም የእርድ ተረፈ ምርትን በአግባቡ ሊያስወግድ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ፎቅሬ ግዛው በበኩላቸው በዓሉ በሚከበርበት ወቅት እሳትና አደጋ እንዳያጋጥ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በአማን ረሺድ
ሥራ ፈላጊ ነዎት⁉️
መልካም ዕድል 🙏
በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ለአሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶች

👉 ከቴዎድሮስ አደባባይ በብሄራዊ ቴአትር ወደ ወደ መስቀል አደባባይ ሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

👉 ከኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ

👉 ከቦሌ አቅጣጫ  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኦሎምፒያ አደባባይ

👉 ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

👉 ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና  ሲኒማ

👉 ከቅ/ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን በአዲሱ መንገድ  ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ ለገሀር መብራት

👉 ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ቴሌ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት

👉 ከጌጃ ሰፈር አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ሰንጋተራ ትራፊክ መብራት

👉 ከሃራምቤ  መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት ላይ

👉 ከብሔራዊ ቤተ መንግስት  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ  ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

👉 ከካዛንቺስ ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ

👉 ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81፤ በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ ጥሪ ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን አስተላልፏል።

መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ባለፉት 6 ዓመታት የከተማዋን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ባለፉት 6 ዓመታት የከተማዋን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ ገለጹ።

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ዓመታት የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ እንደተናገሩ፤ ለውጡ ለአዲስ አበባ አዲስነት ብዙ ገጸ በረከቶችን አምጥቷል።

በተለይም በከተማዋ የተከናወነው የቤት ልማት የሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካሞችን፣ የልማት ተነሺዎችን እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል አቶ ዣንጥራር ።

ከተማዋ ለረጅም ዓመታት የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማዕከልነቷን የማይመጥኑ መሰረተ ልማቶች የነበሩባት ከተማ ነበረች ብለዋል።

የለውጡ መንግስት ለሰው ልጅ ከምግብ ባለፈ ራሱን የሚያዳምጥበት አረንጓዴ ቦታዎችና ፓርኮች ገንብቷል ያሉት አቶ ዣንጥራር፤ የኑሮ ውድነትን በማሻሻል በኩል የእሁድ ገበያን ጨምሮ ትላልቅ የገበያ ማዕከላት ተገንብተዋል። እነዚህም ዝቅተኛ ገቢ ያለቸውን የከተማዋን ነዋሪዎች መሰረት ያደረጉ ማቸው ብለዋል።

የትምህርት ቤት ምገባ፣ የሌማት ትሩፋት ሥራዎች እና የዳቦ ምርት መጠንን ከመጨመር አኳያ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን የገለጹት አቶ ዣንጥራር፤ በቀጣይ በከተማዋ የሚስተዋሉ የልማትና መሰል ችግሮችን ለመፍታት የለውጡ መንግስት የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሳሙኤል ወንደሰን

መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም