Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአዲስ አበባ ባለፉት 6 ዓመታት የከተማዋን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ባለፉት 6 ዓመታት የከተማዋን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ ገለጹ።

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ዓመታት የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ እንደተናገሩ፤ ለውጡ ለአዲስ አበባ አዲስነት ብዙ ገጸ በረከቶችን አምጥቷል።

በተለይም በከተማዋ የተከናወነው የቤት ልማት የሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካሞችን፣ የልማት ተነሺዎችን እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል አቶ ዣንጥራር ።

ከተማዋ ለረጅም ዓመታት የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማዕከልነቷን የማይመጥኑ መሰረተ ልማቶች የነበሩባት ከተማ ነበረች ብለዋል።

የለውጡ መንግስት ለሰው ልጅ ከምግብ ባለፈ ራሱን የሚያዳምጥበት አረንጓዴ ቦታዎችና ፓርኮች ገንብቷል ያሉት አቶ ዣንጥራር፤ የኑሮ ውድነትን በማሻሻል በኩል የእሁድ ገበያን ጨምሮ ትላልቅ የገበያ ማዕከላት ተገንብተዋል። እነዚህም ዝቅተኛ ገቢ ያለቸውን የከተማዋን ነዋሪዎች መሰረት ያደረጉ ማቸው ብለዋል።

የትምህርት ቤት ምገባ፣ የሌማት ትሩፋት ሥራዎች እና የዳቦ ምርት መጠንን ከመጨመር አኳያ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን የገለጹት አቶ ዣንጥራር፤ በቀጣይ በከተማዋ የሚስተዋሉ የልማትና መሰል ችግሮችን ለመፍታት የለውጡ መንግስት የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሳሙኤል ወንደሰን

መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም
ሥራ ፈላጊ ነዎት⁉️
መልካም ዕድል 🙏
እንደሀገር ለስታርት አፕ’ ዘርፉ ዕድገት መሠረት የሚጥሉ ማሻሻያዎች ተደርገዋል” – ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
*****
(ኢ ፕ ድ)

እንደሀገር ለ‘ስታርት አፕ’ ዘርፉ ዕድገት መሠረት የሚጥሉ የተለያዩ የሕግና የፋይናንስ አሠራር ማሻሻያዎች መደረጋቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ።

የ’ስታርት አፕ’ ኢትዮጵያ ዓውደ ጥናት ትናንትና በሳይንስ ሙዚየም በተዘጋጀበት ወቅት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፤ ቴክኖሎጂን ማዕከል አድርገው በሚከናወኑ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታት የሚረዱ የተለያዩ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።

ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል አንዱ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ሃሳባቸውን ወደ ተግባር ለማዋል በሚፈልጉበት ወቅት ያለምንም የንግድ ቤት ኪራይ ውል ሥራ መጀመር የሚችሉበትን አዲስ አሠራር መዘርጋቱ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ማንኛውም የውጭ ሀገር ፈንድ ያገኘ ስታርት አፕ ሙሉ በሙሉ የውጭ ምንዛሪውን ለሚፈልገው ሥራ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125133
ሰሞኑን ያጋጠመው የነዳጅ እጥረት ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል
👉 በቀን ሦስት ሚሊዮን ሊትር የሚጠጋ ነዳጅ ወደ ሀገር እየገባ ነው
**
(ኢ ፕ ድ)
በቅርቡ አጋጥሞ የነበረው የነዳጅ እጥረት በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ መቅረፍ ተችሏል ሲል የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ፡፡ በቀን ሦስት ሚሊዮን ሊትር የሚጠጋ ነዳጅ ወደ ሀገር እየገባ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ዓለማየሁ ፀጋዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የነዳጅ እጥረቱ አጋጥሞ የነበረው በጅቡቲ ጥሎ በነበረው ከባድ ዝናብ ምክንያት መንገዶች በመዘጋጋታቸው ነው፡፡ በዚህ ሳቢያም ነዳጅ የሚጭኑ ከባድ ቦቴዎች ወደ ሀገር መግባትም ሆነ መውጣት አልቻሉም ፡፡

መንገዱ ከዚህ ቀደምም ችግር የነበረበት ነው ያሉት ባለሙያው፤ ከሹፌሮችም በተደጋጋሚ ስሞታ የሚቀርብበት ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

አቶ ዓለማየሁ፤ ድርጅቱ ያጋጠመውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በድሬዳዋ በኩል እንዲገቡ መደረጉን ገልጸው፤ በዚህም አጋጥሞ የነበረውን ችግር ሙሉ በሙሉ መቅረፍ መቻሉን አንስተዋል፡፡

ችግሩ ከማጋጠሙ በፊት በቀን በአማካኝ ከ250 እስከ 300 የሚሆኑ ነዳጅ የሚጭኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125144
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሩዋንዳ ኪጋሊ ገብተዋል።

መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓም
ጢያ ትክል ድንጋይን የሀገሪቱ ሁነኛ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ ነው
******
(ኢ ፕ ድ)

ጢያ ትክል ድንጋይን የሃገሪቱ ሁነኛ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው አስታወቁ። ከግል ባለሃብቶች ጋር በመተባበር ሌሎችንም በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶችና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ለማስተዋወቅና የክልሉን የገቢ አቅም ከፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ እንዳሻው ጣሰው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ክልሉ ከየም ሳጃ ጀምሮ እስከ ጢያ ድረስ እንዲሁም በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች ሰፊ የተፈጥሮና የማይዳሰሱ ሃብቶች ይገኛሉ። ይሁንና እነዚህን ሃብቶች የቱሪዝም መዳረሻ ከማድረግ አኳያ እስካሁን የተሠሩት ሥራዎች እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም።

በተለይም የክልሉ ሕዝብ የዘመናት ቁጭት ሆኖ ቆይቷል። በመሆኑም የክልሉ መንግሥት በተለይም የጢያ ትክል ድንጋይ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በመገንባት ለሃገሪቱ ሁነኛ የቱሪዝም መዳረሻ ....

https://press.et/?p=125130
ለልማት ተነሺዎች የተሰጡ ቤቶች መሠረተ ልማታቸው በፍጥነት እየተሟላ ነው
***
(ኢ ፕ ድ)

ለልማት ተነሺዎች የተሰጡ ቤቶችን መሠረተ ልማታቸው በፍጥነት እየተሟላ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ጽጌወይን ካሣ እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ በኮሪደር ልማቱ አማካኝነት የሚነሱ ነዋሪዎች የገቡባቸው ቤቶች አብዛኛዎቹ ቤቶች መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ቢሆኑም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ያልተሟሉ በመኖራቸው በፍጥነት እንዲሟላ እየተደረገ ይገኛል።

የውሃ፣ የኤሌክትሪክና ሌሎች መሠረተ ልማቶቻቸው በፍጥነት እንዲሟሉ መደረጉን በመጠቆም፤ የመሠረተ ልማት ጥያቄ በቀረበባቸው ቦታዎች ላይ የማስተካከያ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አመላክተዋል።

በኮሪደር ልማቱ የተነሱ ነዋሪዎች በኪራይም ሆነ በይዞታ የሚያገኟቸው ቤቶች ቅድሚያ ከሚኖሩበት የተሻለ የሚባል ደረጃ አላቸው ያሉት ወይዘሮ ጽጌወይን፤ የተሻለ ከተማን ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ለነዋሪዎች.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125145
በቀጣይ አስር ቀናት ውስጥ የሚኖረው የአየር ሁኔታ ለበልግ አብቃይ አካባቢዎች ምቹ ነው
******
(ኢ ፕ ድ )

በሀገሪቱ በቀጣይ አስር ቀናት ውስጥ የሚኖረው የአየር ሁኔታ ለበልግ አብቃይ አካባቢዎች ምቹ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢፕድ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በቀጣይ አስር ቀናት ውስጥ የበልግ ዝናብ በአብዛኛዎቹ የበልግ አብቃይ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እየተጠናከረና እየተስፋፋ የሚሄድ ሲሆን በርካታ ቦታዎችን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የዝናብ መጠን ያገኛሉ።

በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ የሰሜን ምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።

በዚህም በአብዛኛው የበልግ ዝናብ አብቃይ ስፍራዎችን የሚሸፍን እርጥበት ያገኛሉ። ይህም ቀደም ብለው ለተዘሩ ሰብሎችና ለቋሚ ተክሎች የውሃ ፍላጎትን መሟላት እንዲሁም የረጅም ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት እና የማሳ ዝግጅት ለማከናወን...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125155
በርካታ ህዝብ የታደመበት የአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል -የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል
*******
(ኢ ፕ ድ)

በርካታ ህዝብ የታደመበትና በአዲስ አበባ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ ፡፡

ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱና ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ አካላት ምስጋና አቅርቧል፡፡

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በስኬት እና በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።

የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የታደሙበት የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን ግብር ኃይሉ አስታውቋል።

በያዝነው ዓመት በርካታ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት የታደመባቸው ልዩ ልዩ ኹነቶች ሃይማኖታዊ በዓላት እና ስፖርታዊ ዝግጅቶች በሰላም መከናወናቸውንም የግብረ-ሃይሉ መግለጫ አስታውሷል።

ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የተለመደውን ትብብር በማድረጉና በተለይ መላው የፀጥታ አካላት ድካማቸውን ተቋቁመው ሃላፊነታቸውን በትጋት በመወጣታቸው በ2016 ዓ.ም ከተማችን ያስተናገደቻቸው አበይት ኩነቶች ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ማድረጉም ተገልጿል።

መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓም