ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ምርጫ ሕዝብ እውነተኛ የሥልጣን ባለቤት መሆኑ የሚገለጥበት ነው።
"ወዳጄ ናሬንድራ ሞዲ ሰላማዊ ምርጫ በማካሄድ ለድል በመብቃትዎ እንኳን ደስ ያለዎ" ብለዋል።
በህንድ በተካሄደ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሕንድ በተካሄደው ምርጫ ለሦስተኛ ጊዜ አሸንፈዋል።
ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

አፍሪካ ያላትን ከዓለም 30 በመቶ የማዕድን ክምችት ለመጠቀም ጠንካራ ሥራ ይጠይቃል
************
(ኢ ፕ ድ)
አፍሪካ ያላትን ከዓለም 30 በመቶ የሚሆነውን የማዕድን ክምችቷን አውጥቶ ለመጠቀም ተግባራዊ የሆነ ስትራቴጂ መንደፍና ጠንካራ ሥራ ማከናወን እንደሚገባ የአፍሪካ ማዕድን ልማት ማዕከል አስታወቀ፡፡
ለዓለም ካርቦን ቅነሳ መሠረታዊ የሆኑ ማዕድናትን ጥቅም ላይ ከማዋል አንፃር የአፍሪካ አቅም የሚያድግበት ሁኔታ ላይ የመከረ ጉባኤ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና በአፍሪካ ማእድን ልማት ማዕከል አማካኝነት ሰሞኑን ተካሂዷል።
የአፍሪካ ማዕድን ልማት ማዕከል ጊዜያዊ ዳይሬክተር ማሪት ያየህይራድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አፍሪካ ከዓለም 30 በመቶ የሚሆነውን የማዕድን ክምችት...
https://press.et/?p=129348

አዲስ የሥራ ባህል የፈጠረው አዲስ ልማት
************
(ኢ ፕ ድ)
ጥቁሩ የአስፓልት መንገድ ምቹ ሆኗል፤ የግራና የቀኝ እግረኛ መንገዱ ሁሌም ሂዱብኝ ሂዱብኝ ይላል፡፡ ሕንፃዎቹ ውበትን ተላብሰዋል፡፡
በተለይ የኮሪደር ልማቱ ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ የሚወስደውን መንገድ ሁለተናዊ ውበትና ምቹነት አላብሶታል፡፡
የመዲናዋ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ውበት የሚጨምሩ የሕዝብ መናፈሻ ስፍራዎች፣ ፋውንቴኖችና የአረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም የመንገድ ሥራዎች እየተጠናቀቁ ነው፡፡ የተጠናቀቁም እንዳሉ ተመልክተናል።
ይህንን ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ በምሽት ጭምር የግንባታ ሥራው እየተሠራ እንደሆነ የኢፕድ ሪፖርተሮች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ኮሪደር ልማት ሥራው ላይም የብሎኬት፣ የግንብ፣ የጠርዝ ሥራዎችን ሲሠሩ ያገኛቸውን አቶ አባይነህ ናናን አነጋግረናል።
የኮሪደር ልማቱ የመዲናዋን የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴን በማሳለጥ ረገድ ትልቅ ትርጉም ያለው ከመሆኑም በላይ የሥራ ባህላችንን......
https://press.et/?p=129347

የጅምላና ችርቻሮ ንግድ ለውጭ ባለሀብቶች መፈቀዱ ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ ነው
**********
(ኢ ፕ ድ)
የጅምላና ችርቻሮ ንግድ ሥራ ለውጭ ባለሀብቶች መፈቀዱ የግሉ ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን በማድረግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ያሳድጋል ሲሉ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ተናገሩ፡፡
የምጣኔ ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ የጅምላና ችርቻሮ ንግድ ሥራ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት መደረጉ የግሉን ዘርፍ ተወዳዳሪ በማድረግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ያሳድጋል፤ የዋጋ ግሽበት ችግርን ለመፍታትም የራሱ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ታሪክ ከአምስት አስርት ዓመታት በኋላ የውጭ ባለሀብቶች በሀገር ውስጥ የጅምላና የችርቻሮ ንግድ ላይ እንዲሰማሩ መንግሥት መፍቀዱን አውስተው፤ ይህም የግሉን ዘርፍ በሀገር ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን በማሳደግ የሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት.....
https://press.et/?p=129338

ቋሚ ኮሚቴው ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታን ለማግኘት መሥራት እንዳለባቸው አሳሰበ
***********
(ኢ ፕ ድ)
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጣቸው የሕዝብ አመኔታን ለማትረፍ መሥራት እንዳለባቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ቋሚ ጉዳዮች አሳሰበ፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለ143 ሺ 455 መዛግብት እልባት መሰጠቱ ተጠቁሟል፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶቹ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና እና ጥራት ለማሻሻል የተጀመሩ ሥራዎች ጥሩ መሆናቸውን የጠቆመው ቋሚ ኮሚቴው፤ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡ ግን የሕዝብ አመኔታን አግኝቶ የሚፈለገውን.....
https://press.et/?p=129337

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲንጋፖር የመጀመሪያ ቀን ጉብኝታቸው በብሔራዊው የእፅዋት ማዕከል ባህላዊውን እፅዋት የመሰየም ሥነሥርዓት ተካፍለዋል።
በሥነሥርዓቱም በኢትዮዽያ እና ሲንጋፖር መካከል ያለውን መልካም ወዳጅነት እና የጋራ መንፈስ ለማመላከት 'አራንዳ ዐቢይ አሕመድ ዝናሽ ታያቸው' የተሰኘ የኦርኪድ አበባ በስማቸው ተሰይሞላቸዋል።
ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋት በሚሰራው ስራ ላይ እገዛ ማድረግ እንደሚፈልግ ገለፀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋት በሚሰራው ስራ ላይ እገዛ ማድረግ እንደሚፈልግ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን የዓለም ባንክ የትራንስፖርትና ኢነርጂ ቡድንን ትናንት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በሀገራችን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪወዎችን በስፋት ወደ አገልግሎት ለማስገባት የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የተለያዩ ስትራቴጂዎችና ስታንዳርዶችን በመቅረፅና በመተግበር በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን በነበራቸው ውይይት አንስተዋል።
በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የአስር አመት የልማት እቅድ 148ሺህ አውቶሞቢሎችና ከ4ሺህ 800 በላይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶች እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዘርፉ የተያዘውን ግብ ለማሳካት መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ለሚያስገቡና በሀገር ውስጥ ለሚገጣጣጥሙ አካላት የታክስ ማበረታቻ ከማድረግም በተጨማሪ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።
አጋር አካላት የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ የቻርጅ መሙያ ማዕከላትን በማስፋፋት፣ በጋራዥና ጥገና ዘርፍ፣ በዘርፉ ባለሙያዎችን በማሰልጠን በኩል እገዛ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ የግንዛቤ ክፍተት በመኖሩ የአመለካከት ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የግንዛቤ ማሳደግ ስራ ላይም በትብብር መስራት እንፈልጋለን ሲሉ አክለዋል።
እንደ ሀገር ታዳሽ የሀይል ምንጭን በመጠቀም ከተሽከርካሪዎች የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ ለመቀነስ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ በብዙሃን ትራንስፖርት እና በሞተር አልባ ትራንስፖርት ማስፋፋት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ለተግባራዊነቱ የአጋር አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የዓለም ባንክ የቴክኒክና ኢነርጂ ቡድን ሚኒስቴር መ/ቤቱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋትና ታዳሽ የሀይል ምንጭን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያደርገው ጥረት ሊደገፍ የሚገባ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ከተደረገላቸው ገለፃ በመነሳት ሚኒስቴር መ/ቤቱን ቅድሚያ ሰጥቶ በሚሰራባቸው ጉዳዮች እና የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን መፍታት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ እገዛ ማድረግ እንደሚፈልግ ቡድኑ አሳውቋል።
በመጨረሻም ሚኒስትር ዴኤታው በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ላይ አጋር በመሆን እገዛ እያደረገ የሚገኘው የዓለም ባንክ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስፋፋትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት በማሳየቱ ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ግንቦት 29/2016 ዓ.ም