ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲንጋፖር የመጀመሪያ ቀን ጉብኝታቸው በብሔራዊው የእፅዋት ማዕከል ባህላዊውን እፅዋት የመሰየም ሥነሥርዓት ተካፍለዋል።
በሥነሥርዓቱም በኢትዮዽያ እና ሲንጋፖር መካከል ያለውን መልካም ወዳጅነት እና የጋራ መንፈስ ለማመላከት 'አራንዳ ዐቢይ አሕመድ ዝናሽ ታያቸው' የተሰኘ የኦርኪድ አበባ በስማቸው ተሰይሞላቸዋል።
ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋት በሚሰራው ስራ ላይ እገዛ ማድረግ እንደሚፈልግ ገለፀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋት በሚሰራው ስራ ላይ እገዛ ማድረግ እንደሚፈልግ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን የዓለም ባንክ የትራንስፖርትና ኢነርጂ ቡድንን ትናንት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በሀገራችን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪወዎችን በስፋት ወደ አገልግሎት ለማስገባት የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የተለያዩ ስትራቴጂዎችና ስታንዳርዶችን በመቅረፅና በመተግበር በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን በነበራቸው ውይይት አንስተዋል።
በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የአስር አመት የልማት እቅድ 148ሺህ አውቶሞቢሎችና ከ4ሺህ 800 በላይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶች እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዘርፉ የተያዘውን ግብ ለማሳካት መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ለሚያስገቡና በሀገር ውስጥ ለሚገጣጣጥሙ አካላት የታክስ ማበረታቻ ከማድረግም በተጨማሪ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።
አጋር አካላት የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ የቻርጅ መሙያ ማዕከላትን በማስፋፋት፣ በጋራዥና ጥገና ዘርፍ፣ በዘርፉ ባለሙያዎችን በማሰልጠን በኩል እገዛ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ የግንዛቤ ክፍተት በመኖሩ የአመለካከት ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የግንዛቤ ማሳደግ ስራ ላይም በትብብር መስራት እንፈልጋለን ሲሉ አክለዋል።
እንደ ሀገር ታዳሽ የሀይል ምንጭን በመጠቀም ከተሽከርካሪዎች የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ ለመቀነስ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ በብዙሃን ትራንስፖርት እና በሞተር አልባ ትራንስፖርት ማስፋፋት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ለተግባራዊነቱ የአጋር አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የዓለም ባንክ የቴክኒክና ኢነርጂ ቡድን ሚኒስቴር መ/ቤቱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋትና ታዳሽ የሀይል ምንጭን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያደርገው ጥረት ሊደገፍ የሚገባ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ከተደረገላቸው ገለፃ በመነሳት ሚኒስቴር መ/ቤቱን ቅድሚያ ሰጥቶ በሚሰራባቸው ጉዳዮች እና የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን መፍታት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ እገዛ ማድረግ እንደሚፈልግ ቡድኑ አሳውቋል።
በመጨረሻም ሚኒስትር ዴኤታው በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ላይ አጋር በመሆን እገዛ እያደረገ የሚገኘው የዓለም ባንክ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስፋፋትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት በማሳየቱ ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ግንቦት 29/2016 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሲንጋፖር ሪፐብሊክ በኢስታና ቤተመንግስት በነበራቸው ቆይታ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በሁለትዮሽ ምክክር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ብሎም በኢፌዲሪ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሲንጋፖር የትራንስፖርት ሚኒስቴር መካከል የፍላጎት ስምምነት ተፈርሟል።
ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም
ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም
በውኃ ሀብት ተጠቃሚዎች የሚነሱ ግጭቶችንና የውኃ ብክነትን ለማስቀረት እየተሰራ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
በውሀ ሀብት ተጠቃሚዎች የሚነሱ ግጭቶችንና የውሀ ብክነትን ለማስቀረት እየተሰራ እንደሚገኝ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የዋቢ ሸበሌ፣ የገናሌ ዳዋና የኦሞ ግቢ ተፋሰሶች እቅድ የማጽደቅና የተፋሰስ ተጋሪ ክልሎች ፎረም ምስረታ መርሐግብር እየተካሄደ ነው።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዴኤታ አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የውሃ ሀብት አስተዳደርን በማስፈን ተፋሰሶችን ከጉዳትና ብክለት ተጠብቀው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በእቅድ መመራት እንዳለባቸው በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በውሀ ሀብት የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታትና የውሀ በክነትንና ብክለትን ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ የውሀ ሀብትን ከብክለትና ከአደጋ መከላከል የሚያስችል ቴክኒካል ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ኢትዮጽያ በቂ የዝናብ መጠን፣ በርካታ ወንዞች፣ ሀይቆች እና የተለያዩ የውሃ ሀብት ቢኖራትም ከህዝብ ብዛት መጨመርና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ አልተቻለም ሲሉ ተናግረዋል።
ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የውሃ ሀብትን በፍትሀዊነት ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ የተናበበና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ እቅድ ሊኖር ይገባል ያሉት ዶክተር አብርሀም፤ በዚህም መሰረት የዋቢ ሸበሌ፣ የገናሌ ዳዋና የኦሞ ግቢ ተፋሰሶችን እቅድ በማውጣት ለማስጸደቅ መድረክ ተዘጋጅቷል ብለዋል።
የአባይ፣ የአዋሽ፣ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች እና ዛሬ የሚመሰረተውን የዋቢ ሸበሌ፣ የገናሌ ዳዋና የኦሞ ግቢ የተፋሰስ ተጋሪ ፎረም ጨምሮ በሀገሪቱ ስድስት የውሃ ሀብት ፎረሞች ይኖራሉ ብለዋል።
በመርሐግብሩ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌደራል ተቋማት፣ ከስድቱ ክልሎች የተውጣጡ አመራሮች ተገኝተዋል።
በሄለን ወንድምነው

በልማት ኮርደር ስራ ከለሙ አካባቢዎች ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ መሃሙድ ሙዚቃ ቤት ያለው አሁናዊ ገጽታ‼️