Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት አይነተኛ ሚና ይጫወታል"
-አምባሳደር ዘሪሁን አበበ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር
**********************
(ኢ ፕ ድ)
እየተጠናከረ የመጣው የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት አይነተኛ ሚና ይጫወታል ሲሉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ገለጹ።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ለኢፕድ እንደገለጹት፤የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየጠበቀ መምጣቱ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት አይነተኛ ሚና ይጫወታል።

የኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ግንኙነት የሁለቱ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ያደረገና ግንኙነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ የመጣ ነው ያሉት አምባሳደር ዘሪሁን፤ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ለሰላምና መረጋጋትና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ዓላማ ላይ ለነጻነቷ ከፍተኛ ዋጋ ከፍላለች ብለዋል።

አምባሳደር ዘሪሁን፤ ሁለቱ ሀገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፤ በሕዝቦች ለሕዝቦች፣ ፖለቲካዊ ግንኙነት እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129408
የሚኒስትሮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎች‼️

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

✍️ ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የ2017 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2017 ዓ.ም. የፌደራል መንግስት በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ ፤ የ2016 የፌደራል መንግስትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፤ የመንግስት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ፣ ለካፒታል ወጪዎች ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

✍️ በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በአረንጓዴ አሻራ የተጀመሩ ሰፊ ሥራዎች ቀጣይነትን ለማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካላት የቆዳ ስፋት ከግማሽ በላይ የሆነው የተጎሳቆለ መሬት እንዲያገግም ለማድረግ፣ የደን ዘርፉ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲሰጥ ለማስቻል፣ በአሁኑ ወቅት በተበጣጠሰ መልኩ በፌዴራል መንግስትም ሆነ በክልል መንግስታት ፋይናንስ እየተደረገ እየተሰራ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት በተቀናጀና ተገቢውን ሀብት መመደብ በሚያስችል የፋይናንስ አሰራር ስርዓት መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

✍️ በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው፡፡ ተቋማቱ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣ አሰራሮችና የሰለጠነ የሰው ሀይል በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጣቸውን የጥራት ደረጃ ማሻሻል ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ የሚያስችል ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቦቹ ተዘጋጅተው ቀርበዋል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በኦሮሚያ ክልል ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሥራ እድል ተፈጠረ
**********************
(ኢ ፕ ድ)

በ2016 በጀት ዓመት አስር ወራት ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ወጣቶች የሥራ እድል መፈጠሩን የኦሮሚያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ኤባ ገርባ (ኢ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዘንድሮው በጀት ዓመት ባለፉት 10 ወራት ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል።

ለሥራ ዕድል ፈጠራው በመንግሥት ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብሮች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ኃላፊው አንስተዋል።

በኦሮሚያ ክልል በየዓመቱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ወደ ሥራው ዓለም ይቀላቀላሉ ተብሎ ይገመታል ያሉት ኃላፊው፤ በበጀት ዓመቱ በክልሉ ያሉ በርካታ የሥራ እድል ፈጠራ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129447
በሶማሌ ክልል ከለውጡ በኋላ ብቻ ከ230 በላይ አዳዲስ ፋብሪካዎች ሥራ ጀምረዋል
******************
(ኢ ፕ ድ)

ከለውጡ በኋላ ባሉት ስድስት ዓመታት ብቻ በክልሉ ከ230 በላይ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ፋብሪካዎች መከፈታቸውን የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ።

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ ለተሠማራው የጋዜጠኛ ቡድን እንደገለጹት ፤ ክልሉ ያገኘውን ሰላም ተከትሎ የኢንቨስተሮች ቁጥር እያደገ መጥቷል። ከለውጡ በኋላ ባሉት ስድስት ዓመታት ብቻ በክልሉ ከ230 በላይ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ፋብሪካዎች ተከፍተዋል።

ቀደም ሲል በክልሉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ይህ ነው የሚባል ሥራ እንዳልነበር የጠቀሱት ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ ፤ ለዚህም ምክንያቶቹ፣ የሰላም እጦት ፣ የኢንቨስተሩ ዋስትና ማጣት እንዲሁም የነበረው መንግሥት ለኢንቨስትመንት ትኩረት አለመስጠቱ እንደሆኑ ጠቅሰዋል። በዚህም ምክንያት ከለውጡ በፊት በክልሉ አጠቃላይ የነበሩት ፋብሪካዎች....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129478
እንሰትን ዋና የምግብ ሰብል የማድረግ ጥረት
**************
(ኢ ፕ ድ)

በአፈጣጠሩ የሙዝ ተክል የሚመስለው “እንሰት” በኢትዮጵያ ብቻ ለምግብነት የሚውል ሰብል ነው። ከእንሰት ስር የሚወጣው ቆጮ በዳቦ መልክ ሲዘጋጅ፣ ቡላው በገንፎ መልክ ለምግብነት ይውላል። የእንሰት ተረፈ ምርት የሆነው ቃጫም ለግንባታና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓትነት የሚውል ነው። እንሰት በንጥረ ነገር ይዘቱ የበለጸገ መሆኑንም በሰብሉ ላይ ምርምር ያካሄዱ ምሁራን ይናገራሉ።

የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴ ሆኖ በመቆየት አቅሙም ከሌሎች ሰብሎች የተለየ ባህሪው መሆኑ ይነገርለታል። በአመዛኙ በሀገራችን ደቡባዊ አካባቢዎችና በኦሮሚያ የተወሰኑ አካባቢዎች የሚዘወተረው እንሰት በርካታ የጤና ጥቅም ያለው፣ ብዙ ቁጥር ባለው ማኅበረሰብ ዘንድም የሚዘወተር ሰብል ትልቅ ሥፍራ......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129491
በአማራ ክልል 188 ሺህ 631 ሔክታር መሬት በሩዝ ሰብል ለመሸፈን ዕቅድ ተይዟል
***************
(ኢ ፕ ድ)

በአማራ ክልል በዘንድሮ የምርት ዘመን 188 ሺህ 631 ሔክታር መሬት በሩዝ ሰብል ለመሸፈን ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። ዘንድሮ ሰሜን ሸዋና በደቡብ ወሎ ቃሉ አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች ወደ ሩዝ ምርት እንዲገቡ የመሬት ልየታና የዘር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተጠቁሟል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በዘንድሮ የምርት ዘመን የክልሉን የሩዝ ማሳ ሽፋን ወደ 188 ሺህ 631 ሄክታር መሬት ለማድረስ ታቅዷል።

የሩዝ ምርት እንደ ክልል የተሻለ ልምድ አለ ያሉት ያሉት ምክትል ኃላፊው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሩዝ ምርትን ለማሳደግ የተጀመረውን ንቅናቄ በመጠቀም ምርቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

አቶ ቃልኪዳን እንዳስታወቁት፤ በክልሉ ባለፈው የምርት ዘመን 82 ሺህ 279 ሔክታር መሬት በሩዝ ምርት መሸፈን ተችሏል። ዘንድሮ ወደ 188 ሺህ 631 ሄክታር ለማሳደግና በአንድ ሄክታር 53 ኩንታል የሩዝ ምርት....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129480
በወላይታ ዞን አራት ሚሊዮን 953 ሺህ የቡና ችግኞች ተተከሉ
********************
(ኢ ፕ ድ)

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ከሚያዚያ ወር ጀምሮ አራት ሚሊዮን 953 ሺህ የቡና ችግኞች መተከላቸውን የዞኑ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በዘንድሮ ዓመት በዞኑ በአጠቃላይ ስድስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን የቡና ችግኞች ይተከላሉ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ካዉሌ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በዘንድሮ ዓመት የቡና ችግኝ ዝግጅት ስድስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዷል። ከዚህ ውስጥ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የግንቦት መጨረሻ ሳምንት ድረስ አራት ሚሊዮን 953 ሺህ የቡና ችግኞች መተከላቸውንና በሐምሌ ወር በተጨማሪ አንድ ሚሊዮን የቡና ችግኞች እንደሚተከሉ አመላክተዋል።

የቡና ተከላው በተለያዩ ወቅቶች ተከፋፍሎ እየተሠራ መሆኑንና ከጥር ወር ጀምሮ ጉድጓድ የማዘጋጀት ሥራ ሲከናወን መቆየቱን አስታውሰው፤ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የአረንጓዴ ልማት ሥራ እየተከናወነ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129489
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የሚገኙ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የሚገኙ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት አሰታወቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢጃራ ተስፋዬ የተንዳሆና አላሎ ባድ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶች ተመልክተዋል። ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ችግር ለመፍታትና ወደ ስራ ለማስገባት መሆኑን በጉብኝቱ ተገልጿል።

በሚቀጥለው ዓመት ለፕሮጀክቶቹ በጀት በመመድብ ጥገና በማድረግ ወደ ስራ ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በተያያዘ በሰመራ ከተማ የሚገኘውን የኢንስቲትዩቱ ንብረቶች ያሉበትን ሁኔታም መመልክታቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓም
ታንዛኒያ በሰላምና ደኅንነት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ታጠናክራለች
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ታንዛኒያ በሰላምና ደኅንነት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር እንደምትሰራ የሀገሪቱ የመከላከያና ብሔራዊ አገልግሎት ሚኒስትር ስቴርጎሜና ላውረንስ ተናገሩ።

ሚኒስትሯ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ታንዛኒያና ኢትዮጵያ በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ያላቸው ታሪካዊ ትብብር አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

ሁለቱ ሀገራት በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ በትብብር ለመሥራት የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሥምምነት ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑንም አስታውሰዋል።

ታንዛኒያ በቀጣናው እንዲሁም በአህጉር ደረጃ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር ገልፀዋል።

በሰው ኃይል ልማት ትብብር ኢትዮጵያ የታንዛኒያን ሙያተኞች በማሰልጠን ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ትልቅ ሚና እየተጫወተች መሆኗንም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

የሁለቱን ሀገራት የሰላምና ጸጥታ ትብብርን መስክ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ታንዛኒያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራም ተናግረዋል።

ከመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ጋር በዚህ ሳምንት መወያየታቸው ይታወሳል።

ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓም