Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የሚገኙ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የሚገኙ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት አሰታወቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢጃራ ተስፋዬ የተንዳሆና አላሎ ባድ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶች ተመልክተዋል። ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ችግር ለመፍታትና ወደ ስራ ለማስገባት መሆኑን በጉብኝቱ ተገልጿል።

በሚቀጥለው ዓመት ለፕሮጀክቶቹ በጀት በመመድብ ጥገና በማድረግ ወደ ስራ ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በተያያዘ በሰመራ ከተማ የሚገኘውን የኢንስቲትዩቱ ንብረቶች ያሉበትን ሁኔታም መመልክታቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓም
ታንዛኒያ በሰላምና ደኅንነት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ታጠናክራለች
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ታንዛኒያ በሰላምና ደኅንነት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር እንደምትሰራ የሀገሪቱ የመከላከያና ብሔራዊ አገልግሎት ሚኒስትር ስቴርጎሜና ላውረንስ ተናገሩ።

ሚኒስትሯ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ታንዛኒያና ኢትዮጵያ በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ያላቸው ታሪካዊ ትብብር አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

ሁለቱ ሀገራት በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ በትብብር ለመሥራት የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሥምምነት ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑንም አስታውሰዋል።

ታንዛኒያ በቀጣናው እንዲሁም በአህጉር ደረጃ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር ገልፀዋል።

በሰው ኃይል ልማት ትብብር ኢትዮጵያ የታንዛኒያን ሙያተኞች በማሰልጠን ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ትልቅ ሚና እየተጫወተች መሆኗንም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

የሁለቱን ሀገራት የሰላምና ጸጥታ ትብብርን መስክ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ታንዛኒያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራም ተናግረዋል።

ከመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ጋር በዚህ ሳምንት መወያየታቸው ይታወሳል።

ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በአሸናፊ ከበደ የክዋኔ ጥበባት ማዕከል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በመታደሜ ደስ ብሎኛል። አሸናፊ ከበደ ከያኒ ብቻ ሳይሆን የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር ነበር። የአዲሱ ማዕከል ዳይሬክተር ግርማ ይፍራሸዋ ደግሞ በቀደመውና በአሁኑ የኢትዮጵያ ሙዚቃ መካከል ድልድይ በመሆን ያገለግላል። ይህን መሰል ድልድይነትና ቀጣይነት በሁሉም ተቋሞቻችን አስፈላጊ ነው። ሙዚቃ ኃይል አለው። ይህን ኃይል ለወጣቶቻችን አብርሆት ልንጠቀምበት ይገባል። ጥበባት መጪውን ትውልድ ቅርጽ በማስያዝና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕብ በማላቅ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ። ይህን ዐቅም በምሉዕነት መጠቀም ይገባናል።

ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓም
የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ጥገናው ተጠናቆ ዛሬ መደበኛ ሥራውን ይጀምራል
******
(ኢ ፕ ድ )

ለአራት ዓመታት አገልግሎቱ ተቋርጦ የቆየው የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ (ኤርፖርት) ጥገናው ተጠናቆ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም መደበኛ ሥራውን እንደሚጀምር የአክሱም ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ብርሃነ አስታወቁ፡፡

የከተማዋ ከንቲባ አቶ አበበ ብርሃነ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት፤ የአፄ ዮሐንስ አራተኛ የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ በሰሜኑ ጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶበታል ፡፡ ይህን ጉዳት ጠግኖ ወደ ሥራ ለማስገባት በፌዴራል መንግሥት እና በአጋር አካላት ዕቅድ ተይዞ ወደ ትግበራ ተገብቷል፡፡

የአክሱም ኤርፖርት ለከተማዋ ገቢ፣ ቱሪዝምና ንግድ እንቅስቃሴ የጀርባ አጥንት መሆኑን ገልጸው፤ ኤርፖርቱ ለአራት ዓመታት ሥራውን በማቆሙ ምክንያት ለከተማዋ ከባድ ማህበራዊ ቀውስ ፈጥሮ እንደቆየ አውስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ማረፊያው ታህሳስ ወር 2016 ዓ.ም የጀመረው የጥገና ሥራ በፍጥነት ተጠግኖ ወደ ሥራ እንዲገባ ባደረገው ጥረት በተያዘለት ጊዜ ሥራው ተጠናቆ ዛሬ ሰኔ 02 ቀን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129557
በሜዲካል ኮሌጁ ለ400 ታካሚዎች የሥነ ልሳን ህክምና ተሰጠ
***
(ኢ ፕ ድ)

ለ400 ታካዎች የሥነ ልሳን ህክምና መስጠቱን የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አስታወቀ፡፡

በሆስፒታሉ የሥነ ልሳን ህክምና ባለሙያ ዶ/ር አካሉ አሰፋ፣ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት ሆስፒታሉ ባለፉት 11 ወራት ለ400 ህጻናትና አዋቂ ታካሚዎች የሥነ ልሳን ህክምና (Speech Therapy) ሰጥቷል፡፡

ህክምና ያገኙ ታካሚዎች ቁጥር ካለው የባለሙያ ቁጥር አንጻር ትንሽ የሚባል ባይሆንም፣ ህክምናውን ማግኘት ካለባቸው ታካሚዎች አንጻር ግን አነስተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ህክምናው አጭር በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚሰጥ አለመሆኑ ከሌሎች የህክምና ሂደቶች የተለየ እንደሚያደርገው ያነሱት ዶ/ር አካሉ፤ የሥነ ልሳን ህክምና ለውጡ በጊዜ ሂደት ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ታካሚዎች ረዘም ላለ ጊዜ ህክምናቸውን እንደሚከታተሉ ገልጸዋል፡፡

በሆስፒታሉ የሚሰጠው አገልግሎት ውጤታማ ነው በማለት የገለጹት ዶ/ሩ፣ ታካሚዎች በተሻለ ፍጥነት ለውጥ ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ የቤተሰብ ክትትል ወሳኝ መሆኑን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129558
በአቪዬሽን ሳይንስና በኤሮስፔስ ኢንጅነሪግ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፣የኢትዮጵያ አየር ሃይል ፣የጅማ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በአቪዬሽን ሳይንስና በኤሮስፔስ ኢንጅነሪግ ዘርፍ አብረው በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል ።

ስምምነቱ የቴክኖሎጅ ልህቀት ማሳደግ በሚችሉ የአቪዬሽን ሳይንስና የኤሮስፔስ ኢንጅነሪግ ዘርፍ የሚጠይቀውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በጋራ ለማፍራት ያለመ ነው።

ብቁና የሰለጠነ የሰው ሃይል ይዞ እየሰራ የሚገኘው የጅማ ዩኒቨርሲቲ እንደሆነም በስምምነቱ ላይ ተጠቅሷል።

ከሁሉም ተቋሞች የተወጣጣ አስራ ሁለት አባላትን ያካተተ ቴክኒካል ኮሚቴ ተመርጧል። ስምምነቱን ተግባራዊነት እየመራና የአፈፃፀም ሂደቱን እየተከታተለ ለተቋማቱ የበላይ ጠባቂዎች የሚያሳውቅ እንደሆነ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተቋምን የሚያሻግርና ትውልድን የሚጠቅም መሠረት ያለው የቴክኖሎጅ ልህቀት የሚሸጋገርበት ተቋም ለመገንባት በስምምነቱ ኃላፊነት የተጣለባቸው አካላት ዘመኑን የዋጄ ታሪክ ሰርተው ለትውልድ እንዲያስረክቡ ተጠይቋል።

ሰኔ 02 ቀን 2016 ዓ.ም 
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️