Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአቪዬሽን ሳይንስና በኤሮስፔስ ኢንጅነሪግ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፣የኢትዮጵያ አየር ሃይል ፣የጅማ ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በአቪዬሽን ሳይንስና በኤሮስፔስ ኢንጅነሪግ ዘርፍ አብረው በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል ።

ስምምነቱ የቴክኖሎጅ ልህቀት ማሳደግ በሚችሉ የአቪዬሽን ሳይንስና የኤሮስፔስ ኢንጅነሪግ ዘርፍ የሚጠይቀውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በጋራ ለማፍራት ያለመ ነው።

ብቁና የሰለጠነ የሰው ሃይል ይዞ እየሰራ የሚገኘው የጅማ ዩኒቨርሲቲ እንደሆነም በስምምነቱ ላይ ተጠቅሷል።

ከሁሉም ተቋሞች የተወጣጣ አስራ ሁለት አባላትን ያካተተ ቴክኒካል ኮሚቴ ተመርጧል። ስምምነቱን ተግባራዊነት እየመራና የአፈፃፀም ሂደቱን እየተከታተለ ለተቋማቱ የበላይ ጠባቂዎች የሚያሳውቅ እንደሆነ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተቋምን የሚያሻግርና ትውልድን የሚጠቅም መሠረት ያለው የቴክኖሎጅ ልህቀት የሚሸጋገርበት ተቋም ለመገንባት በስምምነቱ ኃላፊነት የተጣለባቸው አካላት ዘመኑን የዋጄ ታሪክ ሰርተው ለትውልድ እንዲያስረክቡ ተጠይቋል።

ሰኔ 02 ቀን 2016 ዓ.ም 
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ዛሬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጋር በመሆን በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ በቤተክርስቲያኒቱ የሚገነባ ህንፃ የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠናል።

ቤተ ክህነት የከተማውን ልማት ሥራ በላቀ ሁኔታ በመደገፍ እና ለኮሪደር ልማት ስራዎች መጀመር፤ በማፍረስ ሂደትም ሆነ መልሶ በመገንባት ሂደት እንዲሁም ህንፃዎችን በማደስ ላደረገችው ተሳትፎ እና ተግባራዊ የሆነ ምላሽ ከልቤ ለማመስገን እወዳለሁ።
በዚህ አጋጣሚ ከቤተክርስቲያንቱ ለቀረበልኝ ምስጋናም እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ

ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓም
ኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ካላቸው የእስያ ሀገራት ምን ትቀስማለች?
***
(ኢ ፕ ድ)

ሀገራት እንደሚከተሉት ፖሊሲ እና ስተራቴጂ የኢኮኖሚ እድገት ደረጃቸው ይለያያል፡፡ የሀገራት የማያቋርጥ ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ሀገራቱ በኢኮኖሚ ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ ለዜጎች ምቹ ሀገር ከመፍጠር አኳያ ትልቅ ድርሻ እንዳለው የዘርፉ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡

ከእስያ ሀገራት መካከል በተለይ አራት ሀገራት ተከታታይ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ “እስያ ታይገርስ” የሚል ስያሜ በማግኘት ይታወቃሉ፡፡ ሀገራቱ ሆንግ ኮንግ፣ ሲንጋፖር (ቻይና) ፣ታይዋን እና ደቡብ ኮሪያ ናቸው፡፡

ሀገራቱ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የጀመሩት እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1960 ጀምሮ ሲሆን ከዚያ በፊት ኋላቀርና ኢኮኖሚያቸውም እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

እነዚህ ሀገራት በፖሊሲያቸው ያላቸውን እና የሌላቸውን ሀብት በመለየት የወጪ ንግድን መሠረት ያደረገ የኢንዱስትሪ አብዮት አካሂደዋል፡፡ የትምህርት ጥራት ላይ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ እድገት ትኩረት ሰጥተው ሠርተዋል፡፡ በዚህም የማያቋርጥ እድገት እያስመዘገቡ በመቀጠል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በማደግ ላሉ ሀገራት ጥሩ አርአያ መሆን መቻላቸውን.....

https://press.et/?p=129624
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

የቀደሙትን የኮሪደር ልማት ስራዎች ግምገማ ስናጠናቅቅ ቀጣዩን ግምገማችንን በስራው ስፍራ ተገኝተን እንደምናካሂድ ቃል ገብተን ነበር። የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር ስራ በተያዘው የሶስት ወር መርሃግብር ማጠናቀቃችንን ስገልፅ ደስታ ይሰማኛል።

በቀጣይ ስራ ሀብት ቁጠባ ቀዳሚ ትኩረት ሆኖ በቀሪ ኮሪደሮች ስራዎቻችን ፈጣን እና ፈጠራ መር ልንሆን ይገባል። ጥራትን ማስጠበቅ እና ለዜጎቻችን ሁሉ የተመቸ ከባቢን መፍጠር ቅድሚያ የምንሰጣቸው ተግባራት ናቸው።

ይህ ፕሮጀክት የሚራመደው በብዙሃን ትብብር ነው። ከጅማሮው በስራችን ባገኘነው በጎፈቃድ ምስጋና አቀርባለሁ። ይህም በእቅድ እና አፈፃፀም ላይ የታየውን ጥረታችንን እና መልካም ፈቃዳችንን የመጠነ ሆኖ ታይቷል።

በዚህ ከተማችንን ለተሻለ ለውጥ ለማብቃት በተደከመበት ታላቅ ስራ ሂደት ውስጥ በዜጎቻችን ላይ ፈጥረነው ሊሆን ለሚችል አለመመቸት ይቅርታ እንጠይቃለን። ኢትዮጵያችን እንድትለወጥ በፅናት እንደምንሰራ በዚህ የኮሪደር ልማት ስራ ሂደትም ያሉ የዲዛይን እና የጥራት ክፍተቶችም ካሉ ማስተካከል እንደምንቀጥል እንድትተማመኑ ለመግለፅ እፈልጋለሁ።

በግሉ ዘርፍ ያሉ አጋሮቻችንን ጨምሮ ትናንት ምሽት በጎዳናዎች ፍቅራችሁን ለገለፃችሁልን፤ በአጠቃላይም በዚህ ስራ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓም