ኢትዮጵያ በማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማትን ሐዘን ገለጸች
*************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎችን ሕይወት በቀጠፈው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገለጸች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው የሐዘን መግለጫ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ለማላዊ መንግሥትና ሕዝብ የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
የማላዊ መከላከያ ኃይል አውሮፕላን የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎችን አሳፍሮ ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡
ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓም

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) 100 ቀናት እና የሁለተኛው ሀገር በቀል ኢኮኖሚ አፈጻጸም እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ባቀረቡት ሪፖርት‼️
👉 ባለፉት አሥር ወራት የ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል፣
👉 ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 ነጥብ 3 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፣
👉 መንግሥት 425 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰብስቧል፣ 271 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰበሰበ ነው፣
👉 ከሸቀጦች የወጪ ንግድ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር፤ ከሬሚታንስ 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል፣
👉 የመንግሥት የበጀት ጉድለትም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ14 በመቶ ቀንሷል፣
👉 ለ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች በሀገር ውስጥ፤ ለ300 ሺህ ለሚሆኑት በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፣
👉 በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ኢትዮጵያ የ7 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ታሰመዘግባለች፣
ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129734

በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች የተገኙ ውጤቶች መንግሥት በተግባር እየፈጸመ መሆኑን ያመላክታሉ - አቶ አደም ፋራህ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች የተገኙ ውጤቶች መንግሥት ቃልን በተግባር እየፈጸመ መሆኑን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ገለፁ።
የበጀት ዓመቱ የመጨረሻው የ100 ቀናት የአፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ፤ ግምገማውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸው፤ ገዥው ፓርቲ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማሳካት ለሕዝብ ቃል የገባቸው ግቦች እንደነበሩት አስታውሰዋል።
በፓርቲው ማኒፌስቶ የተቀመጡ ግቦችን በተግባር ዕውን ለማድረግ የዘንድሮውን ጨምሮ በየጊዜው የአፈጻጸም ግምገማዎች እንደሚደረጉ ጠቁመው፤ በግምገማው ቃልን በተግባር ማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል።
ለአብነትም መንግሥት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከአፍሪካ ግዙፍ አምስት ኢኮኖሚዎች አንዱ የማድረግ ግብን ለሕዝብ በይፋ ማሳወቁን አስታውሰው፤ ይህንንም ቃል በተግባር ማረጋገጥ መቻሉን ነው የገለጹት።
የጥቅል አገራዊ ምርትን በአጭር ጊዜ 205 ቢሊየን ዶላር በማድረስ በእጥፍ ማሳደግ መቻሉን እንዲሁም በነፍስ ወከፍ ገቢም ዕድገት መምጣቱን ጠቅሰዋል።
በግብርናው ዘርፍ ከ3 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ በማልማትና 100 ሚሊየን ኩንታል ምርት በመጨመር ምርታማነትን ማሳደግ ስለመቻሉ ገልፀዋል።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ጨምሮ በዘርፉ በተሰሩ ሥራዎች ነባር ኢንዱስትሪዎች ወደ ሙሉ አቅማቸው እንዲሸጋገሩና አዳዲስ አልሚዎችም ወደማምረቻው ዘርፍ እንዲገቡ ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል።
በቱሪዝም ዘርፍና በማዕድን ዘርፎች ያሉ ዕምቅ ጸጋዎችን የመለየትና የማልማት ሥራዎችም ትልልቅ ኩባንያዎች በዘርፉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በማስቻል ለአገር ብልጽግና የሚበጁ ተግባራት መከናወናቸውንም አንስተዋል።
በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍም የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸውን በአጠቃላይ ግምገማዎቹ ቃልን በተግባር ለማረጋገጥ ጥረቱ መቀጠሉን አመላካች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በአጠቃላይ በኢኮኖሚውና በሌሎች ዘርፎች እንደ አገር የተገኘው እመርታ መንግሥት ቃልን በተግባር እየፈጸመ መቀጠሉን በግምገማው የተገኙ ስኬቶች ማሳያ መሆናቸውን ነው አቶ አደም የተናገሩት።
ሌላው መንግሥት በየጊዜው በሚደረጉ ሕዝባዊ ስብሰባዎች የሚነሱ የሕዝብ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን በመለየት የመፍታት ቃል አንዱ ቁልፍ ጉዳይ እንደነበር ገልጸው፤ በዚህም ተጨባጭ ለውጦች መገኘታቸውን ተናግረዋል።
ለአብነትም ዓለም አቀፍ ችግር የሆነውን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል በግብይት ሥርዓቱ ላይ በተከናወኑ ተግባራት የዋጋ ንረትን ወደ 23 በመቶ መቀነስ መቻሉን ጠቅሰዋል።
በሥራ ዕድል ፈጠራ ረገድም በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ ለ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች አዳዲስ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር መቻሉን አንስተዋል።

አርቲስት ይገረም ደጀኔ የአይን ብሌኑን ለኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ ለመለገስ ቃል ገባ
የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የደም ለጋሾች ቀን ቋሚ ደም ለጋሾችን በማመስገን ይከበራል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
20ኛው የደም ለጋሾች ቀን ፈቃደኛ ደም ለጋሾችን በማመስገን ከሰኔ 7 ጀምሮ እስከ 22 ቀን 2016 ዓም በተለያዩ መርሃግብሮች እንደሚከበር የኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታወቀ።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አሸናፊ ታዘበው(ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፣ ጥራቱ የተጠበቀ የደም አቅርቦት የበርካታ እናቶች ህፃናትና የወጣቶችን ህይወት ያድናል።
ጠንነቱ ስለተጠበቀ የደም አቅርቦትና አስፈላጊነት ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ይሰጣል ያሉት አሸናፊ ታዘበው(ዶ/ር) ቋሚ የደም ለጋሾች የማበረታታትና ጤንነቱ የተጠበቀ የደም አቅርቦት እንዲኖር እየሰራ ይገኛል።
የአገልግሎቱ አምባሳደር የሆነው አርቲስት ይገረም ደጀኔ በበኩሉ፤ ደም መለገስ ብዙ ግዜ የማይፈጅና የጤና ጉዳት የማያደርስ በጎ ተግባር ነው ሲሉ ገልፀዋል።
አንድ ሰው ደም ለግሶ በተወሰነ ደቂቃዎች ወደ ስራው መመለስ ይችላል። በተቃራኒው ደግሞ በርካታ ሰዎች በደም እጦት ህይወታቸው ያልፋል። በመሆኑም ማህበረሰቡ በቋሚነት ደም የመለገስ ልምድ ሊያዳብር ይገባል ብለዋል።
አርቲስት ይገረም ደጀኔ የአይን ብሌኑን ለኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ለመለገስ ቃል ገብቷል።
በአመለወርቅ ከበደ

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን ለመተግበር በአዋጁ የተጠቀሱ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑን የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የበጀት ዓመቱ የመጨረሻው የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። በዚህም መሰረት የፍትህ ሚኒስቴር የበጀት ዓመቱ የመጨረሻዎቹ 100 ቀናት የህግና ፍትህ ሥርዓቱ ያለበት አፈፃፀም ተገምግሟል፡፡
የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) በግምገማው የሽግግር ፍትህ መጽደቅና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። የሽግግር ፍትህ ፖሊሲውን ለማዘጋጀት ጥናቶች፣ ምክክሮችና የባለድርሻ አካላትን የነቃ ተሳትፎ አካቶ የጸደቀ መሆኑን ተናግረዋል።
ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ መውጣቱን ገልጸው በፖሊሲው የተመላከቱ ተቋማትን ማቋቋም የሚያስችሉ የሥነ ስርዓትና ፍሬ ነገር ህጎች እየተዘጋጁ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የፍትህ ዘርፉን ለማሻሻል በፌደራልና በክልል ደረጃ ገቢራዊ የሚደረጉ ሀገር አቀፍ ህጎችና አሰራሮች መውጣታቸውን ጠቅሰው፣ የአስተዳደር ሥነ ስርዓት አዋጅን ማስተግበር፣ የወንጀል ሥነ ስርዓት አጽድቆ ገቢራዊ ማድረግም በትኩረት እየተከናወነ ነው ብለዋል።
የማህበረሰብ ተኮር የፍትህ አገልግሎት ወይም ባህላዊ ፍርድ ቤትን የተመለከተ ሞዴል ህግ ተዘጋጅቶ ለክልሎች ተልኳል ሲሉም ጠቁመዋል።
የዲጂታላይዜሽን አሰራር፣ የፍትህ ዘርፉን አመራርና ባለሙያዎች ለማጥራት የተከናወኑ ተግባራት በጥንካሬ የሚወሰዱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም የፍትህ ስርዓቱን በማሻሻል የዜጎችን ተጠቃሚነት ማጎልበት የሚችሉ ማህበረሰብ ተኮር የፍትህ አገልግሎት ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል፡፡
የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅን በሁሉም ክልሎች ገቢራዊ ማድረግ የወንጀል ፍትህ ስርዓቱን ማሻሻል የቀጣይ የትኩረት መስክ መሆኑንም ገልጸዋል ሲለ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በክልሉ የተከናወኑ የግብርና ስራዎችን አሰመልክተው ለኢፕድ በሰጡት ማብራሪያ ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች‼️
👉 ከ10 ሚሊየን ሄክታር የማያንስ ሊታረስ የሚችል መሬት አለ፤
👉 ከዚህ ውስጥ ከለውጡ በፊት ሲታረስ የነበረው ወደ 400ሺ ሄክታር ወደ 900 ሺ ሄክታር ማልማት ተችሏል፣
👉 ተጨማሪ 50ሺ ሄክታር በማልማት በአጠቃላይ ወደ 1 ሚሊዮን ሄክታር ለማሳደግ ይሰራል፣
👉 በክልሉ የተለያዩ ሰብል አይነቶችን ጨምሮ ይመረት የነበረው በዓመት ከ10 ሚሊዮን ኩንታል የማይበልጥ ነበር፣
👉 በአሁኑ ጊዜ ወደ 26 ሚሊዮን ኩንታል የተለያዩ ምርቶችን ማምረት ተችሏል፣
👉 በዘንድሮ ዓመት በጎዴና ሲቲ ዞኖች በ3 ሺ ሄክታር ላይ የሩዝ ምርት ለማምረት በሙከራ ደረጃ እየተሠራ ነው፣
👉 በፌደራል መስኖ እና ቆላማ ሚኒስቴር ድጋፍ ከስምንት ቢሊየን ብር በላይ የመስኖ ፕሮጀክቶች ተጀምረዋል፣
👉 ከግብርናው ጋር ተያይዞ በእንስሳት ሃብትም በጣም ጥሩ እምርታ እየታየ ይገኛል፣
👉 የእንስሳት ኳራንቲን ማዕከላትን ሠርቶ እንስሳት ለውጭ ገበያ እንዲቀርቡ ከማድረግ አንጻር ተግዳሮቶች አሉ፣
ርዕሰ መስተዳድሩ ከኢፕድ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129495

መንግሥት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተግባራዊ በማድረግ ብዙ ርቀት ተጉዟል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ፣ የመሠረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባትና በጀት በመመደብ የሰላም ስምምነትን ተግባራዊ በማድረግ ብዙ ርቀት መጓዙን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ፓርቲ አባል ኮማንደር ገብረመስቀል ገብረሚካኤል ገለጹ።
የትዴፓ ፓርቲ አባል ኮማንደር ገብረመስቀል ገብረሚካኤል ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤መንግሥት የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ ርቀት ተጉዟል።
በትግራይ ክልል የሰብዓዊ አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ፣ የመሠረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት፣ በጀት በመመደብ፣ የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግና ሌሎች ሥራዎችን በማከናወን የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ተፈጻሚ እንዲሆን ብዙ ረቀት ተጉዟል።
በፌዴራል መንግሥት እና በሕወሓት መካከል የተደረገውን የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ተከትሎ መንግሥት ብዙ አወንታዊ ሥራዎች በክልሉ ሠርቷል ያሉት ኮማንደር ገብረመስቀል፤አሁንም መንግሥት ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129817

በአንድ ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግና ትሬዲንግ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከአንድ ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
ኩባንያ ከጤፍ የተለያዩ ስናኮችንና ደረቅ የምግብ ዓይነቶችን በማምረት ወደ አውሮፓ፤ አሜሪካና የሩቅ ምስራቅ ሀገራት ኤክስፖርት እንደሚያደርግ ተገልጿል።
የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም፣ ባለፉት 3 ዓመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለመጨመር የሚያስችሉ የተለያዩ ሪፎርሞች ተተግብረዋል።
ኮርፖሬሽኑ ሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም፤ የኮርፖሬት ሀብት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አለማየሁ ሰይፉ እና የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ቤተልሄም ጥላሁን ጋር በጋራ አስቀምጠዋል።
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም

በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ 18 ነጥብ 5 ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኞች ይተከላሉ
***************
(ኢ ፕ ድ)
አማራ ክልል በ2016/17 የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር 18 ነጥብ 5 ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ክልሉ ለ2016/17 የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል።
አማራ ክልል በ2016/17 የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አንድ ነጥብ 59 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል አቅዶ እየሠራ መሆኑን ገልጸው፤ እስካሁን አንድ ነጥብ 34 ቢሊዮን ችግኞችን ለተከላ ዝግጁ በማድረግ የእቅዱን 76 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታውቀዋል።
የሚተከሉት ችግኞች ፍራፍሬ፣ ለደን ሽፋን፣ ለምግብነትና የአፈር ለምነትን የሚጨምሩ እንዲሁም ለአካባቢ ጥበቃ የሚያገለግሉ የዛፍ ዝርያዎች መሆናቸውን አስረድተዋል። አጠቃላይ ከሚተከሉት አንድ ነጥብ 59 ቢሊዮን ችግኞች መካከል 18 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑት.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129829

በወላይታ ዞን በዘንድሮ ዓመት 162 ሺህ ኩንታል እሸት ቡና ተሰብስቧል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ከመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ 162 ሺህ ኩንታል እሸት ቡና መሰብሰቡን የዞኑ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽህፈት ቤት ገለጸ። ከዞኑ ስድስት ሺህ ኩንታል የቡና ምርት ለውጭ ገበያ መቅረቡን ተጠቁሟል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ካውሌ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጀት እንደገለጹት፤ በዘንድሮ ዓመት የምርት ዘመን ከዞኑ 162 ሺህ ኩንታል እሸት ቡና ተሰብስቧል።
የዞኑን የቡና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ የግብርና ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው፤ አምራች አርሶ አደሮች ጥራት ያለው ቡና እንዲያዘጋጁ የሚረዱ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።
ከቡና ወጪ ንግድ ጋር በተያያዘ ከዞኑ ስድስት ሺህ ኩንታል ምርት ለውጭ ገበያ መላክ ተችሏል ሲሉ አስረድተዋል።
ከዓለም የቡና ገበያ መውረድ ጋር ተያይዞ የዞኑ የቡና ገበያም የመቀነስ አዝማሚያ እንዳለው አመላክተው፤ በቀጣይ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ ወደተለያዩ......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129825