Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ባለፉት አስር ወራት ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በሀገር ውስጥና በውጭ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል - ሙፈሪያት ካሚል
*********************
(ኢ ፕ ድ)

በ2016 በጀት ዓመት ያለፉት አስር ወራት ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በሀገር ውስጥና በውጭ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ።

ሚኒስትሯ እንደተናገሩት፤ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ለሥራ የሚሰማሩ ዜጎች ተፈላጊውን ክህሎት እንዲጨብጡ የማብቃት ተግባር ትኩረት ተሰጥቶታል።

በተለይም የሰለጠነ የሰው ኃይል ወደ ውጭ ለማሰማራት አስፈላጊው ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው፥ ስልጠና ከመስጠት ባለፈ ብቁ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል።

እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ በበጀት ዓመቱ አስር ወራት 314 ሺህ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ሆነዋል።

የሥራ ስምሪቱ ዜጎች ደህንነታቸው፣ የሚያገኙት ጥቅምና መብታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ በሚያስችል መልኩ መከናወኑንም አብራርተዋል።

በሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው በጥቅሉ ለ3 ሚሊዮን 77 ሺህ ዜጎች የሀገር ውስጥና የውጭ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ እንዳሉት የዲጂታል ሥርዓት በመዘርጋት ዜጎች ተመዝግበው ወደ ሥራ ገበያው እንዲገቡ ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ላይም በትኩረት እየተሰራ ነው።

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍም ወጣቶች ያላቸውን የፈጠራ ሀሳብ ወደ ቴክኖሎጂ ምርት መቀየር የሚችሉበት ስልጠና እና ምቹ ምህዳር መፈጠሩንም አክለዋል።

በዚህም የስራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶችን በማወዳደር ምርቶቻቸውን ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት እንዲጠቀሙ በተጀመረው ሂደት 76 ቴክኖሎጂዎች ወደ ምርት መሸጋገራቸውን አብራርተዋል።

ስታርትአፖችና ኢንተርፕራይዞችን በማጎልበት ተጨማሪ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ በመንግስት ትኩረት መደረጉን አስረድተዋል።
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ የደህንነት ስጋት እንደሌለበት በኦዲት ተረጋግጧል
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አስራት ቀጄላ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ ዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዘርፍ ከ12 አመት በኋላ የመጀመሪያውን የአቪዬሽን ደህንነት ማረጋገጫ ኦዲት ሰርቷል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት አየር ማረፊያዎች ምንም አይነት የደህንነት ችግር እንደሌለባቸው አረጋግጧል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ያመለክታል። በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርፖርቶች በተደረገላቸው ዳሰሳ ጥሩ ውጤት አግኝተዋል።

ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ምንም አይነት የአቪዬሽን ስጋት የለባትም ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ይህም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ውጤት ነው። አየር መንገዱም የኢትዮጵያና የአፍሪካ ኩራት ሆኖ እንዲቀጥል ይረዳዋል ብለዋል።

ውጤቱ አየር መንገዱ በቀላሉና ያለ ምንም የቅድመ ደህንነት ፍተሻ የበረራ አድማሱን ለማስፋት ይረዳዋል። ሌሎች አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለመስራት ትልቅ እድል ይከፍታ።

በኦዲት የተገኘው የአቪዬሽን ደህንነት ውጤት የቱሪዝም ፍሰቱን ያሳድገዋል። የኢትዮጵያን ገጽታም ለመገንባት ይረዳል።

የተሰጡ አስተያየቶች በቀላሉ የሚስተካከሉ ናቸው ያሉት ዳይሬክተሩ፣ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር በቅርቡ ማስተካከያ ይደረግባቸዋል ብለዋል።

በቀጣይም የአቪዬሽን ዘርፉን ተመራጭ ለማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ሞገስ ጸጋዬ
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ከ7 ቢሊዩን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል
********************
(ኢ ፕ ድ)

በዘንድሮው አመት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም 7 ነጥብ 5 ቢሊዩን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው አመት በአንድ ጀምበር በሚደረገው ችግኝ ተከላ መርሐግብርን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ዝግጀት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል።

ከሚተከሉ ችግኞች 43.9 በመቶ የደንና የውበት እንዲሁም 56.1 በመቶ የጥምር ደን መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

ከ800 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ችግኝ የሚተከልባቸው ቦታዎችን በጂኦሪፈራንስ እንዲለዩና ካርታ እንዲወጣላቸው ማድረግ እንደተቻለ አብራርተዋል፡፡

በዘንድሮው አመት በአንድ ጀምበር በሚደረገው ችግኝ ተከላ መርሐግብር በርካታ ችግኞችን በመትከል በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ዝግጀት እየተደረገ መሆኑን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የተፈጥሮ ሃብት መመናመንና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ በመከላከል የግብርናውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ዘላቂነት ያለው አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የአረንጓዴ አሻራ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡

በአንደኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በአጠቃላይ 20 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ መላውን ህብረተሰብ በተደራጀ ሁኔታ በማነቃነቅ 25 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ተችሏል።

ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም
የሀረር ኢኮ ፓርክ ግንባታ ስራ 92 በመቶ ተጠናቋል- አቶ ተወለዳ አብዶሽ ባህል ፣ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በሀረር ከተማ ከመደመር ትውልድ መፅሃፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ እየተገነባ የሚገኘው የሀረር ኢኮ ፓርክ ግንባታ 92 በመቶ መጠናቀቁን የሀረሪ ክልል ባህል ፣ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ገለፁ፡፡

ፓርኩ በውስጡ ሀረር የምትታወቅበትን የጅብ ትርኢት ማሳያ አንፊ ቲያትር ጨምሮ የተለያዩ ባህላዊ የእደ ጥበብ ውጤቶች ለቱሪስቶች የሚሸጡበት ማእከላትና የመዝናኛ ስፍራዎችን በውስጡ የያዘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፓርኩ እየተገነባበት የሚገኘው ስፍራ ሀረር የምትታወቅባቸው የተለያዩ እፅዋት የነበሩበት ስፍራ መሆኑን ጠቅሰው፣በስፍራው ይገኙ የነበሩ አትክልትና ቡናን ጨምሮ የተለያዩ መድሃኒትነት ያላቸው እፅዋቶችን መልሶ በማልማት ተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻ ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከመደመር ትውልድ መፅሃፍ ሽያጭ በተገኘ ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ገቢና በክልሉ የሚገኙ ባለሃብቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ የመንግስት ሰራተኞችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እየተገነባ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ፓርኩን ለመገንባት ከሚያስፈልገው 162 ሚሊየን ብር ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሸፈነ መሆኑ ፕሮጀክቱን በክልሉ በመንግስት እየተገነቡ ከሚገኙ ሌሎች ፕሮጀክቶች የተለየ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

የፓርኩ ግንባታ ሲጠናቀቅም ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል ከመፍጠር ባሻገር ለክልሉ የቱሪዝም እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
የአሜሪካን ኤምባሲ ለኤጀንሲው የሐሰተኛ ሰነድ መለያ ቴክኖሎጂ ግብዓት ድጋፍ አደረገ
***
(ኢ ፕ ድ)

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባገኘው ድጋፍ በሐሰተኛ ሰነድ አይነቶች፣ ዝግጅትና ልየታ ለአንድ ወር ሲሰጥ የነበረው የ8 ዙር ስልጠና አጠናቋል።

ኤምባሲው ከ2ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ድጋፍ በተጨማሪ ሃሰተኛ ሰነድ ለመለየት የሚያስችሉ በሃገር ውስጥ በቀላሉ የማይገኙ የአጉሊ መነፅርና የUV ጨረራ የቴክኖሌጂ መሳሪያዎችን ለተቋሙ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተረክበዋል። ለተደረገው የአቅም ግንባታና የቁሳቁስ ድጋፍ በኤጀንሲውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ኤጀንሲው አስታውቋል።

ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም
በኦጋዴን ከ21 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ጋዝ መኖሩ ተረጋገጠ
***
(ኢ ፕ ድ)

በሶማሌ ክልል ኦጋዴን በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ መረጋገጡን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በሶማሌ ክልል ኦጋዴን በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ ተረጋግጧል፡፡

በአካባቢው 19 ጉድጓዶችን በመቆፈር በተደረገ ዳሰሳ 21 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ጋዝ ተገኝቷል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በክልሉ ኦጋዴን አካባቢ ያለውን ሀብት በተገቢው መልኩ ለመጠቀም በስፋት ሥራዎች መሠራታቸውን አብራርተዋል፡፡

በአካባቢው ትልቅ ሀብት እንዳለ መረጋገጡን ያነሱት አቶ ሚሊዮን ፤ በተጨማሪም በኢትዮጵያ በስድስት ቦታዎች ላይ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መኖሩን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129874
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 46 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ አቅርቧል
*****
(ኢ ፕ ድ)
በበጀት ዓመቱ ባለፉት 11 ወራት 46 ሺህ ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አስታወቀ፡፡ በመጪው ክረምት 71 ሚሊዮን የተለያየ ዝርያ ያላቸው የቡና ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ክልሉ ጨምሮ ገልጿል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በክልሉ 46 ሺህ ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ተችሏል፡፡

እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ 67 ሺህ 348 ቶን የቡና ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለመላክ ታቅዶ ባለፉት 11 ወራት 46 ሺህ ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ ተልኳል ያሉት አቶ አስራት፤ የተመረተው የቡና ምርትም ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እንዲሁም ለውጭ ገበያ.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129878
👍1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በክልሉ ከ612 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)

በጋምቤላ ክልል በፌዴራል መንግሥት የተጀመሩ ከ612 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ዘጠኝ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ መሆናቸውን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ገለጹ፡፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ እንደገለፁት፤ የመሠረተ- ልማት ዘርፍ ጥራቱን የጠበቀ ፍትሃዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት ለማረጋገጥ በለውጡ ዓመታት የክልሉ መንግሥት ከፌዴራል መንግሥት ጋር በቅንጅት እየሠራ ይገኛል፡፡ በርካታ የመንገድ፣ የመብራትና የቴሌኮም ማስፋፊያ ተግባራትም ተከናውነዋል፡፡

በመንገድ መሠረት ልማት፣ ጤና ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማትና ሌሎች የኤሰቲ መሠረተ ልማቶችም በሰፊው እንደተሠሩ የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በመንገድ ልማት ዘርፍ አያሌ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

ከለውጡ በፊት የጎሬ-ጋምቤላ የአስፋልት መንገድ ብቻ የነበረ መሆኑን አንስተው፤ በአሁኑ ሰዓት በፌዴራል መንግሥት የተጀመሩ 612 ነጥብ 24 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው ዘጠኝ የመንገድ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129879
በጸጥታ ችግር ምክንያት ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የቡርቂቱ የውሃ ፕሮጀክት ዳግም ወደ ግንባታ ተመለሰ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በጸጥታ ችግር ምክንያት ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የቡርቂቱ የውሃ ግድብ ፕሮጀክት ዳግም ወደ ግንባታ መመለሱን የምስራቅ ቦረና ዞን አስታወቀ።

የኦሮሚያ ክልል የግብርና ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በምስራቅ ቦረና ዞን በጎሮ ዶላ ወረዳ የቡርቂቱ የውሃ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።

የምስራቅ ቦረና አስተዳደር አቶ አብዱራዛቅ ሁሴን በወቅቱ እንደገለጹት፤ በጸጥታ ችግር ምክንያት ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የቡርቂቱ የውሃ ግድብ ፕሮጀክት ዳግም ወደ ግንባታ ተመልሷል።

በክልሉ የፊና ፕሮጀክቶች ውስጥ የሚለሙ በዞኑ አራት የውሃ ግድብ ፕሮጀክቶች አሉ ያሉት አቶ አብዱራዛቅ፤ የቡርቂቱ የውሃ ግድብ የአርሶ አደሩን ከፍተኛ የውሃ ችግር ከመቅረፍ ጎን ለጎን በመስኖ የምግብ ፍጆታውን እንዲሸፍን ውጥን ያለው መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደ አቶ አብዱራዛቅ ገለጻ፤፡ፕሮጀክቱ በ30 ሄክታር ላይ የተቀመጠ ሲሆን ፕሮጀክቱ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የኦሮሚያ መስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ግርማ ረጋሳ በበኩላቸው በክልሉ በፊና ፕሮጀክት ስር 73 የውሃ ግድብ እየተገነቡ መሆኑን ጠቅሰው 12 የሚሆኑት መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

የቡርቂቱ የውሃ ግድብ ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን ማሽነሪ ተሟልቶ ዳግም ወደ ስራ ገብቷል።

አፈጻጸሙ 20 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ(ቦረና)
ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
በከተማችን ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ከሆኑ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ተወያይተናል።
የዛሬው መድረካችን እየተሻሻለ የመጣውን የገዢ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ የመስራት አዲስ የፖለቲካ ባህል መዳበር የበለጠ የሚያጠናክር ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ብቻ ስለከተማችን ሰላም፣ ልማት እና የፖለቲካ ባህል መዳበር ስንመክር ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ምንም እንኳን የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረንም፣ የጀመርነውን ይህን የትብብር ባህል በማጠናከር የጋራ አጀንዳዎቻችን ላይ ለጋራ ሃገር በጋራ መስራታችንን አሁንም እንቀጥላለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ