የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት‼️
የታላቁ ህዳሴ ግድብ መገኛ፣ የንጉስ ሼህ ሆጀሌ ሀገር፣ የወርቋ ምድር ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ገብተናል። በቆይታችንም በክልሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን የምንጎበኝ ይሆናል፡፡ በአሶሳ አውሮፕላን ማረፊያ የሞቀ አቀባበል ላደረጉልን የክልሉ ፕሬዝደንት እና ካቢኒያቸው እንዲሁም የአሶሳ ከተማ ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።
ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓም

የአዲስ አበባ ካቢኔ በሦስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል
****
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ካቢኔ 3ኛ አመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል
👉 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ባሉ የሴትባክ (setback) ፕላን ትግበራ ከመንገድ ያላቸው ርቀት መጠን በካቢኔ ወስኖ ወደ ትግበራ መግባቱ ይታወሳል።
ከዚህ በፊት የተወሰኑ የሴት ባክ ለማስተግበር፤ ሂደቱን ለማሳለጥና አገልግሎቱን ለማፍጠን የቀረቡ በደንብ የተደገፉ ማብራሪያዎችን በጥልቀት ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
👉 የመንገድ ዳር መብራትና መሠረተ ልማቶች ለማስተዳደር የሚችል አስተዳደር ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ደንብ መርምሮ አጽድቋል። በዚህም የመንገድ ዳር መብራቶችና መሠረተ ልማቶች ስንታንዳርዶችን ማውጣት፣ መቆጣጠር እንደ አስፈላጊነቱም በሚወጣው መመሪያ መሠረት ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል።
👉 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አደረጃጀት አሰራር ማሻሻያ ደንብን ካቢኔው መክሮበት አፅድቋል። ከተማዋ ከጊዜው ጋር የሚመጥን የፅዳት አጠባበቅ አጠቃቀምና የቆሻሻ አወጋገድና የተሸከርካሪ የመንገድ አጠቃቀም እንዲሁም የመንገድ ፍሳሽ አወጋገድ ያለአግባብ የመንገድ ላይ የመፀዳዳት ተግባራትን እንዲጠበቁ የሚያደርጉ የህግ ማዕቀፎችና ተጥሰው ሲገኙ ለማስከበር ህገወጥ አሰራሮችን ለመቅጣት የሚያግዙ የህግ ማዕቀፎችን የያዘ ነዉ፡፡

በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ሽኝት ተደረገ
****
(ኢ ፕ ድ)
በካሜሮን ዱዋላ ከተማ በሚደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ሽኝት ተደርጓል፡፡
በሻምፒዮናው ላይ ኢትዮጵያ በ41 የውድድር ዓይነቶች በ34 ሴት እና በ43 ወንድ በድምሩ በ77 አትሌቶች ትሳተፋለች።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፤ አትሌቶቹ አብረው በቆዩባቸው 15 የልምምድ ቀናት እርስ በእርስ ይበልጥ መተዋወቅ መቻላቸውን ተናግራለች፡፡
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደ ኦሎምፒክ ላሉ ውድድሮች መነሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶችን ለማብቃት እያደረገ ያለውንም ጥረት አድንቀዋል፡፡
የልዑክ ቡድኑ ከነገ በስትያ ረቡዕ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ወደ ካሜሮን ዱዋላ ከተማ እንደሚጓዝ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተሠራው ከፍተኛ ፀጥታን የማረጋገጥ ሥራ ክልሉ ወደ ተሟላ ሠላም ተመልሷል
************************
(ኢ ፕ ድ)
በቤኒሻንጉል ክልል የነበረው የሠላም መደፍረስ፣ የፀጥታ ችግርና የደህንነት ስጋት በተደረጉ ከፍተኛ ሰላምና ፀጥታን የማስፈን ሥራዎች ተወግዶ ክልሉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ መመለሱ
ተገለጸ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በፅህፈት ቤታቸው በሰጡት ማብራሪያ እንደገለፁት፤ ጥቅሜ ተነካ በሚሉ ሃይሎች ቀስቃሽነት ተጀምሮ የነበረው ክልሉን የመረበሽ፣ የሕዝቡን ሰላምና ፀጥታ አደጋ ላይ የመጣል ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሮ ዛሬ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል።
እንደ ርእሰ መስተዳድሩ ማብራሪያ የለውጡን መምጣት ተከትሎ ጥቅሜ ይቀራል በሚል ያኮረፉና ወደ ጦርነት ሳይቀር የገቡ ኃይሎች የነበሩ ሲሆን፣ እነዚህ ኃይሎች የፈጠሩት ቀውስ በክልሉ ሰላም እንዲደፈርስ አድርጎ ቆይቷል። ይሁን እንጂ፣ በተከፈለው ውድ መስዋእትነት አሁን በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ሊገኝ ችሏል።
በአሁኑ ሰአት በየትኛውም የክልሉ አካባቢዎች በነፃነት መንቀሳቀስ የሚቻል መሆኑን የገለፁት አቶ አሻድሊ ሀሰን የተወሰኑ ችግሮች ያሉት ከአጎራባች ክልሎች ጋር በሚያዋስኑ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130152

የ70 ዓመታት የውሃ ጥሟን የቆረጠችው ጎዴ ከተማ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ጎዴ በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ አንዱ የሆነው የሸበሌ ዞን ዋና ከተማ ነች።
በዘመነ አጼ ኃይለስላሴ የጦር ሰፈር ተመስርቶባት ቀስበቀስ ወደ ከተማነት የተሸጋግረችው ጎዴ፤ ዛሬ ላይ የንግድ እንቅስቃሴ ከሚታይባቸውና የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የክልሉ ከተሞች አንዷ ለመሆን በቅታለች።
ሕይወታቸውን በንግድ ሥራ የሚመሩ የአካባቢውን እና ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ነዋሪዎችን አቅፋለች።
ያም ሆኖ ግን ይህች ከተማ ጎዴ ከተማ ከተቆረቆረች ጊዜ ጀምሮ በተለይም የንጹህ መጠጥ ውሃ አንገብጋቢ ጥያቄዋን አዝላ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተጉዛለች።
ጎዴ ስትጠማ የኖረችው ከተማዋን ሰንጥቆ የሚያልፈውን የዋቤ ሸበሌ ወንዝ ይዛ መሆኑ ደግሞ ምን ጊዜም ነዋሪዎቿን ሲያስቆጭ የኖረ ጉዳይ ነበር።
ዛሬ የሶማሌ ክልሉ ያገኘውን ሰላም ተከትሎ የልማት ጥያቄያቸው መልስ ካገኘ በርካታ ከተሞች ውስጥ የጎዴ ከተማ አንዷ ለመሆን በቅታለች።
ለጎዴ ከተማ ነዋሪዎች ፈተና ሆኖ ለረዥም ዘመን የኖረው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እልባት በማግኘቱ ነዋሪዎቿ እፎይ ብለዋል።
በከተማዋ ፈጣን እድገትና ለውጥም ደስተኛ ሆነዋል።
ወይዘሮ ነስር መሃመድ በተለይም ከውሃ አንጻር የቀድሞዋን እና የአሁኗን ጎዴ እንዲህ ይገልጿቸዋል። ‹‹ለከተማው ሕዝብ ትልቁ ችግር የመጠጥ ውሃ ነበር።
ከወንዝ የሚቀዳ ድፍርስ ውሃ ስለምንጠቀም ለተለያዩ........
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130151

በኮሪደር ልማቱ ህንፃዎች ታድሰው ከመንገዱ ጥራት ጋር ደረጃቸውን ጠብቀው መታየት ጀምረዋል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በኮሪደር ልማቱ ህንፃዎች ታድሰው ከመንገዱ ጥራት ጋር ደረጃቸውን ጠብቀው መታየት ጀምረዋል ሲሉ ኢፕድ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ አቶ ታደሰ ንጋቱ ደተናገሩት፤ የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ፣ አበባ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲሁም ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የላቀ ሚና ይጫወታል። በዚህም ለረጅም ዓመት ሳይታደሱ የቆዩ ህንፃዎች ታድሰው ከመንገዱ ጥራት ጋር ደረጃቸውን ጠብቀው መታየት ጀምረዋል።
ይህም የአዲስ አበባን የመንገድ ሽፋንና ዘመናዊነት እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰት ያሳድጋል። ከዚህም ባለፈ ህንፃዎች ለዓይን በሚስብ መልኩ መታደሳቸው አዲስ አበባ የዓለም የዲፕሎማሲ መዲና፣ የአፍሪካ ዋና ከተማ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ እንቅስቃሴ.........
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130162

በትግራይ ክልል ከ122 ሺህ በላይ ተማሪዎች የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል ከ122 ሺህ በላይ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ታደሰ ካህሳይ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዛሬ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ነው።
ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥም ተናግረዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ከተፈታኞች መካከል 62 ሺህ 732 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች ናቸው።
ተማሪዎቹ ፈተናውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲወስዱ አስቀድሞ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።
የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ተቆጣጣሪዎች በበቂ ሁኔታ መመደባቸውን ጠቁመው፣ ለፈተናው ሰላማዊነትም የጸጥታ አካላት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል።
ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓም

የባሕርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
****************
( ኢ ፕ ድ)
በባሕርዳር ከተማ የሚገነባውና ለከተማዋ ሁለንተናዊ ለውጥ ትልቅ ድርሻ ያለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ተጀመረ።
ፕሮጀክቱ የ22 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት የሚሸፍን ነው ተብሏል።
በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ የአማራ ክልል እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል።