Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተባበሩት መንግስት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
****
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተባበሩት መንግስት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ዴኒስ ፍራንሲስን ጋር በአለም አቀፍና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያና ተመድ አብረው በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች፣ በአለም አቀፍና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል።

በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ የሀሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን የገለጹት አምባሳደር ነብዩ፣ ኢትዮጵያ ለቀጣናው መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት በተመለከት አድናቆት ችረዋል ብለዋል።

አምባሳደር ዴኒስ ለታዳጊ የሀገራት አጀንዳዎች በተለይ የእዳ ቅነሳና ሽግሽግ፣ የዘላቂ ልማት አፈጻጸም ላይ ለሰጡት ትኩረት አምባሳደር ታዬ ምስጋና ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለተባበሩት መንግስት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ማረጋገጫ መስጠታቸውን ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በተመለተከተ ገለጻ ተድርጎላቸዋል።

በሞገስ ጸጋዬ

ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓም
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት‼️

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መገኛ፣ የንጉስ ሼህ ሆጀሌ ሀገር፣ የወርቋ ምድር ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ገብተናል። በቆይታችንም በክልሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን የምንጎበኝ ይሆናል፡፡ በአሶሳ አውሮፕላን ማረፊያ የሞቀ አቀባበል ላደረጉልን የክልሉ ፕሬዝደንት እና ካቢኒያቸው እንዲሁም የአሶሳ ከተማ ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።

ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓም
የአዲስ አበባ ካቢኔ በሦስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል
****
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ካቢኔ 3ኛ አመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል

👉 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ባሉ የሴትባክ (setback) ፕላን ትግበራ ከመንገድ ያላቸው ርቀት መጠን በካቢኔ ወስኖ ወደ ትግበራ መግባቱ ይታወሳል።

ከዚህ በፊት የተወሰኑ የሴት ባክ ለማስተግበር፤ ሂደቱን ለማሳለጥና አገልግሎቱን ለማፍጠን የቀረቡ በደንብ የተደገፉ ማብራሪያዎችን በጥልቀት ተወያይቶ  በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

👉 የመንገድ ዳር መብራትና መሠረተ ልማቶች ለማስተዳደር የሚችል አስተዳደር ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ደንብ መርምሮ አጽድቋል። በዚህም የመንገድ ዳር መብራቶችና መሠረተ ልማቶች ስንታንዳርዶችን ማውጣት፣ መቆጣጠር እንደ አስፈላጊነቱም በሚወጣው መመሪያ መሠረት ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል።

👉 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አደረጃጀት አሰራር ማሻሻያ ደንብን ካቢኔው መክሮበት አፅድቋል። ከተማዋ ከጊዜው ጋር የሚመጥን የፅዳት አጠባበቅ አጠቃቀምና የቆሻሻ አወጋገድና የተሸከርካሪ የመንገድ አጠቃቀም እንዲሁም የመንገድ ፍሳሽ አወጋገድ ያለአግባብ የመንገድ ላይ የመፀዳዳት ተግባራትን  እንዲጠበቁ የሚያደርጉ የህግ ማዕቀፎችና ተጥሰው ሲገኙ ለማስከበር  ህገወጥ አሰራሮችን ለመቅጣት የሚያግዙ የህግ ማዕቀፎችን የያዘ ነዉ፡፡

ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓም
በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ሽኝት ተደረገ
****
(ኢ ፕ ድ)

በካሜሮን ዱዋላ ከተማ በሚደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ሽኝት ተደርጓል፡፡

በሻምፒዮናው ላይ ኢትዮጵያ በ41 የውድድር ዓይነቶች በ34 ሴት እና በ43 ወንድ በድምሩ በ77 አትሌቶች ትሳተፋለች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፤ አትሌቶቹ አብረው በቆዩባቸው 15 የልምምድ ቀናት እርስ በእርስ ይበልጥ መተዋወቅ መቻላቸውን ተናግራለች፡፡

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደ ኦሎምፒክ ላሉ ውድድሮች መነሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶችን ለማብቃት እያደረገ ያለውንም ጥረት አድንቀዋል፡፡

የልዑክ ቡድኑ ከነገ በስትያ ረቡዕ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ወደ ካሜሮን ዱዋላ ከተማ እንደሚጓዝ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓም
በተሠራው ከፍተኛ ፀጥታን የማረጋገጥ ሥራ ክልሉ ወደ ተሟላ ሠላም ተመልሷል
************************
(ኢ ፕ ድ)
በቤኒሻንጉል ክልል የነበረው የሠላም መደፍረስ፣ የፀጥታ ችግርና የደህንነት ስጋት በተደረጉ ከፍተኛ ሰላምና ፀጥታን የማስፈን ሥራዎች ተወግዶ ክልሉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ መመለሱ
ተገለጸ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በፅህፈት ቤታቸው በሰጡት ማብራሪያ እንደገለፁት፤ ጥቅሜ ተነካ በሚሉ ሃይሎች ቀስቃሽነት ተጀምሮ የነበረው ክልሉን የመረበሽ፣ የሕዝቡን ሰላምና ፀጥታ አደጋ ላይ የመጣል ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሮ ዛሬ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል።

እንደ ርእሰ መስተዳድሩ ማብራሪያ የለውጡን መምጣት ተከትሎ ጥቅሜ ይቀራል በሚል ያኮረፉና ወደ ጦርነት ሳይቀር የገቡ ኃይሎች የነበሩ ሲሆን፣ እነዚህ ኃይሎች የፈጠሩት ቀውስ በክልሉ ሰላም እንዲደፈርስ አድርጎ ቆይቷል። ይሁን እንጂ፣ በተከፈለው ውድ መስዋእትነት አሁን በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ሊገኝ ችሏል።

በአሁኑ ሰአት በየትኛውም የክልሉ አካባቢዎች በነፃነት መንቀሳቀስ የሚቻል መሆኑን የገለፁት አቶ አሻድሊ ሀሰን የተወሰኑ ችግሮች ያሉት ከአጎራባች ክልሎች ጋር በሚያዋስኑ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130152
የ70 ዓመታት የውሃ ጥሟን የቆረጠችው ጎዴ ከተማ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ጎዴ በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ አንዱ የሆነው የሸበሌ ዞን ዋና ከተማ ነች።

በዘመነ አጼ ኃይለስላሴ የጦር ሰፈር ተመስርቶባት ቀስበቀስ ወደ ከተማነት የተሸጋግረችው ጎዴ፤ ዛሬ ላይ የንግድ እንቅስቃሴ ከሚታይባቸውና የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የክልሉ ከተሞች አንዷ ለመሆን በቅታለች።

ሕይወታቸውን በንግድ ሥራ የሚመሩ የአካባቢውን እና ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ነዋሪዎችን አቅፋለች።

ያም ሆኖ ግን ይህች ከተማ ጎዴ ከተማ ከተቆረቆረች ጊዜ ጀምሮ በተለይም የንጹህ መጠጥ ውሃ አንገብጋቢ ጥያቄዋን አዝላ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተጉዛለች።

ጎዴ ስትጠማ የኖረችው ከተማዋን ሰንጥቆ የሚያልፈውን የዋቤ ሸበሌ ወንዝ ይዛ መሆኑ ደግሞ ምን ጊዜም ነዋሪዎቿን ሲያስቆጭ የኖረ ጉዳይ ነበር።

ዛሬ የሶማሌ ክልሉ ያገኘውን ሰላም ተከትሎ የልማት ጥያቄያቸው መልስ ካገኘ በርካታ ከተሞች ውስጥ የጎዴ ከተማ አንዷ ለመሆን በቅታለች።

ለጎዴ ከተማ ነዋሪዎች ፈተና ሆኖ ለረዥም ዘመን የኖረው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እልባት በማግኘቱ ነዋሪዎቿ እፎይ ብለዋል።

በከተማዋ ፈጣን እድገትና ለውጥም ደስተኛ ሆነዋል።

ወይዘሮ ነስር መሃመድ በተለይም ከውሃ አንጻር የቀድሞዋን እና የአሁኗን ጎዴ እንዲህ ይገልጿቸዋል። ‹‹ለከተማው ሕዝብ ትልቁ ችግር የመጠጥ ውሃ ነበር።

ከወንዝ የሚቀዳ ድፍርስ ውሃ ስለምንጠቀም ለተለያዩ........

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130151
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️