Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
የኮሪደር ልማቱ ተጨማሪ ትሩፋት
***************
(ኢ ፕ ድ)
አካባቢው እጅጉን ተቀይሯል። አላፊ አግዳሚውም በየቀኑ እየመጣ ያለውን ለውጥ በአግራሞት መመልከት ከጀመረ ሰንብቷል። እግረኛው ደከም ሲለውም በየመንገድ ዳሩ በተሰናዱ መቀመጫዎች ላይ አረፍ በማለት መንፈሱን ያድሳል። የአካባቢው የማታም ሆነ የቀኑ ድባብ ለየት ያለ ሆኗል።

ለዜጎች የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠትና የአዲስ አበባ ከተማን የአፍሪካ መዲናነት ለማጽናት እየተሠሩ ካሉ ሥራዎች መካከል በተመረጡ የከተማዋ አካባቢዎች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት አንዱ ነው።

በዚህም ልማቱ ከፒያሳ እስከ አራት ኪሎ፣ ከአራት ኪሎ እስከ ቦሌ ድልድይ፣ ከቦሌ ድልድይ በመገናኛ ወደ ሲኤምሲ፣ ከቦሌ ተርሚናል ወደ ጎሮ፣ ከሜክሲኮ ወደ ወሎ ሰፈር፣ እንዲሁም ከእንግሊዝ ኤምባሲ ወደ አራት ኪሎ የሚወስዱ ኮሪደሮችን የሚያጠቃልል ነው።

ከእነኝህም መካከል ከአራት ኪሎ እስከ ራስ መኮንን ድልድይ ያለው መንገድ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል።

በዚህ የኮሪደር መንገድ ቀን ከወጣላቸው ስፍራዎች አንዱ የ100 ደረጃ ነው።ይህ ስፍራ ታሪካዊ ከመሆኑም ባሻገር በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች የሚዝናኑበት ስፍራ ነበር።

ሆኖም ከስፍራው ታሪካዊነት አንጻር በአግባቡ እንዳልተያዘና ያልተገቡ......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130301
አረንጓዴ አሻራ የሱማሌ ክልል በረሃማ አካባቢዎችን ወደ አረንጓዴነት እየመለሰ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የሱማሌ ክልል በረሃማ አካባቢዎችን ወደ አረንጓዴነት እየመለሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በክልሉ በ2016 ዓ.ም ከታቀደው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እስካሁን 80 በመቶ ያህሉ እንደተሳካም ተጠቁሟል፡፡

የሱማሌ ክልል አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አስተባባሪ አቶ መሐመድ ቡሌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በክልሉ እስካሁን ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ይገኛል፡፡

በርካቶች ተሳትፎ አድርገው የሥራ ዕድል ያገኙበት ሲሆን፤ ሰፊው የኅብረተሰብ ክፍል ባከናወነው ሥራም የክልሉ በርሃማ አካባቢዎች ወደ አረንጓዴነት እየተቀየሩ ይገኛሉ፡፡

አስተባባሪው እንዳሉት፤ አካባቢው በረሃማ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የአየር ንብረት ለውጡ፤ የአፈር መሸርሸርና መሰል ችግሮች የነበሩበት ነው፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከተጀመረ ወዲህ በርካታ ችግኞች ተተክለዋል፡፡ በዚህም በርካታ የተጎዱ መሬቶችን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130302
በመስኖ ስንዴ ከ106 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በ2016 የምርት ዘመን በመስኖ ስንዴ ከ106 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኢሳያስ ለማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ፤ በ2016 የምርት ዘመን የመስኖ ስንዴን በሦስት ሚሊዮን ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ለማልማት ታቅዶ ሁለት ሚሊዮን 978 ሺህ 122 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈን ተችሏል፡፡

በዚህም በዘንድሮው የምርት ዘመን በዘር ከተሸፈነው መሬት ውስጥ ሁለት ሚሊዮን 199 ሺህ 402 ሄክታር መሬት በባህላዊ እንዲሁም 741 ሺህ 304 ሄክታሩን በኮምባይነር በመሰብሰብ 106 ሚሊዮን 24 ሺህ 856 ኩንታል ምርት ተገኝቷል ብለዋል።

እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ፤ የመስኖ ስንዴ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፤ ደቡብ-ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ሶማሌ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት ተመርቷል፡፡

በሶማሌ ክልል ከለማው 6 ሺህ 704 ሄክታር መሬት ውስጥ 6 ሺህ 145 ሄክታር......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130311
በ2016 በጀት አመት አስር ወራት የ170 አምራች ኢንዱስትሪዎች የኃይል አቅርቦት ጥያቄ መመለስ ተችሏል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ፕሮጀክት ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን መምራት የሚያስችል ከ2016-2018 ለሶስት ዓመት የሚቆይ እቅድ ወደ ተግባራዊ በመደረጉ የ2016 የአስር ወራት አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል፡፡

በ2014 በጀት 12 በመቶ የነበረው የብድር አቅርቦት መጠን በ2016 ወደ 16 በመቶ ከፍ ማለቱን ጠቁመዋል፡፡

ለላፉት 10 ወራት 710 አዳዳስ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉን፣ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱትሪዎች ሽግግር የተፋጠነ እንደነበር ጠቁመው ከመሠረተ ልማት አንጻርም የመሬት፣ የኃይልና የትራንስፖርት አቅርቦት ውጤት አስመዝግቧል።

በክልል ከተሞች 12 ሺ ሄክታር መሬት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የተላለፉበትና ለ170 አምራች ኢንዱስትሪዎች የኃይል አቅርቦት ጥያቄች ምላሽ መሰጠት መቻሉን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ መረጃ ያመለክታል።

ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓም
በተጎዱ አካባቢዎች ላሉ ህፃናት ትምህርት ለመስጠት ያለመ አለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው
***********************
(ኢ ፕ ድ)
"የአደጋ ጊዜ ትምህርት እና በችግር በተጎዱ አካባቢዎች ላሉ ህፃናት በጨዋታ ላይ የተመሰረተ የመማር አቀራረቦች" በሚል መሪ ሀሳብ አለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ በትምህርት ሚኒስትር የከፍተኛ ትምህርት ዴኤታ አቶ ኮራ ቶሹኔ እንደገለፁት፤ ኮንፍረንሱ በሀገሪቱ ጦርነት ላለባቸው አካባቢዎች ያሉበትን ሁኔታ በማገናዘብ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ነው።

በተጨማሪም ከማስተማር ባለፈ የጨዋታ ትምህርት ስርአት በመፍጠር ከደረሰባቸው የስነልቦና እና አካል ጉዳት እንዲያገግሙ የሚረዳ ነው ብለዋል።

የኮተቤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሀነመስቀል ጠና በበኩላቸው፤ መድረኩ በጦርነት አካባቢ የሚገኙ ህፃናት ከትምህርት ውጪ የሚሆኑበትን ሁኔታ የማስቀረት ያለመ ነው ብለዋል።

ለዚህም በፀጥታ ችግር ያለበት አካባቢ የሚገኙ መምህናንን ስልጠና የመስጠት ስራ እንደሚሰራም ገልጸዋል።

በዚህ ተግባርም ከሀገር ውስጥና ውጭ የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ ዶ/ር ብርሀነመስቀል አስታውቀዋል።

የኮተቤ የትምሀርት ዩኒቨርስቲ ከኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከፕለይማተርስ ኢትዮጵያ የተዘጋጀው የምርምር ኮንፍረንስ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ነው።

በማህሌት ብዙነህ
የኢትዮጵያ የብሪክስ አዲሱ ልማት ባንክ አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ ከተለያዩ አገሮች ድጋፍ ተገኝቷል
- አምባሳደር ነብዩ ተድላ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት:-ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲሱ ልማት ባንክ አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ የፖለቲካ ድጋፍ ከተለያዩ አገሮች ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በሩሲያ የብሪክስ ስብሰባዎችና ተጎዳኝ መድረኮች ላይ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጓን ጠቅሰው የብሪክስ አገራት የብሔራዊ ተወካዮችና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተሳትፎ ማድረጓን ገልጸዋል።

በመድረኩ ኢትዮጵያን ጨምሮ አዳዲስ የብሪክስ አባል አገራት የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ አባል እንዲሆኑ ድጋፍ እንዲሰጣቸው ተቀምጧል ያሉት አምባሳደር ነብዩ ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲሱ ልማት ባንክ አባልነት ጥያቄዎች እንዲፋጠኑ የፖለቲካ ድጋፍ ከተለያዩ አገሮች ተገኝቷል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኩል እንደአገር በብሪክስ ተሳትፎዋ ያላትን የጎላ ሚና ለማሳደግ የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ መቆየቷን ማብራራታቸውን ገልጸዋል።

በመድረኩ ኢትዮጵያን ጨምሮ አዳዲስ አባል አገራት በብሪክስ ውስጥ በተሳለጠ መልኩ ወደ ማዕቀፉ እንዲገቡ ድጋፍ እንዲደረግ የጋራ መግለጫ መሰጠቱን ጠቅሰው ኢትዮጵያን ጨምሮ አዳዲስ የብሪክስ አባል አገራት የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ አባል እንዲሆኑ ድጋፍ እንዲሰጣቸው ተቀምጧል ብለዋል።

ከቻይና ከብራዚል ከደቡብ አፍሪካና ሩሲያ ጋር የተደረጉ የተናጠል ውይይቶች ተደርገዋል ያሉት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲሱ ልማት ባንክ አባል ለመሆን ያቀረበችውን ጥያቄ እንዲፋጠን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል ብለዋል።

በተጨማሪም በሳምንቱ የተካሄደ አንኳር ዲፕሎማሲያዊ ሁነቶችንም አብራርተው ውጤታማ የሁለትዩሽ ውይይቶች መካሄዳቸውን ገልጸዋል።

በማርቆስ በላይ
ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓም
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የ275 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት አፀደቀ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለሁለተኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የ275 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት አዋጅን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 3ኛ ዓመት 33ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ በከተማ ውስጥ በሚገኝ መሬት፤ በመሬት ማሻሻያና በህንጻ ላይ የንብረት ታክስ እንዲሰበሰብ የሚያደርግ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመራ፡፡

በከተሞች ውስጥ ከሚገኘው ሀብት ውስጥ እያደገ የመጣውን የመንግስት የወጪ ፍላጎት በተወሰነ ደረጃ ለመሸፈን የሚያስችል ሃብት ማሰባሰብ እንዲቻል ዘመናዊ የንብረት ታክስ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የምክር ቤት አባል አወቀ አምባዬ (ዶ/ር)፣ የጸደቀውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅን ጨምሮ ሰሞኑን እያጸደቅናቸው የሚገኙ አዋጆች ደሃው ህዝብ ላይ ጫና የሚፈጥሩ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ህብረተሰቡ ችግር ውስጥ ባለበት ሁኔታ ተጨማሪ ክፍያ ማስከፈል አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡

ጫናው የሚበረታው ደሃው ህብረተሰብ ላይ በመሆኑ ባግባቡ ሊታይ ይገባል ብለዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ ስጋት አለኝ ያሉት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ህብረተሰቡ ቤት ለመስራት ከ15 እስከ 20 ዓመታት ከፍሎ ለመጨረስ የሚፈጅ እዳ ገብቶ ነው፡፡

ንብረት ለማፍራት ዕድሜ ልኩን ዕዳ ከሚከፍል ህዝብ ታክስ መሰብሰብ ይከብዳል ሲሉ አዋጁ ባግባቡ እንዲታይ ተጠይቀዋል፡፡

የአዋጁን አጭር መግለጫ ለምክር ቤት አባላት ያቀረቡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤ በአብዛኞቹ የአለም አገራት በከተማና በገጠር በሚገኝ መሬት ላይ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ‹‹የመሬት ታክስ›› በሚል ስያሜ ሲሰበሰብ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

በኢትዮጵያም ከ1937 ዓ.ም ጀምሮ ከንብረት ላይ በተለያዩ መጠሪያዎች መጠነኛ ክፍያ በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ እና የአካባቢና ማህበራዊ ተጽህኖ ግምገማ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡

በዘላለም ግዛው
ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓም
በ224 ሚሊየን ብር ወጪ የተከናወነው የኤረር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሊመረቅ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)

በሀረሪ ክልል በ224 ሚሊየን ብር ወጪ የተከናወነው የኤረር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በመጪው ቅዳሜ ይመረቃል።

ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ከተማ ከሚገባው አጠቃላይ የውሃ መጠን በእጥፍ ይበልጣል ተብሏል። የህዝቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግርን በማቃለል ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑ የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓም