Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

“ሁሉም ለሰላም፣ ሰላም ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን የጎዳና ላይ ሩጫ ከከተማችን ነዋሪዎች፣ ከሚኒስትሮች፣ ከአምባሳደሮችና በከተማች ከሚገኙ የአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮችና ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን ሮጠናል።

ሰላማችንን በጋራ እናጸናለን፣ እናስቀጥላለን!

"ሁሉም ለሰላም ፣ ሰላም ለሁሉም!"

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓም
የ12ኛ ከፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን ይሰጣል - ትምህርት ሚኒስቴር
*****
(ኢ ፕ ድ)

የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የኦንላይን ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ የሚሠራጨው መረጃም ፍጹም ከእውነት የራቀ ሐሰተኛ መረጃ መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም ተማሪዎች ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ዝግጅታቸውን እንዲቀጥሉ ገልጾ፤ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር የሚተላለፉ መረጃዎችን መከታተል እንደሚገባም አሳስበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦንላይንና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ ይገኛል።

ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
#ሀረር_ኢኮ_ቱሪዝም_ፓርክ‼️

ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢና በክልሉ መንግስት የበጀት ድጋፍ የተገነባው የሀረር ኢኮ ቱሪዝም ፓርክ‼️

ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓም