Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ስራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሰገኑ
****
(ኢ ፕ ድ)

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ስራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሰገኑ።

የኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ለከተማዋ ነዋሪ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ከዘመናዊነት ጋር የተቃኘ አሰራርን በመዘርጋትና በማሳለጥ የኢኮኖሚ እድገት ወሳኙን ሚና እንድንወጣ ያስቻለ መሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በሂደቱ በምታደርጉት ተሳትፎ በአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ታሪካዊ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ መሆናችሁን ተረድታችሁ ስራውን በፍጥነት ብቻ ሳይሆን በጥራት እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ ብለዋል።

በታሪክ ሂደት የከተማዋን የሥራ ባህል በቀየርንበት ፤ ቀንና ለሊት በስራችሁበት ጎን ለሥራ ጥራት የምትሰጡት ትኩረት ባህል ሆኖ መቀጠል እንዲችል መስራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

በቦሌ ሳይት በምሽት በሥራ ላይ ለነበሩ ሰራተኞችን የእራት ግብዣ እያደረጉ ያሉትን የአካባቢውን ነዋሪዎች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል ማለታቸውን የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።

ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓም
ሩሲያ በብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ታጠናክራለች
*******
(ኢ ፕ ድ)
ሩሲያ በብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ይበልጥ አጠናክራ ለመቀጠል እንደምትሰራ በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን ተናገሩ።

አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ብሪክስን ከተቀላቀለች ጀምሮ በሚደረጉ ሁነቶች እያደረገች ያለው የነቃ ተሳትፎ የሚደነቅ ነው።

ሩሲያ የተያዘው የፈረንጆች ዓመት የብሪክስ ሊቀመንበር መሆኗን አስታውሰው፤ ጥምረቱን ማጠናከር የሚያስችሉ የተለያዩ ሁነቶችን እያካሄደች መሆኗን ጠቁመዋል።

ለአብነትም በቅርቡ የብሪክስ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የሌሎች ተቋማት ተወካዮች በሩሲያ ሞስኮ ከተማ ስብሰባ መካሄዱን ገልፀዋል። በዚህም ስብሰባ ኢትዮጵያ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጓን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሙያተኞችና ሚኒስትሮች ደረጃ የምታደርገው ተሳትፎ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ እንዲሁም ብሪክስን የሚያጠናክር መሆኑን ነው ያስረዱት።

ኢትዮጵያ በብሪክስ እያደረገች ያለው ተሳትፎ በትብብር ማዕቀፉ ለጋራ እድገት መረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል።

እንደ አምባሳደሩ ገለፃ፤ አባል ሀገራቱ በሚቀይሱት የትብብር አቅጣጫ መሠረት ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች አጋርነቷን ታጠናክራለች።

ኢትዮጵያ የብሪክስ የልማት ባንክ አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ሩሲያ እንደምትደግፍም አረጋግጠዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2006 ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድና ቻይና "ብሪክ" ቡድን የፈጠሩ ሲሆን በ2010 ደቡብ አፍሪካ ቡድኑን በመቀላቀሏ "ብሪክስ" ወደሚለው ስያሜ መጥቷል።

ከዘንድሮ የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ይህንን በመስፋፋት ላይ ያለውን ጥምረት በይፋ ተቀላቅለዋል።

የብሪክስ አባል ሀገራት አሁን ላይ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን የሚሆነውን የዓለም ሕዝብ የሚይዙ ሲሆን፤ ይህም ከአጠቃላይ የዓለም ሕዝብ ቁጥር አንጻር 45 በመቶ ማለት ነው።

የሀገራቱ ምጣኔ ኃብት 28 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር የሚገመት ሲሆን፤ ይህም ከወቅታዊው የዓለም ምጣኔ ኃብት አንጻር ሲታይ 28 በመቶ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና”
#ጽዱኢትዮጵያ #CleanEthiopia

'ጽዱ ጎዳና፣ ኑሮ በጤና' በሚል የተጀመረው ንቅናቄ ለ'#ጽዱኢትዮጵያ' እንደቀጠለ ነው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 54 ሺህ 795 ሜትሪክ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ
******
(ኢ ፕ ድ)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 54 ሺህ 795 ሜትሪክ ቶን የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

አጠቃላይ አቅርቦቱም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃርም የ28 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

እየተሻሻለ የመጣው የቡና ማሳ እንክብካቤ፣ በክልሉ የቡና ቅምሻና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል ሥራ መጀመር፣ የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር መጠናከርና በግብይት ሂደት ያጋጥሙ የነበሩ ማነቆዎችን መፍታት መቻሉ ለምርት ዕድገቱ አስተዋፅኦ ማበርከቱንም አብራርተዋል፡፡

በ2017 የበጀት ዓመትም ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ ለማቅረብ በተሻለ አቅምና ተነሳሽነት መሥራት እንደሚጠበቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቋል።

ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓም
የይቻላል ተምሳሌቷ- ሲምቢጣ
***
(ኢ ፕ ድ)
በህብረ ቀለማት ያጌጡት ባህላዊ መኖሪያ ቤቶችና የአካባቢው ልምላሜ የፈጠሩት ቅንብር ለተመልካች ቀልብን ይስባል። የቲማቲም፣ የሙዝ፣ የሽንኩርት፣ የአቮካዶና ሌሎች ፍራፍሬና አትክልቶች ቀዬውን የተፈጥሮ ውበት መገለጫ አድርገውታል። በሲምቢጣ አካባቢው ሁሉ ተፈጥሮ ተፈጥሮን ይሸታል።

የአካባቢው ውበት እንዲሁ የመጣ አይደለም። ቀድሞ በጎርፍ ትጠቃ የነበረችው ሲምቢጣ ልማት የማይታይባት ሥፍራ ነበረች። አሁን ላይ ታሪኳ ተቀይሯል። ምክንያቱም በቀዬው የሰውና የእንስሳት ሕይወት እንዲሁም ሰብል ሲያጠፋ የነበረው ጎርፍ አሁን ላይ አቅጣጫው ተቀይሮለት ወደ ዲጆ ወንዝ እንዲገባና ለመስኖ ሥራ እንዲውል ተደርጓል።

ከጎርፍ የተላቀቀችው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሃላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ስር የምትገኘው ሲምቢጣ ቀበሌ ለሥራ የተጉ እጆች ይበዙባታል። ትጋት መገለጫቸው የሆኑ አርሶ አደሮቿ ስለሲምቢጣ የቀደመ ታሪክ ሲያነሱ ቀበሌዋ የምትታወቀው በችግር፣ በተረጅነትና በጎርፍ ተጋላጭነቷ ነበር ይላሉ።

ትናንት ብዙዎች የርዳታ እጃቸውን ለመዘርጋት፣ የሴፍትኔት ርዳታ ለማድረስና ጎርፍ ያደረሰውን ጉዳት ለመመልከት ወደ ቀበሌዋ ያመሩ ነበር። ለውጡን ተከትሎ አካባቢው ላይ በተሠሩ የቅንጅት የልማት ሥራዎች ለክልሉ ብሎም ለሀገር እዳ የነበረችው ሲምቢጣ ወደ ምንዳነት ተለውጣለች።

አሁን ላይ ምርጥ ተሞክሮዋን ለመቅሰም፣ የተትረፈረፈ ምርቷን ለመገብየትና ልምላሜዋን ለማድነቅ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች የሚመላለሱባት “የይቻላል ተምሳሌት”.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131862
በመዲናዋ በከተማ ግብርና ከ150 ሺህ ቶን በላይ ምርት ተገኝቷል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በከተማ ግብርና ልማት ከ150 ሺህ ቶን በላይ ምርት ማግኘት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።

ከ690 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ መሆኑም ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አካሌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመዲናዋ የከተማ ግብርና በስፋት እየተሠራ ይገኛል።

በ2016 በጀት ዓመት በ11 ወራት 130 ሺህ 826 ቶን ምርት ለማግኘት ታቅዶ 153 ሺህ 358 ቶን የእንስሳትና እጽዋት ምርት ማግኘት ተችሏል።

ይህ የከተማ ግብርና ልማት ምርት የመደበኛ እና የሌማት ትሩፋትን ያካተተ ሲሆን፤ 110 ሺህ 152 ቶን የሚሆነው ከእንስሳት ምርት እንዲሁም 43 ሺህ 206 ቶን ከእፅዋት ምርት የተገኘ መሆኑን አብራርተዋል።

ከተገኘው የእንስሳት ምርትም 317 ሚሊዮን 862 ሺህ 924 እንቁላል፣ 25 ሚሊዮን 905 ሺህ ሊትር በላይ ወተት፣ አራት ሺህ 955 ቶን የዶሮ ስጋ፣ 329 ሺህ 910 ኪሎ ግራም ማር፣ አራት ሺህ ኪሎ ግራም የአሳ ስጋ እንዲሁም 23 ሺህ 108 ቶን የበሬ፣ የበግና ፍየል ሥጋ ምርት......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131882
በዘንድሮው ክረምት በ214 ሺህ 552 ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ ይተከላል
************************
(ኢ ፕ ድ)
በዘንድሮው ክረምት በ214 ሺህ 552 ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ እንደሚተከል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ደፈረስ ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ በተያዘው መኸር ወቅት 214 ሺህ 552 ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ ይተከላል።

ከአረንጓዴ ዐሻራ ወዲህ በ850 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ መትከል ተችሏል ያሉት አቶ ፍቃዱ፤ በተያዘው ክረምት ወቅት የሚተከል አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ችግኝ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

እስከ አሁንም 106 ሺህ 168 ሄክታር መሬት አዲስ ተከላ መካሄዱን አብራርተዋል።

አቶ ፍቃዱ አክለውም፤ ባለፈው ዓመት አጠቃላይ 833 ሺህ ቶን ምርት ማግኘት ተችሏል ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ በቡና ልማት ሀገሪቱ መጠቀም ያለባትን ያህል መጠቀም ባትችልም ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥሩ መሻሻሎችን.......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131872
በሲዳማ ክልል ከአራት ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የጠጠር መንገድ ተገንብቷል
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ሲዳማ እራሱን ችሎ እንደክልል ከተቋቋመ ወዲህ ከአራት ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ መገንባቱን የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ታምሩ ታፌ እንደተናገሩት፤ ሲዳማ እንደ ክልል ከተቋቋመ በኋላ በተፈጠረው ምቹ አስተዳደራዊ መዋቅር የህብረተሰቡን አንገብጋቢ የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ በትጋት ተሠርቷል።

በዚህም ሲዳማ ክልል እንደ ክልል ከተዋቀረ በኋላ በአራት ዓመታት ውስጥ አራት ሺህ 14 ኪሎ ሜትር ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ በክልሉ መንግሥት ወጪ ተገንብቶ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የቀድሞው የደቡብ ክልል ሳይከፋፈል ሁለገብ የጠጠር መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ፤ በ2004 ዓ.ም የመንገድ መሠረተ ልማት ሥራው ሁሉ አቀፍ ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ፕሮግራም የሚል አደረጃጀት ተፈጥሮለት፣ መዋቅር ተዘጋጅቶለት ወደ ሥራ እንደተገባ ተናግረዋል።

ከ2004 እስከ 2012 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ውስጥ ዛሬ ላይ ሲዳማ እንደ ክልል በተዋቀረበት አካባቢ የተሠራው 339 ፕሮጀክቶችን ያቀፈ ሁለት ሺህ 86 ኪሎ ሜትር መንገድ ብቻ መሆኑን አብራርተዋል።

ሲዳማ እንደ ክልል ከተቋቋመ በኋላ በዘጠኝ ዓመት ውስጥ የተሠራውን የመንገድ መሠረተ ልማት እጥፍ.......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131873
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ሁለት የገበያ ማዕከላት አገልግሎቶች ለ3ኛ ወገን አስተላለፈ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የከተማ አስተዳደሩ በኮልፌና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተገነቡት የገበያ ማዕከላት አገልግሎቶችን ለ3ኛ ወገን ማስተላለፉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢንያም ምክሩ ገልፀዋል።

ለ3ኛ ወገን ተላለፉት አገልግሎቶች የአስተዳደር፣ የጽዳትና የጥበቃ አገልግሎቶች መሆናቸው ተገልጿል። አገልግሎቶቹን ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ የተፈለገው ንግድ ቢሮ የሚያስቀምጠውን የዋጋ ተመን፣ የጽዳና የጥበቃ ሥራዎች ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ነው ተብሏል።

ይህም ሸማቹ ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ያስችላል ያሉት አቶ ቢንያም፤ ሥራው እየተጠናከረ ሲሄድ በከተማዋ የሚታየውን የዋጋ ንረት በእጅጉ ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተመረጡ የመንግስት አገልግሎቶች ለ3ተኛ ወገን ተላልፈው እንዲሰጡ መወስኑ ይታወሳል ያሉት አቶ ቢኒያም፤ በግልፅ ጨረታ ተወዳድረው ላሸነፉ ድርጅቶች በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡ የገበያ ማእከላት የአስተዳደር ስራዎችን ለ3ኛ ወገን አስተላልፋል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩን አገልግሎቶች ለ3ኛ ወገን ያሰተላለፈው ለሀብ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግል ማህበር እና ኢትዮ ጥበቃ አገልግሎት የሶስት ወር የውል ስምምነት የተደረገላቸው መሆኑንም ገልፀዋል።

ከሐምሌ አንድ ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ መጀመራቸው ተገልጿል።

በሳሙኤል ወንደሰን
ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወደምድረ ቀደምት በኢትዮዽያ አየር መንገድ!
በመዲናዋ 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85 ሺህ 219 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀንና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67 ሺህ 903 የሚሆኑት ማለትም 78.9 በመቶ ያህሉ 50 እና በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ አስታውቀዋል።

ተማሪዎች https://aa.ministry.et/#/result ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት እንደሚችሉ ትምህር ቢሮ አስታውቋል።
አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ከተለያዩ ሀገራት ጋር ፓርላሜንታዊ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ውይይት አካሄዱ
******
(ኢ ፕ ድ)
በሩሲያ ሰይንት ፒተርስ በርግ ለብሪክስ አባል ሀገራት በተዘጋጀው ፓርላሜንታዊ ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ከተለያዩ የብሪክስ አባል ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂዷል።

የሁለትዮሽ ግንኙነት ውይይቶችን ከሩሲያ ፌዴሬሽን፣ ከአዘርባጃንና ከኢራን ፓርላማ ልዑክ ጋር አካሄዷል፡፡

ከሩሲያ ፌዴሬሽን ካውንስል አፈ-ጉባዔ ቫሌንቲኖ ኢቫኖቭና ማትቪዮንኮ ጋር በተደረገ ውይይት የሁለቱ ሀገራት ፓርላሜንታዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ተቀራርቦ መሥራት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ፓርላሜንታዊ ግንኙነቶች ለማጠናከር የልምድ ልውውጦች፣ ሥልጠናና ሌሎች ድጋፎችን ማጠናከር እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፓርላሜንት ካውንስል ጋር የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ሐምሌ 05 ቀን 2016 ዓ.ም