Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና”
#ጽዱኢትዮጵያ #CleanEthiopia
#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ጥሪ ስናቀርብ ዜጎቻችን በከፍተኛ ተነሳሽነት በሥራው ተሳትፈዋል። ዋናው አላማችን አካባቢያችንን ሳቢ በማድረግ መፀዳጃ ቤት የመጠቀም ባህላችንን ከመሠረቱ ማዳበር ነበር።

ዛሬ በዜጎቻችን በዋጋ የማይተመን የልብ መዋጮና እምነት የተገነቡትን ሥራዎች በቦታው በመገኘት ገምግመናል።

ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ጠንካራና ዘመን ተሻጋሪ በሆኑ ቁሶች በመጠቀም ደረጃቸውን የጠበቁ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ለመገንባት ቁርጠኝነት ይዘናል።

ይህ የሥራው መጀመሪያ ነው። በእናንተ ያላሰለሰ ድጋፍ የጀመርናቸውን ሥራዎች እናስፋፋለን።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት በቴሌኮም ዘርፍ‼️

👉 4G አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞች 424 ደርሰዋል

👉 462 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች ተገንብተዋል

👉 132 የገጠር የሞባይል ጣቢያዎች ከ2G ወደ 3G አገልግሎት አድገዋል፣

👉 4G አገልግሎት 34 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል፣

👉 በአምስት ከተሞች 5G አገልግሎት ተደራሽ ተደርጓል፣

👉 የሞባይል ኔትወርክ ያልነበራቸውን 216 የገጠር ቀበሌዎች በኔትወርክ ተሳስረዋል፣

👉 የሞባይል ኔትወርክ ተደራሽነት 85 ነጥብ 4፤ በተጠቃሚዎች ከ99 በመቶ በላይ ደርሷል፣

👉 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ሰብስቧል፣

👉 21 ነጥብ 79 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አግኝቷል፣

👉 የደንበኞቹን ቁጥር ከ78 ሚሊዮን በላይ አድርሷል

👉 በቴሌ ብር ከአንድ ነጥብ 8 ትሪሊዮን ብር በላይ አገበያይቷል

👉 የቴሌብር ደንበኞት ቁጥርም 47 ነጥብ 55 ሚሊዮን፣

👉 86 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚያስችል የሞባይል ኔትወርክ ተገንብቷል፣

👉 በዓለም አቀፍ ከሚገኙ 778 የቴሌኮም ኦፕሬተሮች 17ኛ፣ በአፍሪካ ከ195 የቴሌኮም ኦፕሬተሮች 2ኛ ደረጃን ይዟል፣

ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131808
ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች
******
(ኢ ፕ ድ)

ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በፓርላማ በማጽደቅ ስድስተኛ ሀገር ሆናለች፡፡ ከ11 የናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ስድስት ሀገራት በፓርላማ ካጸደቁ ቋሚ የናይል ተፋሰስ ሀገራት ኮሚሽን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግባት ይችላል፡፡

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል ከተፈረመ ቆይቷል፡፡ አምስት ሀገራት በፓርላማቸው አጽድቀው ነበር፡፡

የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ለመመስረት የሚጠበቀው ስድስተኛ ሀገር በፓርላማ እስኪያጸድቅ ድረስ ነበር፤ ደቡብ ሱዳን አጸድቃለች ብለዋል፡፡

ስድስት ሀገራት የናይል ስምምነት ማዕቀፍን ማጽደቃቸው ፋይዳው ከፍተኛ ነው ያሉት አምባሳደሩ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት በሙሉ በሰነዱ ይገዛሉ፡፡ በሐምሌ አንድ ቀን 2016 ዓ.ም የደቡብ ሱዳን በፓርላማ የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በማጽደቅ ስድስተኛ ሀገር ሆናለች፡፡

የናይል ስምምነት ማዕቀፍን ለማጸደቅ ሂደቱ በጣም ከባድ ነበር ያሉት አምባሳደር ነቢል፤ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለፉት ሶስት አመታት ብዙ ትግል አድርጓል፡፡ የደቡብ ሱዳን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከአምስት አመት በፊት ያጸደቀው ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየቱን ገልጸዋል፡፡

በፓርላማ ውስጥ የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር የተገኘ ውጤት ነው፡፡ የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግስት በመሆኑ የሰላም ስምምነቱን የፈረሙ ፓርቲዎችን በሙሉ በማነጋገር የመጣ ነው ብለዋል፡፡ መፈረማቸው ለደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ስድስተኛ ሀገር ሆና የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጽድቃለች ያሉት አምባሰደሩ፤ በቅርቡ የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት ይፈርማሉ፡፡ በመቀጠልም ሰነዱን ለአፍሪካ ህብረት በመላክ ሕጋዊ ሰነድነቱ ይረጋገጣል፡፡

ከደቡብ ሱዳን በፊት የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፈርመዋል፤ይሁንና ወሳኙ ስድስተኛ ሀገር መፈረም በመሆኑ ደቡብ ሱዳን መፈረሟ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ ጉዳዩን የኢትዮጵያ መንግስት የቅርብ ክትትል ያደረገበት በመሆኑ የተሳካ መሆን ችሏል፡፡

ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን መፈረሟ ለኢትዮጵያ ያላትን አጋርነት ያሳያል፡፡ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ነጻነት ከፍተኛ መስዋትነት ከፍላለች፡፡ ደቡብ ሱዳንም አጠቃላይ ለተፋሰሱ ሀገር በተለይ ለላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ያላትን አጋርነት ያረጋገጠችበት ነበር ብለዋል፡፡

ማእቀፉን ያጸደቁ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ዩጋዳንዳ፣ ብሩንዲና ደቡብ ሱዳን ናቸው፡፡

የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት እአአ 2006 የተዘጋጀ ሲሆን የናይል ተፋሰስ አገራት የውሃ ሀብቶችን በትብብር ማልማትና ማስተዳደር የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ያስቀመጠ ነው፡፡ የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ (NBI) የሽግግር ማእቀፍ ሆኖ በዘጠኝ መስራች አባል ሀገራት የጋራ ራእይ የተመሰረተና ቋሚ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን እስከሚመሰረት የሽሽግር ማእቀፍ ሆኖ እንዲያገልገል ታስቦ መቋቋሙ ይታወቃል።

በሞገስ ጸጋዬ

ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ስራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሰገኑ
****
(ኢ ፕ ድ)

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ስራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሰገኑ።

የኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ለከተማዋ ነዋሪ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ከዘመናዊነት ጋር የተቃኘ አሰራርን በመዘርጋትና በማሳለጥ የኢኮኖሚ እድገት ወሳኙን ሚና እንድንወጣ ያስቻለ መሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በሂደቱ በምታደርጉት ተሳትፎ በአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ታሪካዊ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ መሆናችሁን ተረድታችሁ ስራውን በፍጥነት ብቻ ሳይሆን በጥራት እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ ብለዋል።

በታሪክ ሂደት የከተማዋን የሥራ ባህል በቀየርንበት ፤ ቀንና ለሊት በስራችሁበት ጎን ለሥራ ጥራት የምትሰጡት ትኩረት ባህል ሆኖ መቀጠል እንዲችል መስራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

በቦሌ ሳይት በምሽት በሥራ ላይ ለነበሩ ሰራተኞችን የእራት ግብዣ እያደረጉ ያሉትን የአካባቢውን ነዋሪዎች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል ማለታቸውን የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።

ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓም
ሩሲያ በብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ታጠናክራለች
*******
(ኢ ፕ ድ)
ሩሲያ በብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ይበልጥ አጠናክራ ለመቀጠል እንደምትሰራ በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን ተናገሩ።

አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ብሪክስን ከተቀላቀለች ጀምሮ በሚደረጉ ሁነቶች እያደረገች ያለው የነቃ ተሳትፎ የሚደነቅ ነው።

ሩሲያ የተያዘው የፈረንጆች ዓመት የብሪክስ ሊቀመንበር መሆኗን አስታውሰው፤ ጥምረቱን ማጠናከር የሚያስችሉ የተለያዩ ሁነቶችን እያካሄደች መሆኗን ጠቁመዋል።

ለአብነትም በቅርቡ የብሪክስ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የሌሎች ተቋማት ተወካዮች በሩሲያ ሞስኮ ከተማ ስብሰባ መካሄዱን ገልፀዋል። በዚህም ስብሰባ ኢትዮጵያ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጓን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሙያተኞችና ሚኒስትሮች ደረጃ የምታደርገው ተሳትፎ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ እንዲሁም ብሪክስን የሚያጠናክር መሆኑን ነው ያስረዱት።

ኢትዮጵያ በብሪክስ እያደረገች ያለው ተሳትፎ በትብብር ማዕቀፉ ለጋራ እድገት መረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል።

እንደ አምባሳደሩ ገለፃ፤ አባል ሀገራቱ በሚቀይሱት የትብብር አቅጣጫ መሠረት ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ የትብብር መስኮች አጋርነቷን ታጠናክራለች።

ኢትዮጵያ የብሪክስ የልማት ባንክ አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ሩሲያ እንደምትደግፍም አረጋግጠዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2006 ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድና ቻይና "ብሪክ" ቡድን የፈጠሩ ሲሆን በ2010 ደቡብ አፍሪካ ቡድኑን በመቀላቀሏ "ብሪክስ" ወደሚለው ስያሜ መጥቷል።

ከዘንድሮ የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ይህንን በመስፋፋት ላይ ያለውን ጥምረት በይፋ ተቀላቅለዋል።

የብሪክስ አባል ሀገራት አሁን ላይ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን የሚሆነውን የዓለም ሕዝብ የሚይዙ ሲሆን፤ ይህም ከአጠቃላይ የዓለም ሕዝብ ቁጥር አንጻር 45 በመቶ ማለት ነው።

የሀገራቱ ምጣኔ ኃብት 28 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር የሚገመት ሲሆን፤ ይህም ከወቅታዊው የዓለም ምጣኔ ኃብት አንጻር ሲታይ 28 በመቶ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና”
#ጽዱኢትዮጵያ #CleanEthiopia

'ጽዱ ጎዳና፣ ኑሮ በጤና' በሚል የተጀመረው ንቅናቄ ለ'#ጽዱኢትዮጵያ' እንደቀጠለ ነው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 54 ሺህ 795 ሜትሪክ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ
******
(ኢ ፕ ድ)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 54 ሺህ 795 ሜትሪክ ቶን የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

አጠቃላይ አቅርቦቱም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃርም የ28 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

እየተሻሻለ የመጣው የቡና ማሳ እንክብካቤ፣ በክልሉ የቡና ቅምሻና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል ሥራ መጀመር፣ የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር መጠናከርና በግብይት ሂደት ያጋጥሙ የነበሩ ማነቆዎችን መፍታት መቻሉ ለምርት ዕድገቱ አስተዋፅኦ ማበርከቱንም አብራርተዋል፡፡

በ2017 የበጀት ዓመትም ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ ለማቅረብ በተሻለ አቅምና ተነሳሽነት መሥራት እንደሚጠበቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቋል።

ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓም
የይቻላል ተምሳሌቷ- ሲምቢጣ
***
(ኢ ፕ ድ)
በህብረ ቀለማት ያጌጡት ባህላዊ መኖሪያ ቤቶችና የአካባቢው ልምላሜ የፈጠሩት ቅንብር ለተመልካች ቀልብን ይስባል። የቲማቲም፣ የሙዝ፣ የሽንኩርት፣ የአቮካዶና ሌሎች ፍራፍሬና አትክልቶች ቀዬውን የተፈጥሮ ውበት መገለጫ አድርገውታል። በሲምቢጣ አካባቢው ሁሉ ተፈጥሮ ተፈጥሮን ይሸታል።

የአካባቢው ውበት እንዲሁ የመጣ አይደለም። ቀድሞ በጎርፍ ትጠቃ የነበረችው ሲምቢጣ ልማት የማይታይባት ሥፍራ ነበረች። አሁን ላይ ታሪኳ ተቀይሯል። ምክንያቱም በቀዬው የሰውና የእንስሳት ሕይወት እንዲሁም ሰብል ሲያጠፋ የነበረው ጎርፍ አሁን ላይ አቅጣጫው ተቀይሮለት ወደ ዲጆ ወንዝ እንዲገባና ለመስኖ ሥራ እንዲውል ተደርጓል።

ከጎርፍ የተላቀቀችው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሃላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ስር የምትገኘው ሲምቢጣ ቀበሌ ለሥራ የተጉ እጆች ይበዙባታል። ትጋት መገለጫቸው የሆኑ አርሶ አደሮቿ ስለሲምቢጣ የቀደመ ታሪክ ሲያነሱ ቀበሌዋ የምትታወቀው በችግር፣ በተረጅነትና በጎርፍ ተጋላጭነቷ ነበር ይላሉ።

ትናንት ብዙዎች የርዳታ እጃቸውን ለመዘርጋት፣ የሴፍትኔት ርዳታ ለማድረስና ጎርፍ ያደረሰውን ጉዳት ለመመልከት ወደ ቀበሌዋ ያመሩ ነበር። ለውጡን ተከትሎ አካባቢው ላይ በተሠሩ የቅንጅት የልማት ሥራዎች ለክልሉ ብሎም ለሀገር እዳ የነበረችው ሲምቢጣ ወደ ምንዳነት ተለውጣለች።

አሁን ላይ ምርጥ ተሞክሮዋን ለመቅሰም፣ የተትረፈረፈ ምርቷን ለመገብየትና ልምላሜዋን ለማድነቅ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች የሚመላለሱባት “የይቻላል ተምሳሌት”.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131862
በመዲናዋ በከተማ ግብርና ከ150 ሺህ ቶን በላይ ምርት ተገኝቷል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በከተማ ግብርና ልማት ከ150 ሺህ ቶን በላይ ምርት ማግኘት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።

ከ690 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ መሆኑም ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አካሌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመዲናዋ የከተማ ግብርና በስፋት እየተሠራ ይገኛል።

በ2016 በጀት ዓመት በ11 ወራት 130 ሺህ 826 ቶን ምርት ለማግኘት ታቅዶ 153 ሺህ 358 ቶን የእንስሳትና እጽዋት ምርት ማግኘት ተችሏል።

ይህ የከተማ ግብርና ልማት ምርት የመደበኛ እና የሌማት ትሩፋትን ያካተተ ሲሆን፤ 110 ሺህ 152 ቶን የሚሆነው ከእንስሳት ምርት እንዲሁም 43 ሺህ 206 ቶን ከእፅዋት ምርት የተገኘ መሆኑን አብራርተዋል።

ከተገኘው የእንስሳት ምርትም 317 ሚሊዮን 862 ሺህ 924 እንቁላል፣ 25 ሚሊዮን 905 ሺህ ሊትር በላይ ወተት፣ አራት ሺህ 955 ቶን የዶሮ ስጋ፣ 329 ሺህ 910 ኪሎ ግራም ማር፣ አራት ሺህ ኪሎ ግራም የአሳ ስጋ እንዲሁም 23 ሺህ 108 ቶን የበሬ፣ የበግና ፍየል ሥጋ ምርት......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131882
በዘንድሮው ክረምት በ214 ሺህ 552 ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ ይተከላል
************************
(ኢ ፕ ድ)
በዘንድሮው ክረምት በ214 ሺህ 552 ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ እንደሚተከል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ደፈረስ ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ በተያዘው መኸር ወቅት 214 ሺህ 552 ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ ይተከላል።

ከአረንጓዴ ዐሻራ ወዲህ በ850 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ መትከል ተችሏል ያሉት አቶ ፍቃዱ፤ በተያዘው ክረምት ወቅት የሚተከል አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ችግኝ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

እስከ አሁንም 106 ሺህ 168 ሄክታር መሬት አዲስ ተከላ መካሄዱን አብራርተዋል።

አቶ ፍቃዱ አክለውም፤ ባለፈው ዓመት አጠቃላይ 833 ሺህ ቶን ምርት ማግኘት ተችሏል ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ በቡና ልማት ሀገሪቱ መጠቀም ያለባትን ያህል መጠቀም ባትችልም ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥሩ መሻሻሎችን.......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131872