የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት‼️
ጎርጎራ ቅኔ ነው፤ ጎርጎራ የልዕልና ምልክት ነው፤ ጎርጎራ የመቻል ምሳሌ ነው፤ ጎርጎራ ትናንትን ከዛሬና ነገን ማስተሳሰሪያ ገመድ ነው ፣ ጎርጎራ የኢትዮጵያ ከፍታ ማሳያ ነው፡፡
ዓይን የማያስከድን የድንቅ ውበት ባለቤት የሆነው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን ዛሬ መርቀናል፡፡
ጥንታዊቷ ጎረጎራ "በገበታ ለሀገር" ፕሮጀክት በስሟና በታሪኳ ልክ የሚመጥናትን ገፀ በረከት አግኝታለች፡፡
የጎርጎራ ልማት ለጣና ተጨማሪ ሞገስ፣ ለጎንደርና ባሕር ዳር ክብር፣ ለኢትዮጵያ ደግሞ የመቻል ማሳያዋ ነዉ፡፡ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት እንደ ሀገር በፈተናዎች የመፅናት አቅማችን የተገለጠበት ውጤታችን ነው፡፡
ጎርጎራ ንፅፅር የማይሻ፣ ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ የተገነባ፣ ውበትን በልዩ ጥበብ የታደለና ሳይደበዝዝ ለትውልድ የሚተላለፍ ድንቅ የዕጅ ስራ ነው፡፡
ይህን ግሩም የቱሪስት መስህብ ለመገንባት ያቀዱ፣ ተከታትለውና መርተው ላስጨረሱት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር፣ ንድፋን ለጣሉ ዕጆች፣ ለገነቡ ብርቱ ክንዶች እንዲሁም ውበትን ላላበሱ ዕሳቤዎች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል፡፡
ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓም