Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.7K subscribers
40.2K photos
309 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት‼️

ጎርጎራ ቅኔ ነው፤ ጎርጎራ የልዕልና ምልክት ነው፤ ጎርጎራ የመቻል ምሳሌ ነው፤ ጎርጎራ ትናንትን ከዛሬና ነገን ማስተሳሰሪያ ገመድ ነው ፣ ጎርጎራ የኢትዮጵያ ከፍታ ማሳያ ነው፡፡

ዓይን የማያስከድን የድንቅ ውበት ባለቤት የሆነው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን ዛሬ መርቀናል፡፡

ጥንታዊቷ ጎረጎራ "በገበታ ለሀገር" ፕሮጀክት በስሟና በታሪኳ ልክ የሚመጥናትን ገፀ በረከት አግኝታለች፡፡

የጎርጎራ ልማት ለጣና ተጨማሪ ሞገስ፣ ለጎንደርና ባሕር ዳር ክብር፣ ለኢትዮጵያ ደግሞ የመቻል ማሳያዋ ነዉ፡፡ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት እንደ ሀገር በፈተናዎች የመፅናት አቅማችን የተገለጠበት ውጤታችን ነው፡፡

ጎርጎራ ንፅፅር የማይሻ፣ ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ የተገነባ፣ ውበትን በልዩ ጥበብ የታደለና ሳይደበዝዝ ለትውልድ የሚተላለፍ ድንቅ የዕጅ ስራ ነው፡፡

ይህን ግሩም የቱሪስት መስህብ ለመገንባት ያቀዱ፣ ተከታትለውና መርተው ላስጨረሱት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር፣ ንድፋን ለጣሉ ዕጆች፣ ለገነቡ ብርቱ ክንዶች እንዲሁም ውበትን ላላበሱ ዕሳቤዎች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል፡፡

ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓም
ኮሚሽኑ በድሬዳዋና በሦስት ክልሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ሊጀምር ነው
*****
(ኢ ፕ ድ)

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአራት ክልሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይፋ አደረገ፡፡ በ10 ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታና መረጣ መጠናቀቁም ተገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፤ ምክክር ኮሚሽኑ የመጀመሪያውን አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስኬት ማካሄዱን አስታውሰዋል።

በመጪው ሳምንት በአራት ክልሎች አጀንዳ የማሰባሰብና የማወያየት ተግባር ይጀምራል ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣በሐረር፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

ኮሚሽነሮች ምደባ በማካሄድ በአንድ ጊዜ ወደ አራት ክልሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራው እንደሚሠራ ገልጸው፤ የክረምቱ ሁኔታ ካላስቸገረ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በአብዛኛው ክልሎች አጀንዳ የማሰብሰብ ሥራው እንደሚጠናቀቅ አመላክተዋል።

በአፋር ክልል በዚህ ወቅት ሙቀቱ እየበረታ የሚሄድበት ወቅት ነው ያሉት ዋና ሰብሳቢው፤ ሙቀቱ እየቀነሰ ሲመጣ በሚቀጥለው ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ አካባቢ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132012
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የ#ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ምርቃት‼️