ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ ማሳሰቢያ‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለክቡራን መንገደኞቹ የሚሰጣቸው ዓለም አቀፍ የበረራ ቲኬት ሽያጭ አገልግሎቶች በሙሉ በውጪ ምንዛሪ (hard currency) ብቻ እንደሚሆን ተደርጎ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ አውታሮች ሲዘዋወር ተመልክቶታል።
ይሁን እንጂ የጉዳዩ ትክክለኛ መረጃ በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም መመርያ ማውጣቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም ከሀገር ውጪ ተነስተው ወደ ሀገራችን ለሚደረጉ ጉዞዎች በሀገር ውስጥ መገበያያ ገንዘብ ሲሰጥ የነበረውን የበረራ ቲኬት ሽያጭ አሰራር ከሐምሌ 02 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል የተከለከለ መሆኑን እና በውጪ ምንዛሪ አገልግሎቱን የሚያገኙ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
ይኸውም ሀገር ውስጥ በሚንቀሳቀሱ በሁሉም አየር መንገዶች ተግባራዊ እንዲደረግ የወረደ መመርያ መሆኑን እያሳሰብን ኢትዮጵያዊያን እና ህጋዊ ሰነድ ያላቸው (የመኖርያ ፈቃድ፣ ቢጫ ካርድ፣ የሥራ ፈቃድ፣ የዲፕሎማቲክ ፈቃድ ወዘተ) የውጪ ሀገር ዜጎች በሙሉ ከሀገር ውስጥ ወደ ውጪ ሀገራት ለሚደረጉ በረራዎች የቲኬት ሽያጭ አገልግሎታችንን ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። ነገር ግን ትኬታቸውን በኢትዮጵያ የሚገዙ የውጭ ሀገር ዜጎች በውጭ ምንዛሬ መክፈል ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ እባክዎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችንን በመጎብኘት፣ የጉዞ ወኪልዎን በማነጋገር ወይም ሀገር ውስጥ ከሆኑ ወደ 6787 በመደወል ዓለም አቀፍ የደንበኞች ማስተናገጃ ማዕከላችንን ያነጋግሩ አልያም ድረ ገፃችን ላይ ካሉት ቁጥሮች በመምረጥ ይደውሉ።
ሐምሌ 10 ቀን 2016 ዓም

ደቡብ ሱዳን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱን ማፅደቋ ለኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ማረጋገጫ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)
ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማፅደቋ ለኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ማረጋገጫ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ማፅደቋን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ከአሁን በፊት የናይል ተፋሰስ ሀገራትን በማስተባበር፤ ሙግትና ሀሳብ ከማመንጨት ጀምሮ በርካታ ሥራዎችን ስትሠራ መቆየቷን ተናግረዋል፡፡ ከ14 ዓመታት በፊት የፀደቀውና ለ11 ዓመታት ድርድር የተካሄደበት የትብብር ማዕቀፍ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ መድረሱ ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ስኬትን ያሳያል ብለዋል፡፡
እንደ ፕሮፌሰር ያዕቆብ ገለጻ፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ለማዘጋጀትም ሆነ የትብብር ማዕቀፉ በናይል ተፋሰስ ሀገራት እንዲፈረም ትልቅ ጥረት፣ አስተዋፅዖና ተጋድሎ አድርጋለች፡፡ አሁን ላይ ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ማፅደቋም ለኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132248

❤1
ተሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገው ድንገተኛ የቴክኒክ ፍተሻ ተጠናክሮ ይቀጥላል
👉 20ሺ ተሽከርካሪዎች ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎባቸዋል
👉 4ሺ ያህል ተሽከርካሪዎች ጉድለታቸውን እንዲያስተካክሉ ተደርጓል
*****
(ኢ ፕ ድ)
ተሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገውን ድንገተኛ የቴክኒክ ፍተሻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር፣ ደሳለኝ ተረፈ (ኢንጂነር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በተሽከርካሪዎች ውጫዊና ውስጣዊ አካል ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን ለማስተካከል በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገውን ድንገተኛ ፍተሻ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
በተጠናቀቀው የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ500ሺ በላይ ተሽከርካሪዎች የቦሎ ምርመራ ማድረጋቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ በ20ሺ መኪኖች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ መደረጉን አስታውቀዋል።
ተሽከርካሪዎች በዓመት አንድ ጊዜ የቦሎ ምርመራ ስላደረጉ ብቻ ዓመቱን ሙሉ ጤናማ ሆነው ይዘልቃሉ ማለት አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ፣ በተሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገውን ድንገተኛ ፍተሻ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በበጀት ዓመቱ ድንገተኛ ፍተሻ የተደረገባቸው ተሽከርካሪዎች ቁጥር በመዲናዋ ካለው የተሽከርካሪ ቁጥር.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132265

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)መልዕክት‼️
ዛሬ የአየርላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ እና መከላከያ ሚኒስትር የሆኑትን ሚካኤል ማርቲን እና ልዑካን ቡድናቸውን አግኝቼ በርከት ባሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት በማድረጌ ደስ ብሎኛል።
ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓም

ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የደራርቱ ቱሉ የስፖርት ማሰልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩትን መረቁ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሱሉልታ ከአንድ ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ብር በሆነ ወጪ የተገነባውን የደራርቱ ቱሉ የስፖርት ማሰልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩትን መረቁ።
በ16 የስፖርት ዓይነቶች ከ800 በላይ ስፖርተኞችን ተቀብሎ የማሰልጠን አቅም እንዳለው ተገልጿል።
የሀገሪቱን ስፖርት በሳይንሳዊ መንገድ በመምራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ለማድረግ የተቋቋመ እንደሆነ ተጠቁሟል።
በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰአዳ አብዱራህማን፣ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የኦሊምፒክና የፊፋን ደረጃን ጠብቆ የተገነባዉ አካዳሚዉ በዉስጡ 196 የስፖርተኞች ማደርያ ክፍል፣ 2 የአስተዳደር መኖርያ ቤቶች፣ 80 የአሰልጣኞች መኖርያ፣ 24 የመማርያ ክፍሎች፣ 2 የጥናትና ምርምር ክፍሎች፣ 5200 ሰዉ መያዝ የሚችል ጂምናዝየም፣ 3 የእግር ኳስ ሜዳ፣ 1 የሩጫ መም፣ 2 የእጅ ኳስ ሜዳ፣ 4 የቅርጫት ኳስ ሜዳ 6 የመረብ ኳስ ሜዳ፣ 6 የሜዳ ቴኒስ፣ 2 የዉሃ መዋኛ ገንዳ፣ 5200 ሰዉ መያዝ የሚችል አደራሽ፣ 250 ሰዉ የሚያስተናግድ ዘመናዊ አደራሽ፣ ክሊኒክና የመዝናኛ ክፍሎችን አካቷል።
በአለማየሁ ግዛዉ

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
በዛሬው የምክር ቤታችን ውሎ ለ2017 በጀት ዓመት 230.39 ቢሊዮን ብር በጀት አውጀናል።
ከዚህ ውስጥ 146.48 ቢሊዮን ብር (63.6 በመቶ) ለካፒታል የተመደበ ሲሆን፣ 74.55 ቢሊዮን ብር (33.4 በመቶ) ለመደበኛ ወይም ለአስተዳደርዊ ወጪ የተመደበ ነው።
ለካፒታል ከተመደበው ውስጥ 90.4 በመቶ ለድህነት ቅነሳና እድገት ተኮር ዘላቂ ልማት ለሆኑ ፕሮጀክቶች የተመደበ ነው።
ውድ የከተማችን ግብር ከፋዮች፤ ይህን በጀት ማሳካት የጋራ ርብርብ ይጠይቃል።
በ2016 በጀት ዓመት ግብራችሁን በወቅቱ በፈቃደኝነት በመክፈላችሁ 146.8 ቢሊዮን ብር ግብር ሰብስበን 18,091 ፕሮጀክቶችንና የኮሪደር ልማትን ተግብረን ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ አበባ በማድረግ የጋራ አሻራችንን እያስቀመጥን ነው።
በዚህ ዓመትም እጅ ለእጅ ተያይዘን የበለጠ ለመስራት ሁላችንም ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህቦቿን ይባርክ

የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ስለቡና ግብይት በሰጡት ማብራሪያ‼️
👉በቡና ግብይት በላኪውና በአቅራቢው መካከል የሚፈጠሩ ችግሮች እንዲፈቱ እንሰራለን፣
👉 የግብይት ስርዓቱን ማሳጠር ብቻ ሳይሆን ከአንድ ኪሎ ቡና ዝቅተኛ ዋጋ ህዳግ ማስተካከል አስፈላጊ ነበር፣
👉 ኮሜርሻል የሚባሉት ደረጃ አራትና አምስት መጠናቸውን በመቀነስ ስፔሻሊቲ ቡና ላይ በመስራት በኒውዮርክ ገበያ ከብራዚል ቡና ጋር እኩል መወዳደር እንዲችል ማሻሻያ ተደርጓል፣
👉 የስፔሻሊቲ ቡናን ድርሻ ከፍ ለማድረግ በ2014 ዓ.ም የስፔሻሊቲ ቡናን ወደ 60 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል፣
👉 የኮሜርሻሉ ከ70 በመቶ ወደ 40 በመቶ እንዲወርድ ተደርጓል፣
👉 በ2014 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣
👉 በልማቱ ዘርፍ ምርትና ምርታማቱ ላይ ያሉ ችግሮችን የመቅረፍ ስራ ተከናውኗል
👉 በ2017 ዓ.ም አንድ ነጥብ 8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እናገኛለን ብለን አቅደን እየሰራን ነው፣
👉 በቡና ግብይት ላይ አሁንም ፈተናዎች አሉ፤ ስርቆቱን መቶ በመቶ ቀርፈናል አንልም፤
👉 ሆኖም ግን ቴክኖሎጂ በማበልጸግ ቡና የት እንደሚደርስ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግበት ስርዓት ተፈጥሯል፣
👉 የቡና ግብይት መመሪያው የሚለው ቡና በተረካከቡ በሶስተኛው ቀን ቅሬታቸው ለባለስልጣኑ ማቅረብ ይችላሉ፣
👉 የቀጥታ ትስስር ግብይትና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አማራጭ ናቸው፣
👉 የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አልተዘጋም የቀጥታ ትስስር ግብይት አስገዳጅ ሳይሆን አማራጭ የገበያ ስርዓት ነው፣
👉 ለምሳሌ ምርት ገበያ ላይ በፈረሱላ አራት ሺ ብር ከሆነ የቀጥታ ትስስር እስከ አራት ሺ 200 ድረስ መገበያየትን ዕድል ይሰጣል፣
https://press.et/?p=132195

በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት ተስማምተናል
- የክልሎቹ ርዕሳነ መስተዳድሮች
*****
(ኢ ፕ ድ)
በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት ከስምምነት መደረሱን የየክልሎቹ ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት መስማማታቸውን በተመለከተ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በዘላቂነት ለመፍታት የክልሎቹና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ በቀጣይም ለግጭቶች ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት የጋራ መፍትሄ ለመስጠት ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።