Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የደራርቱ ቱሉ የስፖርት ማሰልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩትን መረቁ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሱሉልታ ከአንድ ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ብር በሆነ ወጪ የተገነባውን የደራርቱ ቱሉ የስፖርት ማሰልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩትን መረቁ።

በ16 የስፖርት ዓይነቶች ከ800 በላይ ስፖርተኞችን ተቀብሎ የማሰልጠን አቅም እንዳለው ተገልጿል።

የሀገሪቱን ስፖርት በሳይንሳዊ መንገድ በመምራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ለማድረግ የተቋቋመ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰአዳ አብዱራህማን፣ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኦሊምፒክና የፊፋን ደረጃን ጠብቆ የተገነባዉ አካዳሚዉ በዉስጡ 196 የስፖርተኞች ማደርያ ክፍል፣ 2 የአስተዳደር መኖርያ ቤቶች፣ 80 የአሰልጣኞች መኖርያ፣ 24 የመማርያ ክፍሎች፣ 2 የጥናትና ምርምር ክፍሎች፣ 5200 ሰዉ መያዝ የሚችል ጂምናዝየም፣ 3 የእግር ኳስ ሜዳ፣ 1 የሩጫ መም፣ 2 የእጅ ኳስ ሜዳ፣ 4 የቅርጫት ኳስ ሜዳ 6 የመረብ ኳስ ሜዳ፣ 6 የሜዳ ቴኒስ፣ 2 የዉሃ መዋኛ ገንዳ፣ 5200 ሰዉ መያዝ የሚችል አደራሽ፣ 250 ሰዉ የሚያስተናግድ ዘመናዊ አደራሽ፣ ክሊኒክና የመዝናኛ ክፍሎችን አካቷል።

በአለማየሁ ግዛዉ
ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

በዛሬው የምክር ቤታችን ውሎ ለ2017 በጀት ዓመት 230.39 ቢሊዮን ብር በጀት አውጀናል።
ከዚህ ውስጥ 146.48 ቢሊዮን ብር (63.6 በመቶ) ለካፒታል የተመደበ ሲሆን፣ 74.55 ቢሊዮን ብር (33.4 በመቶ) ለመደበኛ ወይም ለአስተዳደርዊ ወጪ የተመደበ ነው።

ለካፒታል ከተመደበው ውስጥ 90.4 በመቶ ለድህነት ቅነሳና እድገት ተኮር ዘላቂ ልማት ለሆኑ ፕሮጀክቶች የተመደበ ነው።

ውድ የከተማችን ግብር ከፋዮች፤ ይህን በጀት ማሳካት የጋራ ርብርብ ይጠይቃል።

በ2016 በጀት ዓመት ግብራችሁን በወቅቱ በፈቃደኝነት በመክፈላችሁ 146.8 ቢሊዮን ብር ግብር ሰብስበን 18,091 ፕሮጀክቶችንና የኮሪደር ልማትን ተግብረን ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ አበባ በማድረግ የጋራ አሻራችንን እያስቀመጥን ነው።

በዚህ ዓመትም እጅ ለእጅ ተያይዘን የበለጠ ለመስራት ሁላችንም ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህቦቿን ይባርክ
የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ስለቡና ግብይት በሰጡት ማብራሪያ‼️

👉በቡና ግብይት በላኪውና በአቅራቢው መካከል የሚፈጠሩ ችግሮች እንዲፈቱ እንሰራለን፣

👉 የግብይት ስርዓቱን ማሳጠር ብቻ ሳይሆን ከአንድ ኪሎ ቡና ዝቅተኛ ዋጋ ህዳግ ማስተካከል አስፈላጊ ነበር፣

👉 ኮሜርሻል የሚባሉት ደረጃ አራትና አምስት መጠናቸውን በመቀነስ ስፔሻሊቲ ቡና ላይ በመስራት በኒውዮርክ ገበያ ከብራዚል ቡና ጋር እኩል መወዳደር እንዲችል ማሻሻያ ተደርጓል፣

👉 የስፔሻሊቲ ቡናን ድርሻ ከፍ ለማድረግ በ2014 ዓ.ም የስፔሻሊቲ ቡናን ወደ 60 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል፣

👉 የኮሜርሻሉ ከ70 በመቶ ወደ 40 በመቶ እንዲወርድ ተደርጓል፣

👉 በ2014 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣

👉 በልማቱ ዘርፍ ምርትና ምርታማቱ ላይ ያሉ ችግሮችን የመቅረፍ ስራ ተከናውኗል

👉 በ2017 ዓ.ም አንድ ነጥብ 8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እናገኛለን ብለን አቅደን እየሰራን ነው፣

👉 በቡና ግብይት ላይ አሁንም ፈተናዎች አሉ፤ ስርቆቱን መቶ በመቶ ቀርፈናል አንልም፤

👉 ሆኖም ግን ቴክኖሎጂ በማበልጸግ ቡና የት እንደሚደርስ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግበት ስርዓት ተፈጥሯል፣

👉 የቡና ግብይት መመሪያው የሚለው ቡና በተረካከቡ በሶስተኛው ቀን ቅሬታቸው ለባለስልጣኑ ማቅረብ ይችላሉ፣

👉 የቀጥታ ትስስር ግብይትና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አማራጭ ናቸው፣

👉 የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አልተዘጋም የቀጥታ ትስስር ግብይት አስገዳጅ ሳይሆን አማራጭ የገበያ ስርዓት ነው፣

👉 ለምሳሌ ምርት ገበያ ላይ በፈረሱላ አራት ሺ ብር ከሆነ የቀጥታ ትስስር እስከ አራት ሺ 200 ድረስ መገበያየትን ዕድል ይሰጣል፣
https://press.et/?p=132195
በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት ተስማምተናል
- የክልሎቹ ርዕሳነ መስተዳድሮች
*****
(ኢ ፕ ድ)

በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት ከስምምነት መደረሱን የየክልሎቹ ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት መስማማታቸውን በተመለከተ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በዘላቂነት ለመፍታት የክልሎቹና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በቀጣይም ለግጭቶች ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት የጋራ መፍትሄ ለመስጠት ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓም
የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ
****
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ።

1ኛ) ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ

2ኛ) አቶ ያብባል አዲስ ጎበዜ -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

3ኛ) አቶ አንድነት ብዙሰው ታመነ- የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር

4ኛ) አቶ ቁሴ ለታ ዋቅጅራ- የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር

5ኛ) አቶ ማሾ ኦላና- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ

6ኛ) ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ - የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

በማርቆስ በላይ

ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓም
“የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ”

የዘንድሮ የ#አረንጓዴዓሻራ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥርዬን አቀርባለው

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የውድድር አድማሱ የሰፋው የባንክ ሥራ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ባለፈው ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራው የባንክ ሥራ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት እንዲደረግ በመንግሥት የተላለፈውን የፖሊሲ ውሳኔ ወደ ተግባር ለማሸጋገር ያለመ ነው፡፡

ረቂቅ ማሻሻያ አዋጁ የውጭ አገር ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ ዕድል የሚፈጥር ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ሀሳቦች ይሰነዘራሉ፡፡

አዋጁን ተከትሎ የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ሥራ ሲጀምሩ ለዜጎች ጥሩ የባንክ አማራጭ እንደሚሆኑ ብዙ የባንክ ሥራ ባለሙያዎች ይስማማሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የባንኮቹ መግባት የሀገር ውስጥ ባንኮችን ሕልውናን ሊፈታተን ይችላል ሲሉ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ፡፡

የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይስማማሉ፡፡ የውጭ ባንኮቹ መግባት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማደግ ትልቅ ፋይዳ ቢኖረውም አዋጁን ተከትለው በሚወጡ መመሪያዎች.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132427