Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአየርላንድ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት በተለያዩ ዘርፎች እንደምትደግፍ ገለፀች
******
(ኢ ፕ ድ)

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ከአየርላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትር ከሆኑት ሚካኤል ማርቲንን ጋር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የምክክር ሂደት በሚመለከት ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአየርላንድ የሰላም ግንባታ ሂደት ተሞክሮ ገልፀው፣ በሂደቱ የፓለቲካ ቁርጠኝነትና ብዘሀነትን የማስተናገድ ፈቃደኝነት ለሀገራዊ ምክክርና ለሰላም ግንባታ ሂደት የነበራቸውን ጉልህ ሚና አብራርተዋል፡፡

በሀገራቸው በተደረጉ የሰላም ግንባታ ሂደቶች ሴቶች ዋነኛ ተሳታፊ መደረጋቸው ሂደቱን ውጤታማ አድርጎታል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት በተለያዩ ዘርፎች ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።

ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
የዓባይ ውሃ ፖለቲካ – ከቅኝ ግዛት ስምምነት ወደ ዘመናዊ ትብብር
***
(ኢ ፕ ድ)

በቅርቡ ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማፅደቋን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው ይታወሳል። ለመሆኑ ደቡብ ሱዳን በስምምነቱ ውስጥ መካተቷ በናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ውስጥ ያለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ምን አንድምታ ይኖረዋል?

የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ከፍተኛ አማካሪ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው እንደሚሉት፤ ከታሪክ አኳያ የናይል ወንዝን በሚመለከት የውሃ መጋራት ስምምነቶች የተፈረሙት በቅኝ ግዛት ዘመን በተለይም በ1929 እና በ1959 በተፈረሙ ስምምነቶች ግብፅና ሱዳንን በእጅጉ የሚደግፉ ናቸው።

እነዚህ ስምምነቶች እንደ ኢትዮጵያ ላሉ የተፋሰሱ ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቁ አልነበሩም። አዲሱ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ያለውን መግባባት በማንፀባረቅ ፍትሐዊ የዓባይ ሀብት ክፍፍልን ለመፍጠር ያለመ ነው። ማዕቀፉ ፕሮጀክቶች እንዴት መተግበር እንዳለባቸው የሚዘረዝሩ የተለያዩ ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን፤ የሀገራቱን የመረጃ ልውውጥ እና ትብብር አስፈላጊነት አጽንዖት ይሰጣል።

እንደ ኢንጂነር ጌዲዮን ገለጻ ማዕቀፉ ተግባራዊ የሚሆነው ከአስራ አንዱ አባል ሀገራት በስድስቱ ሲፀድቅ እና ለአፍሪካ ኅብረት ሲቀርብ ነው። ይህ ስምምነት እ.ኤ.አ. በ1929 እና በ1959 የተፈረሙትን የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን በመተካት ትኩረቱን ወደ ዓባይ ወንዝ የትብብር አስተዳደር በማሸጋገር የውሃ አያያዝ እና ስርጭትን የሚመለከቱ 45 አንቀጾችን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132489
ኢትዮጵያ ድንበር ዘለል የልማት ሥራዎችን እያከናወነች ነው
*****
(ኢ ፕ ድ)

ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ለመስጠት ኢትዮጵያ ድንበር ዘለል የልማት ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ አስታወቁ።

አምባሳደር ነቢል እንደገለጹት፤ እ.ኤ.አ በ2023 ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የ220 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ድንበር አቋራጭ መንገድ ለመገንባት የ738 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የደቡብ ሱዳን የሽግግር ብሔራዊ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማፅደቁን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሁለቱ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር የሚያጠናክር ድንበር ዘለል ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እያደረገች ነው። ኢትዮጵያ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የጋራ ተጠቃሚነትን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132491
«ኢኮ ፓርኩ ለክልሉ ቱሪዝም እድገት ከፍተኛ ሚና አለው» – የሐረሪ ክልል የባሕል ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባው የሐረር ኢኮ ፓርክና የጅብ ትርዒት ማሳያ ማዕከል ለክልሉ ቱሪዝም እድገት ከፍተኛ ሚና እንዳለው የክልሉ የባሕል ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የሐረሪ ክልል የባሕል ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት፤ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ የተገነባው ኢኮ ፓርክና የጅብ ትርዒት ማሳያ ማዕከል ለክልሉ ቱሪዝም እድገት ከፍተኛ ሚና ያለው ነው።

እንደ ኃላፊው ገለጻ፤ ከዚህ ቀደም የነበረው የጅብ ማብላት ትርዒት ለቱሪስቱ ምቹ አልነበረም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐረርን በጎበኙበት ወቅት በሰጡት አስተያየትና የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ገቢ ለዚሁ እንዲውል በሰጡት አቅጣጫ መሠረት በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ሁኔታ በሕዝብ ተሳትፎ መጽሐፉ ተሽጦ ለዚሁ አገልግሎት ውሏል።

ኢኮ ፓርኩ ለክልሉ አሻራና ለቱሪዝሙ እድገት ከፍተኛ ሚና ያለው ነው ያሉት ኃላፊው፤ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል፤ ለዕደ ጥበብና ለሥነ ጥበብ እድገት.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132505
ለአራት አመታት ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ የነበሩ አካባቢዎች ወደ አገልግሎቱ ተመለሱ
*******
(ኢ ፕ ድ)

በኦሮሚያ ክልል አራቱም የወላጋ ዞኖች  ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ በተሰራው የመልሶ ጥገና ስራ ለአመታት ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ የነበሩ ከተሞች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ 

በቄለም ወለጋ ዞን ዳሌ ሰዲ ወረዳ የሚገኙ ሳጠኖ ዲማና ቤለም አካባቢዎች ከ4 ዓመታት በኋላ፤ ደንበል ሱልጣንና ሐረሬ ኦግኦ የሚባሉ ቦታዎች ከ2 ዓመታት በኋላ የተቋረጠባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል ምስራቅ ወለጋ ዞን ግዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ከተማ ብዙ መንደሮችና ለሊ ቀበሌ እንዲሁም ገባ ፈጫሴ፣ጠንከራና ቦነያ ጤና ጣቢያ ከ2 እስከ 4 ዓመታት በኋላ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ችለዋል፡፡

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አባቦ ጉዱሩ ወረዳ ገባ ፈጫሴ፣ ቃዎ፣ ሀለዮ፣ ቆርቾና ገባ ፈጫሴ ቴሌኮም አከባቢዎች ከ2 እስከ 3 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ አገልግሎቱ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን ዩብዶ ወረዳ መለያ ዩብዶ ቀበሌ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ አገልግሎቱ ተመልሳለች፡፡

እነዚህን 18 ቀበሌዎችና ከተሞችን ዳግም ከኤሌክትሪክ ጋር ለማገናኘት በተሰራው ስራ ከ78 ኪ.ሜ በላይ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና ጥገና እንዲሁም 19 ትራንስፎርመሮችን መተካት ተችሏል፡፡

በወላጋ ዞኖች በእስካሁኑ ስራ በዞኖቹ ከ85 በላይ ከተሞችና ቀበሌዎች ዳግም ወደ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲመለሱ መደረጉን  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።

ሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በሲዳማ ክልል ዘጠኝ ሺህ አርሶ አደሮች በዘመናዊ መስኖ ተጠቃሚ ሆነዋል
******
(ኢ ፕ ድ)

ሲዳማ እራሱን ችሎ እንደክልል ከተቋቋመ ወዲህ በክልሉ መንግሥት አቅም ብቻ ዘጠኝ ሺህ አርሶ አደሮች በዘመናዊ መስኖ ልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ከበደ ጋኖሌ (ኢንጅነር) በክልሉ የሥራ ምልከታ ላደረጉ የጋዜጠኞች ቡድን እንደገለጹት፤ ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ በተፈጠረው ምቹ አስተዳደራዊ መዋቅር ግብርናውን በማዘመንና በማሸጋገር ክረምት፣ ከበጋ በዓመት ሦስትና ሁለት ጊዜ ማምረት የሚቻልበትን ዕድል ለመፍጠር ሰፋፊ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ተሠርተው ወደ ሥራ ገብተዋል። በዚህም በክልሉ መንግሥት አቅም ብቻ ዘጠኝ ሺህ አርሶ አደሮች በዘመናዊ መስኖ ልማት ተጠቃሚ ሆነዋል።

ሲዳማ እንደክልል ከመቋቋሙ በፊት በዘመናዊ መስኖ ይለማ የነበረው ከ500 ሄክታር መሬት የማይበልጥ ነበር የሚሉት የቢሮ ኃላፊው፤ ክልል ከሆነ በኋላ በክልሉ መንግሥት ብቻ ወንዝ በመጥለፍና በከርሰ ምድር ውሃ 4ሺህ500 ሄክታር መሬት በዘመናዊ መስኖ ለምቷል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የፌዴራል መንግሥት የግዳቦ ግድብ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን አውስተው፤ በዚህ ፕሮጀክት ብቻ 3ሺህ ሄክታር መሬት በዘመናዊ መስኖ......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132490
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተባለ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

ኢኤስፒኤን (ESPN) የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ 10 ታላላቅ አፍሪካውያን ስፖርተኞችን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሁለት አትሌቶችን በማስመረጥ ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል።

ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቀዳሚውን ደርጃ ሲይዝ ኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሴቶች የዚምቧብዌዋ የዋና ስፖርት ተወዳዳሪ ክርስቲ ኮቨንትሪ ቀዳሚውን ደርጃ ስትይዝ ኢትዮጵያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶች ሁለተኛ በሁለቱም ጾታ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።

ሐምሌ 13 ቀን 2016ዓ.ም
የገንዘብ ፖሊሲው ዘመናዊ የባንክ አሠራርን ያመጣ ይሆን?
**************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንኩን የፖሊሲ ተመን መወሰን፣ የሰነዶች ግብይት ጨረታ መጀመር፣ የአንድ ቀን የብድር እና የገንዘብ አገልግሎት ማስተዋወቅና የባንክ ለባንክ የገበያ ሥርዓት ማስተዋወቅን ያካተተ አዲስ የፖሊሲ ማዕቀፍ በቅርቡ ይፋ አድርጓል።

አዲሱ ፖሊሲ የባንኩን አሠራር የሚያዘምን፣ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ጋር የተጣጣመ፣ ለፈጣን፣ ፍትሃዊ እና ሥራ ፈጣሪ የኢኮኖሚ ልማት የሚረዳም መሆኑን የባንኩ ገዢ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋል።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ክቡር ገና ባንኩ ይፋ ያደረገው አዲሱ ፖሊሲ ወደ ዘመናዊ የባንክ አሠራር የሚያሸጋግር፣ ባንኮች የተረጋጋ አሠራር እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን ያመለክታሉ።

ባንኮች ሊኩዲቲ (የገንዘብ እጥረት) ችግር ስላለባቸው ያንን ለማስተካከል ያስችላልም ነው ያሉት። እንደ ክቡር ገለጻ፤ አንዳንድ ባንኮች የመንግሥት ድጋፍ ባይኖራቸው ኖሮ ከስረው ሊዘጉ ይችሉ ነበር።

ነገር ግን ጥንቃቄ የተላበሰ፣ ሥርዓቱን የጠበቀ አሠራር በመኖሩ በኢትዮጵያ ባንኮች በመንግሥት ድጋፍ ጭምር ሊቀጥሉ ችለዋል።

ይፋ የሆነው አሠራር ከዚህ በፊትም ሊኖር ይገባ የነበረ፣ ባንኮች እርስ በእርስ እንዲበዳደሩ የሚያስችል አሠራር የፈጠረላቸው ነው።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርሄ ተስፋ (ዶ/ር) እንደሚሉትም፤ የባንክ ተመን የፖሊሲ አቋም ለመጠቆም፣ ሰፋ ያለ የገንዘብና የብድር ሁኔታዎች ላይ ተጽእኖ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132572
👍1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️