Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ”

የዘንድሮ የ#አረንጓዴዓሻራ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥርዬን አቀርባለው

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የውድድር አድማሱ የሰፋው የባንክ ሥራ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ባለፈው ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራው የባንክ ሥራ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት እንዲደረግ በመንግሥት የተላለፈውን የፖሊሲ ውሳኔ ወደ ተግባር ለማሸጋገር ያለመ ነው፡፡

ረቂቅ ማሻሻያ አዋጁ የውጭ አገር ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ ዕድል የሚፈጥር ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ሀሳቦች ይሰነዘራሉ፡፡

አዋጁን ተከትሎ የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ሥራ ሲጀምሩ ለዜጎች ጥሩ የባንክ አማራጭ እንደሚሆኑ ብዙ የባንክ ሥራ ባለሙያዎች ይስማማሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የባንኮቹ መግባት የሀገር ውስጥ ባንኮችን ሕልውናን ሊፈታተን ይችላል ሲሉ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ፡፡

የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይስማማሉ፡፡ የውጭ ባንኮቹ መግባት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማደግ ትልቅ ፋይዳ ቢኖረውም አዋጁን ተከትለው በሚወጡ መመሪያዎች.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132427
"የቀድሞው ደቡብ ክልል የጋራ ሀብት በሠላማዊና ፍትሐዊ መንገድ ተከፋፍሎ ተጠናቋል”
– አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
*****
(ኢ ፕ ድ)

የቀድሞው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የነበረው የጋራ ተንቀሳቃሽና ቋሚ ሀብት ሠላማዊና ፍትሐዊ በሆነ መንገገድ ተከፋፍሎ መጠናቀቁን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንደተናገሩት፤ የቀድሞው የደቡብ ክልል አሁን ላይ ወደ አራት ክልል ተከፋፍሏል። ይህንን ተከትሎ የሀብት ክፍፍሉን በሠላማዊ መንገድ ለመቋጨት መረጃ ላይ የተመሠረተ ድርድርና ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።

በቀድሞው ክልል የነበሩ የተንቀሳቃሽና ቋሚ ሀብት ክፍፍል በሠላማዊና ፍትሐዊ በሆነ መንገገድ ተከፋፍሎ ተጠናቋል ብለዋል።

የሀብት ክፍፍሉን በሠላማዊና ፍትሐዊ መንገድ ለመቋጨት መረጃ ላይ የተመሠረተ ድርድርና ውይይት ሲደረግ ቆይቷል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በመጨረሻም ኮሚቴ ተቋቁሞ የተንቀሳቃሽና የቋሚ ንብረቶች ክፍፍል መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ሁሉም የየድርሻውን ማግኘቱን ጠቁመው፤ ጥቂት ቀሪ የተንጠባጠቡ ጉዳዮች ካሉ እየታየ በጋራ ውይይት እልባት ያገኛል ሲሉ አስረድተዋል።

ቋሚ ንብረትን ወይም ሕንፃን በሚመለከት ደቡብ ክልል፣ ክልል ከሆነ እና መቀመጫውን ሃዋሳ ከተማ ካደረገ በኋላ በሀዋሳ ከተማ በጋራ የተገነቡ ንብረቶች ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ አሉ የሚሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ደስታ፤ በጋራ የተገነቡ ሕንፃዎች ተቆጥረው፤ “የቱ ወዴት ይሂድ?” የሚል ምክክር መደረጉን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132443
በሀረሪ ክልል ከ2 ቢሊዮን 253 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በሀረሪ ክልል በ2016 የበጀት አመት ከ2 ቢሊዮን 253 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሀላፊ ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃድር በክልሉ በ2016 የበጀት ከ2 ቢሊዮን 243 ሚሊዮን ለመሰብሰብ ታቅዶ 2 ቢሊዮን 253 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል ብለዋል።

ከተሰበሰበው ገቢ 1 ቢሊዮን 285 ሚሊየን በላይ ከቀጥታ ታክስ፤ 542 ነጥብ 6 ሚሊዮን ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፤ 64 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች፣ 360 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ መሰብሰቡን ገልጸዋል።

ከግብር አሰባሰብ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

በቀጣይም የክልሉ ገቢን ለማጎልበት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓም
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል 97 ነጥብ 5 በመቶው ፈተናውን ወስደዋል
******
(ኢ ፕ ድ)

በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል 97 ነጥብ 5 በመቶው ፈተናውን መውሰዳቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ በመላ ሀገሪቱ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701 ሺህ 749 ተማሪዎች መካከል 97 ነጥብ 5 በመቶው ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል።

ቀሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን ዘግይተው በመጀመራቸው ፈተናውን እንዳልወሰዱም ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ጠዋት መጠናቀቁን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ፈተናው በመላ ሀገሪቱ በስኬት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 29ሺህ 718 ተማሪዎች በበይነ መረብ የተፈተኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የበይነ መረብ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ መሰጠቱን ጠቅሰው፣ በቀጣይ ለሚሰጠው ፈተና የተሻለ ተሞክሮ የተገኘበት ነው ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓም
የአየርላንድ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት በተለያዩ ዘርፎች እንደምትደግፍ ገለፀች
******
(ኢ ፕ ድ)

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ከአየርላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትር ከሆኑት ሚካኤል ማርቲንን ጋር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የምክክር ሂደት በሚመለከት ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአየርላንድ የሰላም ግንባታ ሂደት ተሞክሮ ገልፀው፣ በሂደቱ የፓለቲካ ቁርጠኝነትና ብዘሀነትን የማስተናገድ ፈቃደኝነት ለሀገራዊ ምክክርና ለሰላም ግንባታ ሂደት የነበራቸውን ጉልህ ሚና አብራርተዋል፡፡

በሀገራቸው በተደረጉ የሰላም ግንባታ ሂደቶች ሴቶች ዋነኛ ተሳታፊ መደረጋቸው ሂደቱን ውጤታማ አድርጎታል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት በተለያዩ ዘርፎች ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።

ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
የዓባይ ውሃ ፖለቲካ – ከቅኝ ግዛት ስምምነት ወደ ዘመናዊ ትብብር
***
(ኢ ፕ ድ)

በቅርቡ ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማፅደቋን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው ይታወሳል። ለመሆኑ ደቡብ ሱዳን በስምምነቱ ውስጥ መካተቷ በናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ውስጥ ያለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ምን አንድምታ ይኖረዋል?

የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ከፍተኛ አማካሪ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው እንደሚሉት፤ ከታሪክ አኳያ የናይል ወንዝን በሚመለከት የውሃ መጋራት ስምምነቶች የተፈረሙት በቅኝ ግዛት ዘመን በተለይም በ1929 እና በ1959 በተፈረሙ ስምምነቶች ግብፅና ሱዳንን በእጅጉ የሚደግፉ ናቸው።

እነዚህ ስምምነቶች እንደ ኢትዮጵያ ላሉ የተፋሰሱ ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቁ አልነበሩም። አዲሱ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ያለውን መግባባት በማንፀባረቅ ፍትሐዊ የዓባይ ሀብት ክፍፍልን ለመፍጠር ያለመ ነው። ማዕቀፉ ፕሮጀክቶች እንዴት መተግበር እንዳለባቸው የሚዘረዝሩ የተለያዩ ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን፤ የሀገራቱን የመረጃ ልውውጥ እና ትብብር አስፈላጊነት አጽንዖት ይሰጣል።

እንደ ኢንጂነር ጌዲዮን ገለጻ ማዕቀፉ ተግባራዊ የሚሆነው ከአስራ አንዱ አባል ሀገራት በስድስቱ ሲፀድቅ እና ለአፍሪካ ኅብረት ሲቀርብ ነው። ይህ ስምምነት እ.ኤ.አ. በ1929 እና በ1959 የተፈረሙትን የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን በመተካት ትኩረቱን ወደ ዓባይ ወንዝ የትብብር አስተዳደር በማሸጋገር የውሃ አያያዝ እና ስርጭትን የሚመለከቱ 45 አንቀጾችን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132489
ኢትዮጵያ ድንበር ዘለል የልማት ሥራዎችን እያከናወነች ነው
*****
(ኢ ፕ ድ)

ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ለመስጠት ኢትዮጵያ ድንበር ዘለል የልማት ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ አስታወቁ።

አምባሳደር ነቢል እንደገለጹት፤ እ.ኤ.አ በ2023 ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የ220 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ድንበር አቋራጭ መንገድ ለመገንባት የ738 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የደቡብ ሱዳን የሽግግር ብሔራዊ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማፅደቁን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሁለቱ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር የሚያጠናክር ድንበር ዘለል ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እያደረገች ነው። ኢትዮጵያ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የጋራ ተጠቃሚነትን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132491
«ኢኮ ፓርኩ ለክልሉ ቱሪዝም እድገት ከፍተኛ ሚና አለው» – የሐረሪ ክልል የባሕል ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባው የሐረር ኢኮ ፓርክና የጅብ ትርዒት ማሳያ ማዕከል ለክልሉ ቱሪዝም እድገት ከፍተኛ ሚና እንዳለው የክልሉ የባሕል ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የሐረሪ ክልል የባሕል ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት፤ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ የተገነባው ኢኮ ፓርክና የጅብ ትርዒት ማሳያ ማዕከል ለክልሉ ቱሪዝም እድገት ከፍተኛ ሚና ያለው ነው።

እንደ ኃላፊው ገለጻ፤ ከዚህ ቀደም የነበረው የጅብ ማብላት ትርዒት ለቱሪስቱ ምቹ አልነበረም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐረርን በጎበኙበት ወቅት በሰጡት አስተያየትና የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ገቢ ለዚሁ እንዲውል በሰጡት አቅጣጫ መሠረት በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ሁኔታ በሕዝብ ተሳትፎ መጽሐፉ ተሽጦ ለዚሁ አገልግሎት ውሏል።

ኢኮ ፓርኩ ለክልሉ አሻራና ለቱሪዝሙ እድገት ከፍተኛ ሚና ያለው ነው ያሉት ኃላፊው፤ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል፤ ለዕደ ጥበብና ለሥነ ጥበብ እድገት.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132505
ለአራት አመታት ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ የነበሩ አካባቢዎች ወደ አገልግሎቱ ተመለሱ
*******
(ኢ ፕ ድ)

በኦሮሚያ ክልል አራቱም የወላጋ ዞኖች  ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ በተሰራው የመልሶ ጥገና ስራ ለአመታት ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ የነበሩ ከተሞች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ 

በቄለም ወለጋ ዞን ዳሌ ሰዲ ወረዳ የሚገኙ ሳጠኖ ዲማና ቤለም አካባቢዎች ከ4 ዓመታት በኋላ፤ ደንበል ሱልጣንና ሐረሬ ኦግኦ የሚባሉ ቦታዎች ከ2 ዓመታት በኋላ የተቋረጠባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል ምስራቅ ወለጋ ዞን ግዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ከተማ ብዙ መንደሮችና ለሊ ቀበሌ እንዲሁም ገባ ፈጫሴ፣ጠንከራና ቦነያ ጤና ጣቢያ ከ2 እስከ 4 ዓመታት በኋላ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ችለዋል፡፡

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አባቦ ጉዱሩ ወረዳ ገባ ፈጫሴ፣ ቃዎ፣ ሀለዮ፣ ቆርቾና ገባ ፈጫሴ ቴሌኮም አከባቢዎች ከ2 እስከ 3 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ አገልግሎቱ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን ዩብዶ ወረዳ መለያ ዩብዶ ቀበሌ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ አገልግሎቱ ተመልሳለች፡፡

እነዚህን 18 ቀበሌዎችና ከተሞችን ዳግም ከኤሌክትሪክ ጋር ለማገናኘት በተሰራው ስራ ከ78 ኪ.ሜ በላይ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና ጥገና እንዲሁም 19 ትራንስፎርመሮችን መተካት ተችሏል፡፡

በወላጋ ዞኖች በእስካሁኑ ስራ በዞኖቹ ከ85 በላይ ከተሞችና ቀበሌዎች ዳግም ወደ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲመለሱ መደረጉን  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።

ሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️