Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በከተማዋ በክረምት በጎ ፍቃድ 250 የአረጋውያን ቤቶች እድሳትና ግንባታ ሥራ ተጀምሯል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በሀዋሳ ከተማ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 250 የአረጋውያን እና የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች እድሳትና ግንባታ ሥራ መጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ።

የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በከተማዋ በዘንድሮ በ2016 ዓ.ም ክረምት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት 250ሺህ ዜጎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ከሚከናወኑት የበጎ ፍቃድ ሥራዎች ውስጥ አንዱ በሰው ተኮር ተግባራት የአረጋውያን ቤቶች እድሳትና ግንባታ መሆኑን የጠቆሙት አቶ መኩሪያ፤ በያዝነው ክረምት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የ250 ቤቶች ግንባታና እድሳት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132870
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
***************
(ኢ ፕ ድ)
የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 6ኛ ምርጫ ጊዜ 3ኛ የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን በጋምቤላ ከተማ በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው በሚኖረው ቆይታ የክልሉን የ2016 በጀት ዓመት የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የስራ ክንውን ሪፖርት አድምጦ ያጸድል ተብሎም ይጠበቃል።
በጉባዔው የ2017 በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ፣ የማስፈፀሚያ በጀትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ይሰጣል።

በጉባዔው ላይ የምክር ቤቱ አባላትን ጨምሮ ከ350 በላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የአመራር አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በጉባኤው መክፈቻ ላይ በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት አባላት የዜጎችን የልማት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ አሳሰስበዋል።

አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ባንቻየሁ እንደገለፁት፣ ምክር ቤቱ ለክልሉ ሰላምና ልማት መረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። በክልሉ ተከስቶ የነበረው የሰላም መደፍረስ ዜጎች በሰላም ወጥተው መግባት እንዳይችሉ ስጋት ውስጥ አስገብቶ የነበረ ቢሆንም መንግስትና ሕዝቡ በተለያዩ መድረኮች ውይይት አድርገው ለማስተካከል ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይም በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት አባላት የዜጎችን የልማት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ኡዶል በበኩላቸው የክልሉ ሕዝብ የሚያነሷቸውን የልማትና የሰላም ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የምክር ቤቱ ሚና የላቀ እንደነበር ገልጸው፣ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በሚያደርጉት ክትትልና ቁጥጥር ስራ ሲከናወኑ የነበሩ ልማቶችን መገምገም ተችሏል ብለዋል ሲል መጀመሩን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽህፈት ቤት ዘግቧል።
ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም
1
የትግራይ ክልል የተደራጁ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየሠራ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅና ሰላምን ለማረጋገጥ የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ ሥራ መግባቱን በትግራይ ክልል የጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፤ የትግራይን ሰላም እና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሥራዎች ተጀምረዋል። በመሆኑም መቐለ ከተማ ላይ ማዕከል ያደረጉ የዝርፊያ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር ግብረሃይሉ ተቀናጅቶ በመሥራት ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሠራ ነው።

በከተማው ከ2013 ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም የተሰሩ ከባድ ወንጀሎችን በተመለከተ የምስል ማስረጃ መያዙን በመጥቀስ፤ እነዚህን ወንጀለኞች ወደ ሕግ ለማቅረብ በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሥራ መጀመሩን አመልክተዋል።

በተለይ ከመሬት ወረራ ጋር ተያይዞ ግልፅ መረጃ መያዙንና መሬት መሸጥ እና መለወጥ እንዲቆም
ሙሉውን ለማንብብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132914
በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ቀልጣፋ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለመስጠት ያግዛል ተባለ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ከተጠሪ ተቋማት ጋር እየገመገመ ይገኛል።

በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ቆንጂት ደበላ በወቅቱ እንደገለጹት፦ በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ቀልጣፋ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለመስጠት ያግዛል።

በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ የማዘጋጀታዊ አገልግሎቶች አበረታች ውጤት ተገኘቷል ብለዋል።
በከተማዋ ሊያጋጥሙ የሚችል እሳትና አደጋ ጠንካራ የቅድመ መከላከል ሰራ በመሰራቱ ጉዳቶችን መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል።

የጽዳት ኤጀንሲ የከተማውን ነዋሪና ባለድርሻ አካል በማሳተፍ ጽዱና ማራኪ ከተማ ለመፍጠር ባከናወነው ተግባር አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።

በሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ተቋማትን በሰው ኃይል፣ በአሰራር፣ በአደረጃጀት እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፋ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ጠቁመዋል።

በኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል በተከናወኑ ስራዎች የከተማዋን ገጽታ መቀየር መቻሉን ገልጸው በቀጣይ ቀሪ ስራዎች ለማከናወን በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

ጽህፈት ቤቱ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት ድጋፍ በማድረግ ለአቅመ ደካማ ዘጎች የቤት እድሳት በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ሲወጣ መቆነቱን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላበረከቱ አካላት እውቅና እደሚሰጥም ተመላክቷል።
በአማን ረሺድ
ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሬት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸ ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል
ድጋፉ የተደረገው የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በግላቸው እያደረጉ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ ነው ተብሏል፡፡
ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም
ለዓባይ ግድብ ግንባታ እስካሁን 20 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ተሰብስቧል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የዓባይ ግድብ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 19 ቢሊዮን 942 ሚሊዮን 519 ሺህ ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ አንድ ቢሊዮን 712 ሚሊዮን 183 ሺህ 820 ብር በላይ መሰብሰቡም ተጠቁሟል።

የፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዓባይ ግድብ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የግድቡ መሠረት ድንጋይ ከተጣለበት ከመጋቢት 2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132941
"ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የተደረገው ምክክር የሚያስተባብሩ አጀንዳዎችን እንድንለይ እድል ሰጥቶናል" የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የተደረገው ምክክር የሚያፎካክሩ አጀንዳዎችን ብቻ ሳይሆን የሚያስተባብሩ አጀንዳዎችን እንድንለይ እድል ሰጥቶናል ሲሉ ኢዜማ እና ትዴፓ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በሀገራዊ ስትራቲጂያዊ ጉዳዮች ላይ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ባካሄዱት ምክክር የተሳተፉት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ምክክሩ የሚያፎካክሩ አጀንዳዎችን ብቻ ሳይሆን የሚያስተባብሩ አጀንዳዎችን ለመለየት ዕድል የሚሰጥ ነው።

ሀገር የፖለቲካ ሥሪት ነው ያሉት አርክቴክት ዮሐንስ፤ ፖለቲካ ደግሞ ብዝሃ ሃሳብና አመለካከቶች የሚንጸባረቁበት መሆኑን ጠቅሰው ስለዚህ የተለያዩ አመለካከቶችና ብዝሃ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132932
ከ16 ሺህ በላይ የካንሰር ህሙማን የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የካንሰር ማዕከሉ 16 ሺህ 600 ለሚሆኑ ተመላላሽ እና ተኝቶ ታካሚ የካንሰር ህሙማን አገልግሎት መስጠት መቻሉን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አስታወቀ።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የካንሰር ህክምና ማዕከል ኃላፊና የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር መሀመድ ኢብራሂም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ የቅዱስ ጳውሎስ የካንሰር ህክምና ማዕከል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ16 ሺህ
600...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132976
በክልሉ ከ12 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
በአማራ ክልል ከ12 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሲስተር ክሽን ወልዴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በክልሉ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥርን ለማሳደግ ሰፊ ተሠርቷል፡፡ በዚህም በክልሉ ከ12 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በጤና መድህን ታቅፎ አገልግሎት እያገኘ ነው፡፡

በ2016 በጀት ዓመት ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ተገልጋዮች የምዝገባና እድሳት አገልግሎት የተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ 218 ሺህ 406 ያህሉ በአዲስ የተመዘገቡ የጤና መድህን አባላት መሆናቸውን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132961
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 700 ሺህ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት 700 ሺህ ወጣቶች እየተሳተፉ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ገለጸ። አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪዎችም በመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በዘንድሮ ክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት 14 ዘርፎችን በመለየት ወደ ሥራ ተገብቷል።

በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ 700 ሺህ ወጣቶችና በጎ ፍቃደኛ ማህበረሰቦች እየተሳተፉ መሆኑን የጠቆሙት አቶ የሺዋስ፤ በሚሰጠው አገልግሎት አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ሕዝብ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132934
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
ኢትዮጵያ የወንዞች ሀገር ናት!
የተፋሰስ ምክር ቤትን በፀሀፊነት ከሚመሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደናል፡፡

በውይይታችንም በኢትዮጵያ ተፋሰሶች ገፅታ ተግዳሮቶችና ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገናል፡፡

በቀጣይ ሀገሪቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ የተቀናጀ የውሀ ሀብት አስተዳደርን ለመገንባት በምክር ቤት ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሊሰሩ በሚገባቸው ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ ተወያይተን መግባባት ላይ ደርሰናል፡፡
ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓም
ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ ድጋፍ እንዲኖር ይሠራል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
እ.አ.አ ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2025 በስፔን የሚካሄደው 4ኛው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ተጠናቋል።

ላለፉት አምስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ጉባኤ መጠናቀቁን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊና የ4ኛው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ሊ ጁንዋ እንደገለጹት፣ ዘላቂ የልማት ግብን ለማሳካት የፋይናንስ ድጋፍ ወሳኝነት አለው።

በጉባኤው ላይ ቀጣይነት ያለው እድገትን ለማረጋገጥ ፋይናንስ ችግር መሆኑን ተወያይተናል ያሉት ጸሀፊው፤ በቀጣይ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት አስተማማኝ ፋይናንስ እንዲያገኙ ለማድረግ የጋራ ስራዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል።

አለም አቀፍ ጫናዎች የፋይናንስ አቅርቦት ላይ አሉታዊ አስተዋጽኦ አላቸው ያሉት ጸሀፊው፤ ይህም ድህነት ቅነሳና ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከዘጠኝ አመት በፊት በሶስተኛው አለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ላይ የተፈረመውን የአዲስ አበባ የድርጊት መርሃ ግብር ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ። በዚህም ያሉ ክፍተቶችን በመገምገም ለማስተካከል ይሰራል ብለዋል።

አለም አቀፍ የፋይናንስ ፍሰትን ለማመጣጠን መተማመንና መተባበር አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።
ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንግስት ለነበረው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በጉባኤው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት፣ ከአህጉራዊና አለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ከሲቭል ማህበራት ከ850 በላይ ተሳታፊዎች መታደማቸውን ገልጸዋል።
በሞገስ ጸጋዬ
ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ ተመዘገበ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዓመታዊ ጉባዔ የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሶስት መስፈርቶችን በማሟላት የዓለም ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል።

የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ለጉባኤው በላኩት የፅሁፍ መልእክት ይህ ቅርስ የተመዘገበው ሉሲ የተገኘችበትን 50ኛ አመት በምናከብርበት ወቅት መሆኑ ለሀገራችን ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልፀዋል::

ይህ ቅርስ ተጠብቆ እንዲቆይም የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል::
መልካ ቁንጡሬ ባልጪት ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጂራ በሚወስደው ጎዳና 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አዋሽ ወንዝ ዳርቻ ላይ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ቋሚ የሚዳሰሱ ቅርሶች 12ኛው ነው፡፡

ሥፍራውን በዓለም ቅርስነት ያበቁት መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ከ2.5 ሚሊየን ዓመት እስከ መጨረሻው የድንጋይ ዘመን የሰው ልጅ ይጠቀምባቸው የነበሩ የድንጋይ መገልገያዎች ይዞ የሚገኝ በመሆኑ፡፡
- እስከ 2.5 ሚሊየን ዓመት እድሜ ያላቸው የተለያዩ የሰውና የእንስሳት ቅሪተ አካሎች በብዛት የሚገኙበት በመሆኑ::

- የሰው ልጅ ከድንጋይ የተለያዩ መገልገያዎችን (መሳሪያዎችን) ይሰራ እንደ ነበር የሚያሳዩ ስምንት የባልጩትና ሌሎች የድንጋይ መሳሪያ ማምረቻ ሥፍራዎችን ይዞ የሚገኝ በመሆኑ የሚሉት ናቸው፡፡
👍1