Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሬት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸ ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል
ድጋፉ የተደረገው የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በግላቸው እያደረጉ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ ነው ተብሏል፡፡
ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም
ለዓባይ ግድብ ግንባታ እስካሁን 20 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ተሰብስቧል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የዓባይ ግድብ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 19 ቢሊዮን 942 ሚሊዮን 519 ሺህ ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ አንድ ቢሊዮን 712 ሚሊዮን 183 ሺህ 820 ብር በላይ መሰብሰቡም ተጠቁሟል።

የፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዓባይ ግድብ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የግድቡ መሠረት ድንጋይ ከተጣለበት ከመጋቢት 2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132941
"ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የተደረገው ምክክር የሚያስተባብሩ አጀንዳዎችን እንድንለይ እድል ሰጥቶናል" የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የተደረገው ምክክር የሚያፎካክሩ አጀንዳዎችን ብቻ ሳይሆን የሚያስተባብሩ አጀንዳዎችን እንድንለይ እድል ሰጥቶናል ሲሉ ኢዜማ እና ትዴፓ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በሀገራዊ ስትራቲጂያዊ ጉዳዮች ላይ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ባካሄዱት ምክክር የተሳተፉት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ምክክሩ የሚያፎካክሩ አጀንዳዎችን ብቻ ሳይሆን የሚያስተባብሩ አጀንዳዎችን ለመለየት ዕድል የሚሰጥ ነው።

ሀገር የፖለቲካ ሥሪት ነው ያሉት አርክቴክት ዮሐንስ፤ ፖለቲካ ደግሞ ብዝሃ ሃሳብና አመለካከቶች የሚንጸባረቁበት መሆኑን ጠቅሰው ስለዚህ የተለያዩ አመለካከቶችና ብዝሃ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132932
ከ16 ሺህ በላይ የካንሰር ህሙማን የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የካንሰር ማዕከሉ 16 ሺህ 600 ለሚሆኑ ተመላላሽ እና ተኝቶ ታካሚ የካንሰር ህሙማን አገልግሎት መስጠት መቻሉን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አስታወቀ።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የካንሰር ህክምና ማዕከል ኃላፊና የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር መሀመድ ኢብራሂም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ የቅዱስ ጳውሎስ የካንሰር ህክምና ማዕከል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ16 ሺህ
600...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132976
በክልሉ ከ12 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
በአማራ ክልል ከ12 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሲስተር ክሽን ወልዴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በክልሉ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥርን ለማሳደግ ሰፊ ተሠርቷል፡፡ በዚህም በክልሉ ከ12 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በጤና መድህን ታቅፎ አገልግሎት እያገኘ ነው፡፡

በ2016 በጀት ዓመት ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ተገልጋዮች የምዝገባና እድሳት አገልግሎት የተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ 218 ሺህ 406 ያህሉ በአዲስ የተመዘገቡ የጤና መድህን አባላት መሆናቸውን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132961
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 700 ሺህ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት 700 ሺህ ወጣቶች እየተሳተፉ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ገለጸ። አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪዎችም በመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በዘንድሮ ክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት 14 ዘርፎችን በመለየት ወደ ሥራ ተገብቷል።

በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ 700 ሺህ ወጣቶችና በጎ ፍቃደኛ ማህበረሰቦች እየተሳተፉ መሆኑን የጠቆሙት አቶ የሺዋስ፤ በሚሰጠው አገልግሎት አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ሕዝብ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132934
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
ኢትዮጵያ የወንዞች ሀገር ናት!
የተፋሰስ ምክር ቤትን በፀሀፊነት ከሚመሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደናል፡፡

በውይይታችንም በኢትዮጵያ ተፋሰሶች ገፅታ ተግዳሮቶችና ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገናል፡፡

በቀጣይ ሀገሪቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ የተቀናጀ የውሀ ሀብት አስተዳደርን ለመገንባት በምክር ቤት ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሊሰሩ በሚገባቸው ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ ተወያይተን መግባባት ላይ ደርሰናል፡፡
ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓም
ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ ድጋፍ እንዲኖር ይሠራል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
እ.አ.አ ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2025 በስፔን የሚካሄደው 4ኛው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ተጠናቋል።

ላለፉት አምስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ጉባኤ መጠናቀቁን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊና የ4ኛው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ሊ ጁንዋ እንደገለጹት፣ ዘላቂ የልማት ግብን ለማሳካት የፋይናንስ ድጋፍ ወሳኝነት አለው።

በጉባኤው ላይ ቀጣይነት ያለው እድገትን ለማረጋገጥ ፋይናንስ ችግር መሆኑን ተወያይተናል ያሉት ጸሀፊው፤ በቀጣይ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት አስተማማኝ ፋይናንስ እንዲያገኙ ለማድረግ የጋራ ስራዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል።

አለም አቀፍ ጫናዎች የፋይናንስ አቅርቦት ላይ አሉታዊ አስተዋጽኦ አላቸው ያሉት ጸሀፊው፤ ይህም ድህነት ቅነሳና ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከዘጠኝ አመት በፊት በሶስተኛው አለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ላይ የተፈረመውን የአዲስ አበባ የድርጊት መርሃ ግብር ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ። በዚህም ያሉ ክፍተቶችን በመገምገም ለማስተካከል ይሰራል ብለዋል።

አለም አቀፍ የፋይናንስ ፍሰትን ለማመጣጠን መተማመንና መተባበር አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።
ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንግስት ለነበረው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በጉባኤው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት፣ ከአህጉራዊና አለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ከሲቭል ማህበራት ከ850 በላይ ተሳታፊዎች መታደማቸውን ገልጸዋል።
በሞገስ ጸጋዬ
ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ ተመዘገበ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዓመታዊ ጉባዔ የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሶስት መስፈርቶችን በማሟላት የዓለም ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል።

የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ለጉባኤው በላኩት የፅሁፍ መልእክት ይህ ቅርስ የተመዘገበው ሉሲ የተገኘችበትን 50ኛ አመት በምናከብርበት ወቅት መሆኑ ለሀገራችን ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልፀዋል::

ይህ ቅርስ ተጠብቆ እንዲቆይም የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል::
መልካ ቁንጡሬ ባልጪት ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጂራ በሚወስደው ጎዳና 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አዋሽ ወንዝ ዳርቻ ላይ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ቋሚ የሚዳሰሱ ቅርሶች 12ኛው ነው፡፡

ሥፍራውን በዓለም ቅርስነት ያበቁት መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ከ2.5 ሚሊየን ዓመት እስከ መጨረሻው የድንጋይ ዘመን የሰው ልጅ ይጠቀምባቸው የነበሩ የድንጋይ መገልገያዎች ይዞ የሚገኝ በመሆኑ፡፡
- እስከ 2.5 ሚሊየን ዓመት እድሜ ያላቸው የተለያዩ የሰውና የእንስሳት ቅሪተ አካሎች በብዛት የሚገኙበት በመሆኑ::

- የሰው ልጅ ከድንጋይ የተለያዩ መገልገያዎችን (መሳሪያዎችን) ይሰራ እንደ ነበር የሚያሳዩ ስምንት የባልጩትና ሌሎች የድንጋይ መሳሪያ ማምረቻ ሥፍራዎችን ይዞ የሚገኝ በመሆኑ የሚሉት ናቸው፡፡
👍1
አመታዊው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የተከበረው አመታዊው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የጋራ ፀጥታ ግብረ ኃይል ገለጸ።

በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ መከላከያ ሠራዊት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምሥራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የድሬዳዋ ፖሊስ፣ የምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ፖሊስ፣ የሐረሪ ክልል ፖሊስ፣ የምስራቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ እንዲሁም የሚሊሻ ኃይሉ ጋር የጋራ ዕቅድ በማውጣትና ከቤተክርስቲያኗ አባቶች ጋር በመምከር ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በዓሉ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ግብረ ኃይሉ ገልጿል፡፡

በዓሉን ለማክበር በመጡ ምዕመናን ላይ አንዳንድ የሞባይል ስርቆት ወንጀል በፈፀሙ አካላት ላይ በተቋቋመው ፈጣን ችሎት አማካኝነት ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስከ አንድ አመት ከስምንት ወር የሚደርስ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን የጋራ ፀጥታ ግብረ-ኃይሉ ገልጿል ሲል የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አስታውቋል።
ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን፣ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን አውጇል።
ከስህተቱ የማይማረው ኦሊምፒክ ኮሚቴ ‼️

በታላቁ የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነስርአት ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። በብዙ ሚሊየን የሚቆጠር የአለም ህዝብ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት በሚከታተለው የመክፈቻ ስነስርአት አገራት ራሳቸውን ለማስተዋወቅ ከአለባበስ ጀምሮ የተለየ ነገር ይዘው ይቀርባሉ።

ኢትዮጵያ በበርካታ የኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነስርአቶች ከአበበ ቢቂላ ጀምሮ፣ በምሩፅ ይፍጠር፣ ደራርቱ ቱሉና ኃይሌ ገብረስላሴን በመሳሰሉ የኦሊምፒክ ጀግኖች በተለያየ ጊዜ ሰንደቅአላማ ይዘው ከፊት በመምራት ያሸበረቀችበት አጋጣሚ ብዙ ነው። ይሁን እንጂ ካለፉት ሁለት ኦሊምፒኮች ወዲህ በኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነስርአት ላይ ይህ ባህል ችላ ሲባል እየታየ ነው።
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዘንድሮም ከስህተቱ መማር የፈለገ አይመስልም።
በምሽቱ  ኦሊምፒክ መክፈቻ ስነ-ስረዓት ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የሚይዙ አትሌቶች የተለዩ ሲሆን፣ እልፍ የኦሊምፒክ ጀግኖች ያሏት አገር ሰንደቅ አላማዋን አንግበው ከፊት እንዲመሩ የተመረጡት በመድረኩ ስም የሌላቸው ሆነዋል።
የኢትዮጵያን ሰንደቅ የሚይዙት የ20 ኪሎ ሜትር ርምጃ ተወዳዳሪው አትሌት ምስጋና ዋቁማ እና የ50 ሜትር የነፃ ቀዘፋ ውሃ ዋና ተወዳዳሪዋ ሊና አለማየሁ መሆናቸው ታውቋል።
ሰንደቅ አላማውን ጀግናውና የማራቶን ቡድኑን የሚመራው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ መያዝ አለበት የሚል ተደጋጋሚ አስታየት ቢሰጥም፣ ማራቶን የሚከናወነው የፍፃሜው እለት በመሆኑና ይህም ለአትሌቱ ዝግጅት ምቹ ባለመሆኑ ቀድመው ፓሪስ በገቡት አትሌቶች እንዲያዘ ተደርጓል። ስፍር ቁጥር የሌላቸው የኦሊምፒክ ጀግኖች ባሏት አገር ይህ ጉዳይ ቀድሞውንም እንደሚከሰት እየታወቀ ሌላ የተሻለ አማራጭ ለመውሰድ አለመቻሉ ግን ኦሊምፒክ ኮሚቴውን በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ  ትዝብት ላይ የሚጥለው ነው።