አመታዊው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የተከበረው አመታዊው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የጋራ ፀጥታ ግብረ ኃይል ገለጸ።
በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ መከላከያ ሠራዊት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምሥራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የድሬዳዋ ፖሊስ፣ የምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ፖሊስ፣ የሐረሪ ክልል ፖሊስ፣ የምስራቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ እንዲሁም የሚሊሻ ኃይሉ ጋር የጋራ ዕቅድ በማውጣትና ከቤተክርስቲያኗ አባቶች ጋር በመምከር ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በዓሉ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ግብረ ኃይሉ ገልጿል፡፡
በዓሉን ለማክበር በመጡ ምዕመናን ላይ አንዳንድ የሞባይል ስርቆት ወንጀል በፈፀሙ አካላት ላይ በተቋቋመው ፈጣን ችሎት አማካኝነት ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስከ አንድ አመት ከስምንት ወር የሚደርስ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን የጋራ ፀጥታ ግብረ-ኃይሉ ገልጿል ሲል የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አስታውቋል።
ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

ከስህተቱ የማይማረው ኦሊምፒክ ኮሚቴ ‼️
በታላቁ የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነስርአት ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። በብዙ ሚሊየን የሚቆጠር የአለም ህዝብ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት በሚከታተለው የመክፈቻ ስነስርአት አገራት ራሳቸውን ለማስተዋወቅ ከአለባበስ ጀምሮ የተለየ ነገር ይዘው ይቀርባሉ።
ኢትዮጵያ በበርካታ የኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነስርአቶች ከአበበ ቢቂላ ጀምሮ፣ በምሩፅ ይፍጠር፣ ደራርቱ ቱሉና ኃይሌ ገብረስላሴን በመሳሰሉ የኦሊምፒክ ጀግኖች በተለያየ ጊዜ ሰንደቅአላማ ይዘው ከፊት በመምራት ያሸበረቀችበት አጋጣሚ ብዙ ነው። ይሁን እንጂ ካለፉት ሁለት ኦሊምፒኮች ወዲህ በኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነስርአት ላይ ይህ ባህል ችላ ሲባል እየታየ ነው።
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዘንድሮም ከስህተቱ መማር የፈለገ አይመስልም።
በምሽቱ ኦሊምፒክ መክፈቻ ስነ-ስረዓት ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የሚይዙ አትሌቶች የተለዩ ሲሆን፣ እልፍ የኦሊምፒክ ጀግኖች ያሏት አገር ሰንደቅ አላማዋን አንግበው ከፊት እንዲመሩ የተመረጡት በመድረኩ ስም የሌላቸው ሆነዋል።
የኢትዮጵያን ሰንደቅ የሚይዙት የ20 ኪሎ ሜትር ርምጃ ተወዳዳሪው አትሌት ምስጋና ዋቁማ እና የ50 ሜትር የነፃ ቀዘፋ ውሃ ዋና ተወዳዳሪዋ ሊና አለማየሁ መሆናቸው ታውቋል።
ሰንደቅ አላማውን ጀግናውና የማራቶን ቡድኑን የሚመራው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ መያዝ አለበት የሚል ተደጋጋሚ አስታየት ቢሰጥም፣ ማራቶን የሚከናወነው የፍፃሜው እለት በመሆኑና ይህም ለአትሌቱ ዝግጅት ምቹ ባለመሆኑ ቀድመው ፓሪስ በገቡት አትሌቶች እንዲያዘ ተደርጓል። ስፍር ቁጥር የሌላቸው የኦሊምፒክ ጀግኖች ባሏት አገር ይህ ጉዳይ ቀድሞውንም እንደሚከሰት እየታወቀ ሌላ የተሻለ አማራጭ ለመውሰድ አለመቻሉ ግን ኦሊምፒክ ኮሚቴውን በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ትዝብት ላይ የሚጥለው ነው።

ለመሬት ናዳ ስጋት ዘላቂ መፍትሄ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
ሰሞኑን ኢትዮጵያ የከፋ የመሬት መንሸራረት አደጋን አስተናግዳለች። ከሀገር መሪዎች አንስቶ በርካቶች ኀዘናቸውንም እየገለጹ ይገኛል። በደረሰው ድንገተኛ የሆነ የመሬት ናዳ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የሚውል ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።
የጎፋ ዞን አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በ8091 ድጋፍ እያሰባሰቡ እንደሚገኙ ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል። ለወገን ደራሽ ወገን ነው ከሚለው የድጋፍ መርህ ባለፈ ግን ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ምን አይነት ሥራ ያስፈልጋል የሚለው የወቅቱ ጥያቄ ነው።
የመሬት ናዳ አደጋ እንዴት ይከሰታል፣ ስጋቱን ለመቀነስ ምን አይነት ሥራዎች ያስፈልጋሉ? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ምሁራን ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ሳይንስ ምሁር ፕሮፌሰር ሞሐመድ ሃሰን፤ ከሰሞኑ በጎፋ ዞን ፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=133028

”ኢትዮጵያ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ሆና የሌሎችን እጅ መጠበቅ የለባትም”
-ነገሰ ነገዎ የገዳ ቱለማ ሐዩ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ሆና የሌሎች ሀገራትን እጅ መጠበቅ የለባትም ሲሉ የገዳ ቱለማ ሐዩ ነገሰ ነገዎ አስታወቁ፡፡
በተፈጥሮ ጸጋው ለመጠቀም ትውልዱ ለሥራ መትጋት እንደሚጠበቅበትም አመለከቱ፡፡
የገዳ ቱለማ ሐዩ ነገሰ፣ ከኢፕድ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ናት፡፡ በአብዛኛው ሊታረስ የሚችል መሬትም አላት፡፡
ይህን በተፈጥሮ የተቸረችውን ጸጋ ይዛ የሌሎች ሀገራትን ርዳታ መጠበቅ የለባትም፡፡
አሁን ጊዜው እንደድሮ አይደለም ያሉት ሐዩ ነገሰ፣ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ትከተለው የነበረ የአስተራረስ ዘዴ ምናልባት የሌሎችን ርዳታ እንድትጠብቅና አልፋም እንድትለምን ያስደረጋት ነበር ብለዋል፡፡
ምክንያቱም ድሮ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ይታረስ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=133024

በጎንደርን የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄ መመለሱን ምክንያት በማድረግ የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በጎንደር ከተማ መንግሥት ለልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ያሳየውን ቁርጠኝነት የሚደግፍ እና ያሉ ችግሮች ተሻሽለው አስተማማኝ ሰላም እንዲመጣ የሚጠይቅ ሰልፍ ተካሄደ።
"ለሰላም ዘብ እንቆማለን፤ የተጀመሩ ልማቶችን እናስቀጥላለን" በሚል መሪ ሃሳብ በድጋፍ ሰልፉ ሕዝቡ ዘላቂ ሰላም እና ልማትን ለማምጣት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያስቀጥል ተመላክቷል።
በሰላማዊ ሰልፉ "የጎንደር እና አካባቢው የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን፣ እሳቸው የሚመሩት ፖርቲ እና መንግሥት ያሳዩንን ቁርጠኝነት እውቅና እንሰጣለን" የሚሉና ሌሎች ሃሳቦች መገለጻቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም

የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በመሬት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 75 ቶን ምግብ ነክና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገች
****
(ኢ.ፕ.ድ)
- አደጋው ከደረሰ ጀምሮ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 75 ቶን ምግብ ነክና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጓን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
አደጋው ከደረሰ ጀምሮ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉም ተመላክቷል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን ለመደገፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫውም የመሬት ናዳ አደጋው መድረሱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች የማጽናናት፣ ድጋፍ የማድረግ እና ሌሎች ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውቀዋል።
በዛሬው ዕለት የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በመሬት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ የሚሆን 75 ቶን ምግብ ነክና ሌሎች ቁሳቁሶችን መላኩንና ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መድረሱን ገልጸው፤ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ተረክቦ በቀጥታ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ይላካል ብለዋል።
በሌላ በኩል በክልሎች፣ በከተማ አስተዳድሮች፣ በአጋር ድርጅቶች፣ በባለሀብቶች፣ በግለሰቦች እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ያደረጉት ድጋፍ በዓይነትና በገንዘብ ሲተመን 60 ሚሊዮን መሆኑን ተናግረዋል።
በሔለን ወንድምነው