Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በጎንደርን የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄ መመለሱን ምክንያት በማድረግ የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በጎንደር ከተማ መንግሥት ለልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ያሳየውን ቁርጠኝነት የሚደግፍ እና ያሉ ችግሮች ተሻሽለው አስተማማኝ ሰላም እንዲመጣ የሚጠይቅ ሰልፍ ተካሄደ።

"ለሰላም ዘብ እንቆማለን፤ የተጀመሩ ልማቶችን እናስቀጥላለን" በሚል መሪ ሃሳብ በድጋፍ ሰልፉ ሕዝቡ ዘላቂ ሰላም እና ልማትን ለማምጣት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያስቀጥል ተመላክቷል።

በሰላማዊ ሰልፉ "የጎንደር እና አካባቢው የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን፣ እሳቸው የሚመሩት ፖርቲ እና መንግሥት ያሳዩንን ቁርጠኝነት እውቅና እንሰጣለን" የሚሉና ሌሎች ሃሳቦች መገለጻቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን አደጋው በደረሰበት ሥፍራ በመገኘት አጽናንተዋል፡፡
ሐምሌ 201 ቀን 2016 ዓም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በመሬት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 75 ቶን ምግብ ነክና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገች
****
(ኢ.ፕ.ድ)

- አደጋው ከደረሰ ጀምሮ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል

የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 75 ቶን ምግብ ነክና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጓን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

አደጋው ከደረሰ ጀምሮ 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉም ተመላክቷል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን ለመደገፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም የመሬት ናዳ አደጋው መድረሱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች የማጽናናት፣ ድጋፍ የማድረግ እና ሌሎች ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውቀዋል።

በዛሬው ዕለት የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በመሬት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ የሚሆን 75 ቶን ምግብ ነክና ሌሎች ቁሳቁሶችን መላኩንና ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መድረሱን ገልጸው፤ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ተረክቦ በቀጥታ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ይላካል ብለዋል።

በሌላ በኩል በክልሎች፣ በከተማ አስተዳድሮች፣ በአጋር ድርጅቶች፣ በባለሀብቶች፣ በግለሰቦች እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ያደረጉት ድጋፍ በዓይነትና በገንዘብ ሲተመን 60 ሚሊዮን መሆኑን ተናግረዋል።

በሔለን ወንድምነው
ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እስካሁን የ231 ዜጎችን ሕይወት እንደቀጠፈ በተረጋገጠው የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብ በአካል ለማፅናናት በስፍራው ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ ከቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ከሌሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት አመራሮች ጋር በስፍራው ሲገኙ በክልል ሃላፊዎች እና በማህበረሰቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም