Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጋርዲያን ሽልድ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ከገበያ ታገደ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
ከደረጃ በታች የሆነ እና ምንጩ ያልታወቀ ጋርዲያን ሽልድ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ በገበያ ላይ እንዳይውል መታገዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባካሄደው የገበያ ኢንስፔክሽን ጋርዲያን ሽልድባለ 6 ቀዳዳ outlet for የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ከጥራት ደረጃ በታች መሆኑ ስለተረጋገጠ እና ምንጩ ያልታወቀ ሆኖ በመገኘቱ ገበያ ላይ እንዳይውል ታግዷል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም እያሳሰበ ማንኛውም ነጋዴ ሲሸጥ ቢገኝ ከፍትህ ተቋማት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ መግለፁን ከሚንስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሐምሌ 24 /2016 ዓ.ም
የውሃ ዲፕሎማሲው ፍሬ
***********
(ኢ ፕ ድ)
ከ 11 የናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ዩጋዳንዳ፣ ብሩንዲና ደቡብ ሱዳን የናይል ትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ተቀብለው በፓርላማ አጽድቀዋል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን ጨምሮ የላይኛው የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው፡፡ ይህ ማዕቀፍ በቅኝ ግዛት ወቅት የተፈረሙ ስምምነቶች ትርጉም እንዳይኖራቸው ያደርጋል፡፡

ግብጽ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤትና በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን ለመክሰስ ስታደርግ የነበረውን ጥረትም ምክንያት እንደሚያሳጣት የዘርፉ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡

የተፋሰስ ሀገራት ውሃን በጋራ ማልማት፣ መጠቀምና በጋራ ማስተዳደር እንዳለባቸው የናይል ትብብር ማዕቀፍ ሰነድ ያረጋግጣል፡፡ ይሁንና የውሃ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንዳትሆንና ማዕቀፉም በአባል ሀገራቱ እንዳይጸድቅ ግብጽ የቻለችውን ሁሉ ጥረት ስታደርግ መቆየቷ ይታወቃል፡፡

በናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መሠረት ስድስት ሀገራት ከፈረሙ የውሃ አስተዳደር ኮሚሽኑ ይቋቋማል፡፡ የናይል ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መጽደቁና የኢትዮጵያን ውጤታማ የዲፕሎማሲ ጉዞን በተመለከተ የድንበር
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=133317
👍1
#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ የአፍሪካ ኩራት‼️

የአፍሪካ መዳረሻዎች ‼️
በቅርብ ጊዜ ለተሾሙት አምባሳደሮች ላለፉት ሳምንታት ሲካሄድ የነበረውን ስልጠና ተከትሎ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው አምባሳደሮቹን አግኝተዋል።

ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም
ትኩረት የሚሻው የኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያን ቀጣይነት ያለው የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ሥራ አሁንም ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል። ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በምታደርገው ትግል እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችና መፍትሄዎች ላይም ምሁራን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ኮሌጅ ፕሮፌሰር የሆኑት በላይ ስማኔ እንደሚሉት፤ ባለፉት ዓመታት በግብርናና በምግብ ዋስትና መሻሻል ረገድ መንግሥትም ሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሰፊ ተሳትፎ ቢያደርጉም ኢትዮጵያ የዜጎቿን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት አልቻለችም።

በዓለም አቀፍ የዘርፉ ትርጓሜዎች መሠረት የምግብ ዋስትና ማለት እያንዳንዱ ግለሰብ ሁል ጊዜ በቂ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት አለበት የሚለው ሲሆን፤....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=133354
በ2017 ዓ.ም ሰላምን ለማስፈንና ለማጽናት ትኩረት መስጠቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገለጸ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 ዓ.ም ሰላምን ማስፈንና ማጽናት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።

ርእሰ መስተዳድሩ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሰላምን ለማስፈን የሚደረገው ሂደት እንዳይቀለበስ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል።

በክልሉ ምርታማነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ በመጠቆምም፣ ከተረጂነት ለመውጣት መርሃ ግብር መነደፉን አመልክተዋል። በመጀመሪው ትግበራ 65 በመቶ ለመቀነስ እቅድ መያዙንም ጠቁመዋል።

የህብረተሰቡን ኑሮ ማረጋጋትም በመጪው አመት እቅድ መያዙን ያመለከቱት አቶ እንዳሻው፣ ከሰንበት እስከ ሰንብት አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ገበያዎችን 34 በመጨመር ወደ 138 ለማድረስና የንግድ ስርኣቱን ለመቆጣጠር መታቀዱን ተናግረዋል።

የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጥን፣ በክልሉ የሚነሱ ችግሮችን በእቅዱ በማካተት እየፈታን እንቀጥላለንም ብለዋል።

ዘላለም ግዛው /ሆሳዕና
ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም
ምክር ቤቱ በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት አፀደቀ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ስብሰባው በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት አዋጅ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 3ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጁ ላይ ተወያይቷል፡፡

በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የብድር ሥምምነት ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ ዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር መልካም ውጤት ያስመዘገበውን አገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለመደገፍ ለመጀመሪያው ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የእድገት ልማት ፖሊሲ ማስፈጸሚያ የሚውል 1 ቢሊየን ዶላር እርዳታና 500 ሚሊየን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ መንግሥት ለመስጠት በመስማማቱ ከማኅበሩ ጋር የገንዘብ ድጋፍና የብድር ሥምምነት መፈረሙን ገልጸዋል።

ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር በብድር የተገኘው 500 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመራቸውን የሪፎርም ስራዎች ለመደገፍ እንዲሁም የፌዴራል መንግሥትን የ2017 በጀት በቀጥታ ለመደገፍ የሚውል መሆኑን ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የብድር ስምምነቱን አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ያገኘውን ድጋፍና ብድር የያዘ ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ለፓርላማ አቅርቦ እንደሚያስጸድቅ ጠቁመዋል።

የቀረበው አዋጅ 1345/2016 ሆኖ በአንድ ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

በተስፋ ፈሩ
ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም
1