Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#በካዛንቺስ፣ አዋሬና ቤተመንግስት ዙሪያ #በኮሪደር_ልማትና በመልሶ ማልማት‼️

✍️ 674 በቀበሌ ቤት የሚኖሩ የልማት ተነሺዎች የተለዋጭ መኖሪያ ቤት ዕጣ አውጥተዋል፣

✍️ ከአካባቢዎቹ እስካሁን 1ሺ 218 የቀበሌ ቤቶች መረጃቸው ተጣርቶ ተደራጅቷል፣

✍️ የልማት ተነሺዎች በሂደቱ ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት ስርዓትም ተዘርግቷል፣

መስከረም 11 ቀን 2017 ዓም
በትግራይ ክልል የሰፈነውን ሰላም ጠብቆ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል የተገኘውን ሰላም ጠብቆ ማስቀጠል እንደሚገባና በየደረጃው ያለው አመራር ይህንን ተገንዝቦ መስራት እንዳለበት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ገለፁ።

''ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም'' በሚል መሪ ሃሳብ የዓለም የሰላም ቀን በመቀሌ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

ቀኑን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንትና የሰላምና የፀጥታ ካቤኔ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፌደራል መንግስት ጋር የጀመራቸው ሰላምን የማረጋገጥ ሥራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የተገኘውን ሰላም ጠብቆ እና ተንከባክቦ ለዘላቂነቱ መስራት እንደሚገባ ያመለከቱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ በየደረጃው ያለው አመራርም ይህንን ተገንዝቦ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

በውይይቱ የተሳተፈችው ወጣት ፃድቃን ገብረ እግዚአብሔር ሰላም የሁሉም መሰረት በመሆኑ መጠበቅ አለበት ስትል ገልጻለች።

በግጭት ይበልጥ ለጥቃት ተጋላጭ የሚሆኑ ሴቶችና ህፃናት ናቸው ያለችው ወጣትዋ፤ በዚህም ሰላምን የመጠበቅ ኃላፊነት አለብን ብላለች።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በክልሉ የሰፈነውን ሰላም በማፅናት ልማትና የወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማስቀጠል ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጎን ሆነን እንሰራለን ያለው ደግሞ ወጣት ክብሮም ሰለሞን ነው።

መስከረም 11 ቀን 2017 ዓም
👍1
የህትመት ሚዲያ ተግዳሮቶችን እንዴት ማሻገር ይቻላል?
***
(ኢ ፕ ድ)

.......በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምህርና ተመራማሪ ጌታቸው ጥላሁን (ዶ/ር)፤ የህትመት ሚዲያ ሃሳብን ፣ባህልን፣ ፍልስፍናን፣ እውቀትን፣ ይዘትን በዋናነትም መረጃን ለረዥም ጊዜ በመሰነድ በጽሁፍ የሚያቀርብ ነው ይላሉ፡፡

በሁለተናዊ እድገት ውስጥ የህትመት ዘርፉ ያለው ሚና ቀላል የሚባል አይደለም የሚሉት ጌታቸው ጥላሁን (ዶ/ር)፤ ማህበረሰቡ እውቀቱንና ባህሉን እንዲሁም ማንነቱን እርስ በእርስ የሚጋራበትና የሚያስተላልፍበት መሆኑን ይገልጻሉ።

አንድ ማህበረሰብ የንባብ ባህል ሲኖረውና ያነበበውንም ሲወያይበት አጠቃላይ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የባህል እድገትን ሊያመጣ እንደሚችል ይናገራሉ። ጌታቸው (ዶ/ር)፤ የህትመት ዘርፉ ያሉ ችግሮች በርካታ ናቸው፤ በዋናነት የዲጂታል ሚዲያው እየተበራከተ መምጣት የሚጠቀስ ነው፡፡

የዲጂታል ሚዲያው በአጭር ጊዜ ብዙ መረጃ በተለያዩ አማራጮች ማግኘት የሚቻልበት በመሆኑ የሰዎች ምርጫ መሆን ችሏል፡፡ ይህም የህትመት ዘርፉን በእጅጉ ጎድቶታል ይላሉ፡፡

የህትመት ሚዲያው በተፈጥሮው ጊዜን፣ አስተውሎትን እንዲሁም ጥሞና ይፈልጋል የዲጂታል ሚዲያው ግን በተቃራኒው ነው ሲሉ የሚናገሩት መምህሩ፤ በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ በዲጂታል ሚዲያው ተጽዕኖ ምክንያት ጋዜጦችንም ሆነ ሌሎች የህትመት ውጤቶችን የማንበብ ልምዱ በእጅጉ መቀነሱን ያነሳሉ፡፡

በሌላ በኩል ከህትመት ግብዓቶች የዋጋ መናር፣ የማንበብ ባህል መቀነስ፣ የህትመት ዘርፉን የሚያበረታታ ፖሊሲ አለመኖር ፣ ሃሳብን በነጻነት ያለመጻፍ፣ ለሁሉም እድሜ ክልል የሚሆኑ ህትመቶች አለመኖር....

https://press.et/?p=137101
👍1👎1
#የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል #ዮዮ "#ጊፋታ" ‼️

የወላይታ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች በወላይታ ሶዶ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ የጊፋታ እሴቶችን የሚያስተዋዉቅ አዉደ-ርዕይ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት ተደርጓል።

በዓሉ ያለምንም ልዩነት ሁሉም በጋራ የሚያከብሩበትና የሚደሰቱበት፤ ባህላዊና ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ መከበሩ ለሀገራዊ አንድነት መጠናከር አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ተመላክቷል።

ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወጣጡ የብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች በስፍራው በመገኘት ለበዓሉ ድምቀት መሆናቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

መስከረም 12 ቀን 2017 ዓም
የዘንድሮ ኢሬቻ በዓል መስከረም 25 እና 26 ይከበራል
*****
(ኢ ፕ ድ)

የ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ መስከረም 25 ቀን በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ ፣ መስከረም 26 ቀን ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ እንደሚከበር የኦሮሚያ ሕብረት አባገዳዎች አስታወቀ።

የመጫ አባገዳ እና የኦሮሚያ ሕብረት አባገዳዎች ሰብሳቢ አባገዳ ወርቅነህ ተሬሳ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የኦሮሞ ሕዝብ ከሚያከብራቸው የእርቅና የሰላም ክብረ በዓላት መካከል ኢሬቻ አንዱ ነው። በዓሉም ዘንድሮ መስከረም 25 ቀን በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፣ መስከረም 26 ቀን ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ ይከበራል፡፡

የ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል መስከረም 25 ቀን በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ ፣ መስከረም 26 ቀን ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ እንደሚከበር አመልክተው፤ በዓሉን ለመታደም የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የባህል ልብሳቸውን በመልበስ በዓሉን በፍቅር፣ በአንድነትና በሰላም......

https://press.et/?p=137103
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ፈውስ ያገኙ ልቦች‼️

አክሊለ በቀለ ትባላለች፡፡ ቤተሰቦቿ የልብ ችግር እንዳለባት ያወቁት የስድስት ወር ህጻን እያለች ነው። የነበረብኝ የልብ ህመም የልብ ቀዶ ህክምና ማድረግ እንዳብኝ የሚያስገድድ ነበር የምትለው አክሊለ ከ23 ዓመት በፊት የሁለት ዓመት ከስድስት ወር ህጻን እያለች በእስራኤል ሀገር በሚገኝ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት አማካኝነት የቀዶ የህክምና ማድረጓን ትገልጻለች፡፡

አክሊለ በወቅቱ በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ህክምና ሃኪም አለመኖሩን ገልጻ፤ ነገር ግን የልብ ካርዲዎሎጂስቶች ባደረጉልኝ ህክምና የልብ ችግሩ እንዳብኝና ከሀገር ውጭ ወጥቼ ቀዶ ህክምናውን ማድረግ እንዳብኝ አሳውቀውኛል ትላለች፡፡

ከዛም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አማካኝነት እስራኤል ካለው ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሴቭ ዘ ቺልድረን ጋር መገናኘት በመቻሏ በእስራኤል ሀገር የልብ ቀዶ ህምናውን ማድረጓን ታስታውሳለች፡፡

አሁን ላይ አክሊለ በተደረገላት ህክምና ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ጤነኛ መሆኗንና ነርሲንግ ትምህርት ተምራ በአሁኑ ጊዜ በልብ ቀዶ ህክምና ወቅት ልብና ሳንባን ተክቶ የሚሠራ ማሽን ላይ ለመሥራት የውጭ የትምህርት እድል አግኝታ ለመሄድ ዝግጅት ላይ መሆኗን ተናግራለች፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ወላጆች በዚህ ህመም ምክንያት ከልጆቻቸው ጋር እየተቸገሩ መሆናቸውን የምትገልጸው አክሊለ፤ በኢትዮጵያ ልብ ህሙማ ህጻናት መርጃ ማዕከል ብቻ ከስምንት ሺህ በላይ ህጻናት ወረፋ እየጠበቁ...

https://press.et/?p=137102
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ለናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ትግበራ በጋራ ለመስራት ተሰማሙ
*******
(ኢ ፕ ድ)

በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው የተመድ 79ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ራምዳን ሞሀመድ አብዱላህ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ሁለቱ አገራት በናይል ተፋሰስ ፍትሃዊና እኩል ተጠቃሚነት ላይ ባላቸው ወጥ አቋም ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

አምባሳደር ታዬ ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን በፓርላማ ማፅደቋ የአገሪቱ ሕዝብ በናይል ተፋሰስ በፍትሀዊነትና እኩል ተጠቃሚነት ላይ ያለውን መብት ያስከበረ መሆኑን ገልጸዋል።

በውይይቱ ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ሙሉ ትግበራ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን በፓርላማ አጽድቃ ለአፍሪካ ኀብረት ማቅረቧን ተከትሎ ኡጋንዳ እ.ኤ.አ. በጥቅምት አጋማሽ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን መመሥረት የሚያስችለውን ሁለተኛውን የናይል ጉባዔ ለማዘጋጀት ያሳየችውን ቁርጠኝነት መደገፏ ይታወሳል።
በሮምና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዓባይ ግድብ ከ3200 ዩሮ በላይ አበረከቱ
******
(ኢ ፕ ድ)

በሮምና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዓባይ ግድብ 3250 ዩሮ በቦንድና ስጦታ ሲያበረክቱ፣ 5000 ዩሮ ለመለገስ ቃል ገብተዋል።

በጣሊያን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ፣ ግድብን ለማጠናቀቅም መንግስት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለቀሪ ስራዎች ማጠናቀቂያ ዳያስፖራው ቦንድ እንዲገዛ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መስከረም 12 ቀን 2017 ዓም
በገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት የመንግሥት ሚና
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ በቅርቡ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ ገብታለች። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የዋጋ ንረትን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ይነሳል።

የሀገር ውስጥ ገቢን፣ የፋይናንስ ዘርፉን አካታችነትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግና የውጭ ምንዛሬ መዛባትን ለማስተካከል እንደሚያግዝም ተገልጿል።

ማሻሻያው ሀገሪቱን ወደ ገበያ መር ኢኮኖሚ ሥርዓት ሊያስገባት እንደሚችል ደግሞ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ለመሆኑ ገበያ መር ኢኮኖሚ ሲባል ምን ማለት ነው? በአሁኑ ዘመን ዓለም ላይ በዚህ መንገድ ኢኮኖሚያቸውን የሚያንቀሳቅሱ ሀገራት እነማን ናቸው? ስኬታቸውስ ምን ይመስላል? ስንል ጠይቀናል።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸ (ዶ/ር)፤ ገበያ መር ኢኮኖሚ ሲባል ገበያው ዋጋን እንዲወስን የሚያስችል ነው። ባለሀብቶች የሚሳተፉበት፣ ከፍተኛ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=137162
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️