Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጎቤና ሺኖዬ ጨዋታ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው አመታዊ የወጣቶች የዘመን መለወጫ የብስራት የአደባባይ ጨዋታ ጎቤና ሺኖዬ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው።

ጎቤና ሺኖዬ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በአዲስ አበባ ሲከበር ቆይቷል።

ጎቤና ሺኖዬ የተሰኘው የአዲስ ዓመት የአደባባይ የኦሮሞ ወጣት ወንዶችና የልጃገረዶች ጨዋታ (ካርኒቫል) በየዓመቱ በአደባባይ የሚከበር ነው።

በማርቆስ በላይ
መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም
#የዓለም_የቱሪዝም_ቀን

የዓለም የቱሪዝም ቀንን በኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮኗ ኢትዮጵያ ያክብሩ ።
#አንድነትፓርክ ‼️

መቼ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓም ተመረቀ

የት ቤተ መንግስት ግቢ ይገኛል

በምረቃው ላይ ማን ማን ተገኘ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የቀድሞው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ፣ የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት፣ የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ፣ የበርካታ ሀገራት ተወካዮች እና አምባሳደሮች፤ የክልል ፕሬዝዳንቶችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

አንድነት ፓርክን ይጎብኙ
👍1
ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ‼️

ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል በተለያዩ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚገኙ የኮሚኒኬሽን ባለሞያዎችን ያሰባሰበ የመንግሥት የኮሚኒኬሽን ሥራዎችን ለማላቅ ይቻል ዘንድ በ”ዘመናዊ ኮሚኒኬሽን” ላይ ያተኮረ ስልጠና አካሂዷል።

ስልጠናው በመለወጥ ላይ የሚገኘውን የአለም እና የሀገራችን የኮሚኒኬሽን አውድ ተገንዝቦ ስለመንግስት ፖሊሲዎች፣ አገልግሎቶች እና ቁልፍ ሥራዎች ጠቃሚ መረጃዎችን በወቅቱ ማቅረብ ብሎም ለሰፊው ተደራሲ የሕግ ማዕቀፎችን እና በህጎቹ የመመራት መሥፈርቶችን ግልፅ ማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር።

ውጤታማ የተግባቦት ሥራን በቀጣይነት በማሳደግ በመንግሥት ፖሊሲዎች እና የሥራ እንቅስቃሴዎች ላይ በኅብረተሰቡ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚቻል ይጠበቃል።

እነዚህ ጥረቶች መረጃ ያለው እና በሀገራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ የሚያደርግ ዜጋ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ብሎም መንግሥት ለግልፅነት ያለውን ፅኑ አቋም የሚደግፉ ይሆናሉ።

ምንጭ: የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም
የቱሪዝም ዕድገቱ ዕድል
*********
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገቡ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት ናት።

እነዚህ ቅርሶች ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ኃይማኖታዊና ተፈጥሯዊ ይዘታቸው የበርካታ ቱሪስቶችን ቀልብ ከመያዝ ባለፈም የውጭ ምንዛሬ ገቢ በማሳደግ ረገድ አይነተኛ ሚና አላቸው።

በ2016 ዓ.ም በዘጠኝ ወራት ብቻ በቱሪዝም ሦስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ ሆኗል።

በተለይ በመስከረም ወር የሚከበሩት መስቀል፣ ኢሬቻ፣ ፍቼ ጨንበላላና የተለያዩ ብሔሮች የዘመን መለወጫ በዓላት የቱሪዝም ገቢን ከማሳደግ አኳያ ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።

በዓላቱት ለሀገሪቱ የቱሪዝም ዕድገት ያላቸውን ሚና ከማሳደግ አኳያ ፤ ሁነቶቹን ከማስተዋወቅ ፣ቱሪስቶችን በአግባቡ ከመቀበልና የቆይታ ጊዜያቸውን ከማራዘም አኳያ ምን ያህል አይነት ሥራዎች ያስፈልጋሉ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=137115