Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#የዓለም_የቱሪዝም_ቀን

የዓለም የቱሪዝም ቀንን በኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮኗ ኢትዮጵያ ያክብሩ ።
#አንድነትፓርክ ‼️

መቼ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓም ተመረቀ

የት ቤተ መንግስት ግቢ ይገኛል

በምረቃው ላይ ማን ማን ተገኘ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የቀድሞው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ፣ የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት፣ የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ፣ የበርካታ ሀገራት ተወካዮች እና አምባሳደሮች፤ የክልል ፕሬዝዳንቶችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

አንድነት ፓርክን ይጎብኙ
👍1
ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ‼️

ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል በተለያዩ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚገኙ የኮሚኒኬሽን ባለሞያዎችን ያሰባሰበ የመንግሥት የኮሚኒኬሽን ሥራዎችን ለማላቅ ይቻል ዘንድ በ”ዘመናዊ ኮሚኒኬሽን” ላይ ያተኮረ ስልጠና አካሂዷል።

ስልጠናው በመለወጥ ላይ የሚገኘውን የአለም እና የሀገራችን የኮሚኒኬሽን አውድ ተገንዝቦ ስለመንግስት ፖሊሲዎች፣ አገልግሎቶች እና ቁልፍ ሥራዎች ጠቃሚ መረጃዎችን በወቅቱ ማቅረብ ብሎም ለሰፊው ተደራሲ የሕግ ማዕቀፎችን እና በህጎቹ የመመራት መሥፈርቶችን ግልፅ ማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር።

ውጤታማ የተግባቦት ሥራን በቀጣይነት በማሳደግ በመንግሥት ፖሊሲዎች እና የሥራ እንቅስቃሴዎች ላይ በኅብረተሰቡ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚቻል ይጠበቃል።

እነዚህ ጥረቶች መረጃ ያለው እና በሀገራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ የሚያደርግ ዜጋ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ብሎም መንግሥት ለግልፅነት ያለውን ፅኑ አቋም የሚደግፉ ይሆናሉ።

ምንጭ: የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም
የቱሪዝም ዕድገቱ ዕድል
*********
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገቡ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት ናት።

እነዚህ ቅርሶች ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ኃይማኖታዊና ተፈጥሯዊ ይዘታቸው የበርካታ ቱሪስቶችን ቀልብ ከመያዝ ባለፈም የውጭ ምንዛሬ ገቢ በማሳደግ ረገድ አይነተኛ ሚና አላቸው።

በ2016 ዓ.ም በዘጠኝ ወራት ብቻ በቱሪዝም ሦስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ ሆኗል።

በተለይ በመስከረም ወር የሚከበሩት መስቀል፣ ኢሬቻ፣ ፍቼ ጨንበላላና የተለያዩ ብሔሮች የዘመን መለወጫ በዓላት የቱሪዝም ገቢን ከማሳደግ አኳያ ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።

በዓላቱት ለሀገሪቱ የቱሪዝም ዕድገት ያላቸውን ሚና ከማሳደግ አኳያ ፤ ሁነቶቹን ከማስተዋወቅ ፣ቱሪስቶችን በአግባቡ ከመቀበልና የቆይታ ጊዜያቸውን ከማራዘም አኳያ ምን ያህል አይነት ሥራዎች ያስፈልጋሉ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=137115
ጎቤና ሺኖዬ- የመስከረም ሌላኛው ጌጥ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የመስከረም ወር ለኢትዮጵያውያን ባለብዙ መልክ ነው፡፡ የክረምቱ ጭለማ አልፎ ብሩህ ወቅት የሚታይበት፤ አበቦች የሚፈኩበትና ብሩህ ተስፋ የሚለመልምበት፤ በርካታ ብሔረሰቦች አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩበት ወር ነው፡፡ ለአብነትም ኢሬቻ፣ ያ ሆዴ፣ ዮዮ ጊፋታ፣ ዮ ማስቃላ፣ ማሽቃሮ ከብዙ በጥቂቱ ይገኙበታል፡፡

ጎቤና ሺኖዬም ዓመታዊ የኦሮሞ ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች የዘመን መለወጫ የብሥራት የአደባባይ ጨዋታ ነው። ይህ የወጣቶችን ባሕላዊ ክዋኔ የሕዝቦችን አንድነትና ፍቅር የሚያጠናክር የዘመን መለወጫ ባሕላዊ ጨዋታ (ካርኒቫል) መሆኑም ተገልጿል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲምቢሩ ትላንት በተጠናቀቀው ስድስተኛ ዙር ”ጎቤና ሺኖዬ” የወጣቶች የባሕላዊ ጭፈራ ፌስቲቫል ላይ ተገኝተው እንደገለጹት፣ ”ጎቤና ሺኖዬ” ወጣት ወንዶችና ሴቶች ክረምቱ አልፎ የብራ ወቅት መምጣቱን ለማመላከት በባሕላዊ አልባሳት አጊጠው የሚጨፍሩት ባሕላዊ.....

https://press.et/?p=137241
1
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የቢራ ገብስን በዘመናዊ ገበያ ለማገበያየት እየሠራ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)

በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገባውን የቢራ ገብስ ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የቢራ ገብስን በዘመናዊ ግብይት ሥርዓቱ ለማገበያየት እየሠራ መሆኑን አስታወቀ፤ በተጨማሪም ተቋሙ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ባቄላ፣ ኑግና ሽምብራን እንደሚያገበያይ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የስትራቴጂ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ባየልኝ ዘርዓይ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ መንግሥት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ሲገቡ የነበሩትን የኢንዱስትሪ ግብቶችን በሀገር ውስጥ ግብዓት ለመተካት ግልጽ የፖሊሲ አቅጣጫ አስቀምጦ.....

https://press.et/?p=137270
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ከሻይ ቅጠል ምርት ከሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል
****
(ኢ ፕ ድ)

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከአንድ ሺህ 142 ቶን በላይ የሻይ ቅጠል ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳሬክተር ሣሕለማሪያም ገብረመድኅን፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከተላከ የሻይ ቅጠል ምርት ሁለት ነጥብ 30 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

ከ2015 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ292 ቶን በላይ ብልጫ አለው፤ በገቢም እድገት አሳይቷል ብለዋል፡፡

ለውጭ ገበያ የተላከው የሻይ ቅጠል ምርት ከ2015 ዓም ጋር ሲነፃፀር የ50 ሺህ ቶን ብልጫ ቢኖረውም ሀገሪቱ ካላት አቅም አንጻር ብዙ መሥራት የሚጠይቅ....

https://press.et/?p=137253
ኢትዮቴሌኮም ነባር የኮፐር መስመሮችን ወደ ፋይበር የሚቀይር "ኮፐር ሲዊች ኦፍ" የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ አደረገ
**
(
ኢ ፕ ድ)

ኢትዮ ቴሌኮም ነባር የኮፐር መስመሮችን ወደ ፋይበር የሚቀይር " ኮፐር ሲዊች ኦፍ" የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ አድርጓል።

ከኮፐር ወደ ፋይበር የመቀየር ስራ ከዛሬ ጀምሮ በቀጣዮቹ አመታት በመላ አገሪቱ ይተገበራል።

አዲስ አበባን በሶስት አመታት፤ ክልሎች ደግሞ በአምስት አመታት ተደራሽ እንደሚደረጉ ተጠቁመዋል።

የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ አገልግሎቱን አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ይፍ የተደረገው ኢኒሼቲቭ ከ100 አመታት በላይ አገልግሎት ይሰጥ የነበረውን የደንበኞች የኮፐር ቴሌኮም መስመር ለመተካት ነው።

የደንበኞችን የኮፐር ቴሌኮም መስመር መቀየር ያስፈለገው፤ ረዥም አመታትን ያገለገለ በመሆኑ ዘመኑን የሚመጥን ሆኖ ባለመገኘቱ ነው ብለዋል።

ከኮፐር ወደ ፋይበር የተደረገው ሽግግር የድምጽና የዳታ ጥራትን በማረጋገጥ የደንበኞችን እርካታ ለማሳደግ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

ሽግግሩ በአገር ደረጃ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና እድገትን ለማፍጠን እንደሚያግዝ ጠቁመው ይፋ የተደረገው አገልግሎት ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚደረገው ርብርብ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

በ2017 በጀት አመት የ100 ሺህ ደንበኞችን መስመር የመቀየር ስራ ለመስራት መታቀዱን አመላክተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

መስከረም 14 ቀን 2017 ዓም