"የሆራ ፊንፊኔና የሆራ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓላት በስኬት መጠናቀቃቸው የኦሮሞን ህዝብ ታላቅነት የሚያረጋግጥ ነው"-
- ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ
****
(ኢ ፕ ድ)
የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሃርሰዴ የኢሬቻ ክብረ በአላት ያለአንዳች እንከን ዕሴቱን በጠበቀ አኳኋን በስኬት መጠናቀቃቸው የኦሮሞን ህዝብ ታላቅነት ያረጋገጡ ናቸው"ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ፡፡
የአዲስ አበባና የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች የበአሉን ታዳሚዎች በፍቅር በመቀበል ስላኮራችሁን አመሰግናለሁ ብለዋል።
የኦሮሞ ህዝብ ሰላም ወዳድ፣ ለአንድነትና ለወንድማማችነት ክብር ያለዉ፣ በተግባርም ባህላዊ እሴቶቹን የተላበሰ መሆኑን ዳግም በማረጋገጡ በራሴና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስም ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

👍10💩4😁2
በ2016 የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በአማራ ክልል በ2016 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት መርሐግብር ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ ትምህርት ሰብዓዊና ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል ትልቁ መሳሪያ ትምህርት መሆኑን ገልጸዋል።
ትምህርት ቤቶች ከታለመላቸው ዓላማ ወጥተው በተለይም ባሳለፍነው የትምህርት ዘመን በአንዳንድ አካባቢዎች ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ትውልድ የሚቀረጽበት ተቋም መሆኑን የዘነጋ እንቅስቃሴዎች መታየታቸወን ጠቁመዋል።
በዚህ ችግር ውስጥ ሆነውም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ላደረጉ ምሥጋና አቅርበዋል።
በተመሳሳይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን በ8ኛ እና በ12 ክፍል ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ላይ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖች፣ አንድ መጽሀፍ ለአንድ ተማሪ ንቅናቄ ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ዞኖችና ዘርፉን ለደገፉ ባለሀብቶች እውቅናና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
መስከረም 26 ቀን 2017 ዓም

👍9❤3
ቀድመው የሚደርሱ ሰብሎችን ለመሰብሰብ ከሁለት ሺህ በላይ ኮምባይነሮች ዝግጁ ሆነዋል
******
(ኢ ፕ ድ)
በሀገሪቱ በተለያዩ ቆላማ አካባቢዎች ቀድመው የሚደርሱ ስብሎችን ወቅታቸውን ጠብቆ ለመሰብሰብ ሁለት ሺህ 700 ኮምባይነሮች ዝግጁ መሆናቸውን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሰብሎችን በጊዜያቸው ሰብስቦ ለመውቃትም ከ29 ሺህ በላይ ሁለገብ መውቂያ መሣሪያዎች መዘጋጀታቸውን ተጠቁሟል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የግብርና መካናይዜሽን መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ እሸቱ ሁንዴ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በሀገሪቱ በተለያዩ ቆላማ አካባቢዎች ቀድመው የሚደርሱ ሰብሎችን ጊዜያቸውንና ወቅታቸውን ጠብቆ ለመሰብሰብ ከሁለት ሺህ በላይ ኮምባይነሮችና ከ29 ሺህ በላይ ሁለገብ መውቂያ መሣሪያዎች ዝግጁ ተደርገዋል፡፡
የግብርና ቴክኖሎጂ አቅርቦትን በማስፋፋት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው፤ እየተሠራ ባለውም ሥራም በኢትዮጵያ የተለያዩ ቆላማ አካባቢዎች ቀድመው የሚደርሱ ሰብሎችን......
https://press.et/?p=138010

👎5👍3❤2👏1
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት !
በትላንትናው እለት በከተማችን በመሰራት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶቻችንን ግንባታዎች ተዘዋውረን ገምግመናል።
በተለይም ከተማችንን የኮንፍራንስ፣ የቱሪዝም እና የስበት ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ጥረት የሚያረጋግጡ፣ የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚፈጥሩ እንዲሁም ለነዋሪዎቻችን የስራ እድልን በሰፊው የሚፈጥሩ የአዲስ ኢንተርናሽናል የኤግዚቢሽንና የኮፍረንስ ማዕከል፣ ከዚያ ጋር ተያይዞ እየተሰራ ያለውን የለሚ ፓርክ፣ አየር መንገድ-ጎሮን ከአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ጋር የሚያገናኘዉን መንገድ ግባታ እና የአረንጏዴ ልማት ስራዎቻችን ያሉበትን ደረጃ ጎብኝተናል።
ፕሮጀክቶቹ በተገቢ ጥራት በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን በፍጥነት ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ በቅርበት ክትትል እያደረግን በመስራት ላይ እንገኛለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም

👍2❤1
በአማራ ክልል የወባ ወረርሽኝ ተጨማሪ ቀውስ እንዳያስከትል የክትትልና የቁጥጥር ሥራ እየተሠራ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
👉ከ457 ሺህ በላይ ዜጎች በወባ ተይዘዋል
በአማራ ክልል የወባ ወረርሽኝ ተጨማሪ ቀውስ እንዳያስከትል የክትትልና የቁጥጥር ሥራ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቢሮ አስታወቀ።
457 ሺህ 718 ዜጎች በወባ በሽታ መያዛቸውም ተነግሯል፡፡
በአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና የወባ መከላከልና ቁጥጥር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአማራ ክልል የወባ ወረርሽኝ ስርጭት ተጨማሪ ቀውስ እንዳያስከትል የክትትልና የቁጥጥር ሥራ እየተሠራ ነው፡፡
በክልሉ የታመሙ ሰዎች ተገቢውን የሕክምና መድኃኒት እንዲያገኙ ከማድረግ በተጨማሪ የወባ ትንኝ የሚራባባቸው ቦታዎችን በማፋሰስ፣ አጎበር በማሰራጨት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት ወረርሽኑ ተጨማሪ ቀውስ እንዳያስከትል የመከላከል ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
በአማራ ክልል የወባ በሽታ ወረርሽኝ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከትል፤ በክልሉ ድገተኛ ………..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=138076

👍1🔥1
ሁለቱ ምክር ቤቶች ዛሬ ሥራ ይጀምራሉ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመናቸውን ዛሬ ከሰዓት ከቀኑ 8 ሰዓት በሚያካሂዱት የጋራ ስብሰባ ይጀምራሉ።
በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ (2) እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል።
በድንጋጌው መሰረት የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓትም የሪፐብሊኩ ፕሬዚደንት በተገኙበት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይም የሪፐብሊኩ ፕሬዚደንት ለሁለቱ የፌዴራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

👍1😁1
የአፋር ክልል ሕብረተሰብ ክፍሎች እና ባለድርሻ አካላት ያደራጁትን አጀንዳ ለኮሚሽኑ አስረከቡ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የአፋር ክልል ሕብረተሰብ ክፍሎች እና ባለድርሻ አካላት ለስድስት ቀናት ሲያካሂዱ በቆዩት አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ያደራጁትን አጀንዳ በተወካዮቻቸው ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል።
በሀገር ደረጃ በሚደረገው ምክክር ክልሉን የሚወክሉ ተሳታፊዎችንም መርጠዋል።
በርክክብ ሥነስረዓቱ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድህን፤ ከአፋር ክልል የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ከሌሎች ክልሎች ከተሰበሰቡ አጀንዳዎች ጋር በሀገር ደረጃ በሚካሄደው ጉባኤ ቀርበው ምክክር ይደረግባቸዋል ብለዋል።
ኮሚሽነር አምባሳደር አይሮሪት መሀመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፉ እንዲሳካ አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።
በአጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፉ በክልሉ ከሚገኙ 49 ወረዳዎች የተመረጡ ከ800 በላይ የሕብረተሰብ ክፍል ወኪሎች እና በክልልሉ የሚገኙ ከ700 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሦስቱ የመንግስት አካላት፣ የተለያዩ ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች ተሳትፈዋል፡፡
ተስፋ ፈሩ (ሰመራ)
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም.

👍2👎1