የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️
በብዙ የሀገራችን ክፍል እንደሚታየው የደቡብ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው። በያዝነው የምርት ዘመን የፍራፍሬና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል።
34 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ፍራፍሬና 7ነጥብ 6 ኩንታል አትክልት ተመርቷል።
ይህን በደቡብ ክልል የታየ ስኬት በሌሎች ክልሎችም ለማስፋፋት የጋራ እድገት ለማስገኘትና የምግብ ዋስትና ትልማችንን አሳክቶ ዘላቂ ልማትን በሚያረጋግጥ መልክ ጠንክረን መስራት ይገባል።
መስከረም28 ቀን 2017 ዓም

👍14😢2❤1🤨1
"ኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች መጠለያ ናት"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከአንድ ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች መጠለያ ናት ሲሉ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዛሬ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (UN-IOM) ዳይሬክተር ጄነራል ኤሚ ፖፕ ጋር ውይይት አድርገናል፡፡ ከተቋሙ ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ላይም መክረናል፡፡
በዚህም የህገ ወጥ ፍልሰት ተግዳሮቶችን በዘላቂነት መፍታት እና የውጪ ሀገር ስራ ስምሪት ለዘላቂ ልማት የሚያበረክተዉን አስተዋፅዖ ማሳደግ በሚቻልባቸው የትብብር ሀሳቦች ላይ ከስምምነት ደርሰናል።
የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ህገወጥ ፍልሰትን ከመከላከል፣ ከፍልሰት ተመላሾች እና ተፈናቃዮችን ከመደገፍ አኳያ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል።
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም

👍4👏1😁1
5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት አንድ እስከ 30 ቀን 2017 ዓም ድረስ ይካሄዳል
****
(ኢ ፕ ድ)
5ኛው ሀገርአቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር "የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት"በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2017 ዓም ድረስ ለአንድ ወር እንደሚካሄድ ተገለፀ።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በሰጡት መግለጫ፤በሀገሪቱ የተቋማት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ከማደጉ ጋር ተያይዞ የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።
በሳይበር ደህንነት ወር የሚከናወኑ መርሀግብሮች የተቋማትንና የማህበረሰብን የሳይበር ደህንነት ንቃተህሊና በማጎልበት ለሳይበር ደህንነት ትኩረት እንዲሰጡና ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ ያስችላል ብለዋል።
በሳይበር ደህንነት ወር መክፈቻ በሳይንስ ሙዚየም ይካሄዳል። "የቁልፍ መሰረተ ልማት የሳይበር ደህንነት ለዲጂታል ሉአላዊነት "በሚል ርዕስ ውይይትና የግንዛቤ መለካት የሚያስችል ውድድር የሚካሄድ መሆኑን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በሳይበር ደህንነት ወር ባሉት ቀናትም በሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣የኮደርስ ኢኒሼቲቭ ለሳይበር ደህንነት ሚና፣ በስማርት ስቲ የሳይበር ደህንነት ሚና ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢንፎርሜሽን ደህንነት ማረጋገጥ ስራን ሁሉም ባለድርሻ በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አስታውቀዋል።
ኢመድአ ባለፋት አራት አመታት የሳይበር ደህንነት ወሮችን በማዘጋጀት የንቅናቄ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን አንስተው፤ በዚህም ለሳይበር ደህንነት ትኩረት እንዲሰጡ ንቃተ ህሊናን የመገንባት ስራን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።
በማህሌት ብዙነህ

👍4
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
******
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በሦስት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች፤
1ኛ. የኮሪደር ልማት የግዥ ጥያቄ ፣ የግንባታ በጀት እና የግዢ ሂደት አወሳሰን በተመለከተ በፋይናንስ ቢሮ በኩል ለቀረበልን ጥያቄም፤ ለልማቱ መሳለጥ እና የሀብት መባከን እንዳይፈጠር እንዲሁም የሥራ ቅልጥፍናን በሚጨምር መንገድ ለመስራት እንዲያስችል የሚያደርግ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተወያይተን አፅድቀዋል ::
2ኛ. በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የሚተዳደሩ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አያያዝ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም እና ወደ ከተማው ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር ዘይቤ ማምጣት እንዲያስችሉ ተቋማቱ በትምህርት ቢሮ ይዞታ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ደንብ አስፈላጊ በመሆኑ አፅድቀዋል።
3ኛ. የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ኃይል ስምሪት በማዕከል ፣ በክ/ ከተማ እና በወረዳ ለማመጣጠን እንዲቻል በተዘጋጀው የዝውውር እና ምደባ ረቂቅ ደንብ በየተቋማቱ ያለንን የሰው ሀብት በውጤታማነት ለመጠቀም እንዲያችል የሚያግዝ በመሆኑ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
መስከረም 28 ቀን 2017

👍11❤1
የሬሚዲያል ፕሮግራም መከታተል የሚያስችል የመግቢያ ውጤትን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አደረገ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለሚከታተሉ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።
መስከረም28 ቀን 2017 ዓም
*******
(ኢ ፕ ድ)
በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለሚከታተሉ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።
መስከረም28 ቀን 2017 ዓም
👍10😁1
መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ በአዲስ መልክ ለመሥራት መዘጋጀቱን አስታወቀ
***
(ኢ ፕ ድ)
የኅብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችል እቅድ ነድፎ በአዲስ መልክ ለመሥራት መዘጋጀቱን መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ገለጸ።
በመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ተሰማ ጊደይ ለኢፕድ እንዳሉት፤ ድርጅቱ በሀገር ደረጃ ከሚጠቀሱ ታላላቅ የልማት ድርጅቶች መካከል ተጠቃሽ ነበር። ይሁን እንጂ በጦርነቱ ምክንያት ከደረሰበት ውድመት አገግሞ በአዲስ መልክ ተጨማሪ ዕቅዶች አውጥቶ ለመሥራት ዝግጅት አድርጓል።
ድርጅቱ በተሟላ መልኩ ምርት እንዲጀምር ጥረቶች እየተደረጉ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ቀደም ሲል በሲሚንቶ ፋብሪካዎችና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ጀርባ በመሆን የኢንጂነሪንግ ሥራ ሲያከናውን የነበረ ሲሆን፤ በተጨማሪም የመኪና መለዋወጫ ዕቃ እና መገጣጠሚያ እንዲሁም ሁለገብ የኢንጂነሪንግ ሥራዎች ሲሠራ መቆየቱን.....
https://press.et/?p=138201

👍1😁1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአደባባይ በዓላት በድምቀት ተከብረው እንዲጠናቀቁ አስተዋጽዖ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል
********************
(ኢ ፕ ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ የአደባባይ በዓላት በድምቀት ተከብረው እንዲጠናቀቁ አስተዋጽዖ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።
ከንቲባ አዳነች በተለይም ከአዲስ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ በአዲስ አበባ የተከበሩት በዓላት ፍጹም ሰላማዊ፣ የተረጋጋ፣ ደማቅ፣ ህዝቡን ባከበረ እና ላቅ ባለ ዲስፒሊን በተሞላበት መንገድ ኃላፊነታቸውን የተወጡ የጸጥታ አካላትን፣ በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩን አመራሮችን እንዲሁም መላው የከተማውን ህብረተሰብ አመስግነዋል::
የአደባባይ በዓላት ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት እና የቱሪስት መስህብ ናቸው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ነዋሪውን የሰላሙ ባለቤት በማድረግ ከተማችን አዲስ አበባን ሰላማዊ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል::
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው የአደባባይ በዓላቱ በድምቀት ተከብረው ለመጠናቀቃቸው የከተማ አስተዳደሩ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ለሰራው ስራና ለተገኘው ውጤት አመስግነው ይበልጥ ውጤታማ ስለሚያደርገን በጋራ መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
መስከረም29 ቀን 2017 ዓም

👍4❤2