የሁለተኛ ምዕራፍ #የኮሪደር_ልማት ፕሮጀክት‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ‼️
✍️ የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ በዚህ ሳምንት ይጀመራል፣
✍️ በአጠቃላይ 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል፣
✍️ ለቀበሌ ቤት ተነሺዎች ምትክ ቤቶች ተዘጋጅተዋል፣
✍️ ተነሺዎች ያላቸው ማህበራዊ ትስስር እንዳይበተን በአንድ አካባቢ እንዲሰፍሩ ይደረጋል፣
✍️ከ500 በላይ የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ለነዋሪዎቻችን ዝግጁ ተደርገዋል፣
✍️ በአዲስ አበባ የሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስምንት ኮሪደሮች ይለማሉ፣
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም

👍4👎2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️
በብዙ የሀገራችን ክፍል እንደሚታየው የደቡብ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው። በያዝነው የምርት ዘመን የፍራፍሬና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል።
34 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ፍራፍሬና 7ነጥብ 6 ኩንታል አትክልት ተመርቷል።
ይህን በደቡብ ክልል የታየ ስኬት በሌሎች ክልሎችም ለማስፋፋት የጋራ እድገት ለማስገኘትና የምግብ ዋስትና ትልማችንን አሳክቶ ዘላቂ ልማትን በሚያረጋግጥ መልክ ጠንክረን መስራት ይገባል።
መስከረም28 ቀን 2017 ዓም

👍14😢2❤1🤨1
"ኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች መጠለያ ናት"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከአንድ ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች መጠለያ ናት ሲሉ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዛሬ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (UN-IOM) ዳይሬክተር ጄነራል ኤሚ ፖፕ ጋር ውይይት አድርገናል፡፡ ከተቋሙ ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ላይም መክረናል፡፡
በዚህም የህገ ወጥ ፍልሰት ተግዳሮቶችን በዘላቂነት መፍታት እና የውጪ ሀገር ስራ ስምሪት ለዘላቂ ልማት የሚያበረክተዉን አስተዋፅዖ ማሳደግ በሚቻልባቸው የትብብር ሀሳቦች ላይ ከስምምነት ደርሰናል።
የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ህገወጥ ፍልሰትን ከመከላከል፣ ከፍልሰት ተመላሾች እና ተፈናቃዮችን ከመደገፍ አኳያ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል።

👍4👏1😁1
5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት አንድ እስከ 30 ቀን 2017 ዓም ድረስ ይካሄዳል
****
(ኢ ፕ ድ)
5ኛው ሀገርአቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር "የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት"በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2017 ዓም ድረስ ለአንድ ወር እንደሚካሄድ ተገለፀ።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በሰጡት መግለጫ፤በሀገሪቱ የተቋማት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ከማደጉ ጋር ተያይዞ የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።
በሳይበር ደህንነት ወር የሚከናወኑ መርሀግብሮች የተቋማትንና የማህበረሰብን የሳይበር ደህንነት ንቃተህሊና በማጎልበት ለሳይበር ደህንነት ትኩረት እንዲሰጡና ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ ያስችላል ብለዋል።
በሳይበር ደህንነት ወር መክፈቻ በሳይንስ ሙዚየም ይካሄዳል። "የቁልፍ መሰረተ ልማት የሳይበር ደህንነት ለዲጂታል ሉአላዊነት "በሚል ርዕስ ውይይትና የግንዛቤ መለካት የሚያስችል ውድድር የሚካሄድ መሆኑን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በሳይበር ደህንነት ወር ባሉት ቀናትም በሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣የኮደርስ ኢኒሼቲቭ ለሳይበር ደህንነት ሚና፣ በስማርት ስቲ የሳይበር ደህንነት ሚና ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢንፎርሜሽን ደህንነት ማረጋገጥ ስራን ሁሉም ባለድርሻ በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አስታውቀዋል።
ኢመድአ ባለፋት አራት አመታት የሳይበር ደህንነት ወሮችን በማዘጋጀት የንቅናቄ ስራዎች የተሰሩ መሆኑን አንስተው፤ በዚህም ለሳይበር ደህንነት ትኩረት እንዲሰጡ ንቃተ ህሊናን የመገንባት ስራን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።
በማህሌት ብዙነህ

👍4
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
******
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በሦስት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች፤
1ኛ. የኮሪደር ልማት የግዥ ጥያቄ ፣ የግንባታ በጀት እና የግዢ ሂደት አወሳሰን በተመለከተ በፋይናንስ ቢሮ በኩል ለቀረበልን ጥያቄም፤ ለልማቱ መሳለጥ እና የሀብት መባከን እንዳይፈጠር እንዲሁም የሥራ ቅልጥፍናን በሚጨምር መንገድ ለመስራት እንዲያስችል የሚያደርግ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተወያይተን አፅድቀዋል ::
2ኛ. በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የሚተዳደሩ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አያያዝ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም እና ወደ ከተማው ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር ዘይቤ ማምጣት እንዲያስችሉ ተቋማቱ በትምህርት ቢሮ ይዞታ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ደንብ አስፈላጊ በመሆኑ አፅድቀዋል።
3ኛ. የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ኃይል ስምሪት በማዕከል ፣ በክ/ ከተማ እና በወረዳ ለማመጣጠን እንዲቻል በተዘጋጀው የዝውውር እና ምደባ ረቂቅ ደንብ በየተቋማቱ ያለንን የሰው ሀብት በውጤታማነት ለመጠቀም እንዲያችል የሚያግዝ በመሆኑ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
መስከረም 28 ቀን 2017

👍11❤1