Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛው አካል የተሰጠ ውክልና የለም - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
*******
(ኢ ፕ ድ)
በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል ውክልና አለመስጠቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለሥራ እንልካለን በማለት የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ሚኒስቴሩ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና እንደሌለም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣እንግልትና ከሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

ዜጎች የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ለማግኘት (lmis.gov.et) የተሰኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጠቁሟል።

ህዳር 14 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍7👏3👎1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍5😁2🕊21
እንደምን አደሩ‼️
#አዲስ_ዘመን_ዛሬ‼️
ህዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ
https://press.et/?p=141433
መልካም ቀን!
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን‼️
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://news.1rj.ru/str/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ 👇
https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et
👍7👎21
ጥንቃቄን የሚሻው የስኳር ህመም
***
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የስኳር ህመም እንዳለባቸው በዓለም አቀፉ የስኳር ፌደሬሽን የተደረገ ጥናት ያሳያል። ከጠቅላላው ሕዝብ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚሆነው ለህመሙ ተጋላጭ መሆኑን የሚያሳየው ጥናቱ፤ በኢትዮጵያ በህመሙ ከሚጠቁት ስልሳ ሰባት በመቶዎቹ ህመሙ እንዳለባቸው እንደማያውቁ ይገልፃል። ለዚህም ምክንያቱ ህመሙ ቅድሚያ ምልክት የማያሳይ በመሆኑ እንደሆነ በጥናቱ ተጠቁሟል።

የስኳር ህመም ታማሚ የሆነችው ፅጌ በቀለ ስሟ የተቀየረ) ህመሙ እንዳለባት ካወቀች ዓመት እንዳልሞላት ትገልፃለች። እንደ እሷ ገለፃ ህመሙ እንዳለባት ሳታውቅ ረጅም ጊዜ ቆይታለች። ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰውነቴ እየቀነሰ ሲሄድ ተደናግጬ የኤች አይቪ ምርመራ እስከማድረግ ደርሻለሁ የምትለው ፅጌ፤ አቅሟ ተዳክሞ መንቀሳቀስ እያቃታት ሲመጣ ወደ ሆስፒታል እንዳቀናች ታስታውሳለች።

ምርመራ ያደረጉላት ሀኪሞችም ስኳሯ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ገልፀው፤ ሆስፒታል ተኝታ እንድትታከም ማድረጋቸውን ትገልፃለች። ከዚህ ጊዜ አንስቶም ኢንሱሊን መጠቀም እንደጀመረች አስታውሳ፤ በቤተሰብ ደረጃ ህመሙ ያለበት ሰው ስላልነበረ፣ ዕድሜዋ ከአርባ ዓመት በታች ስለሆነና ያን ያህል አስጊ.....

https://press.et/?p=141438
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ቴሌግራም https://news.1rj.ru/str/ethpress
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍71👏1
#አህጉር_አቀፍ #የሰላም_ኮንፈረንስ ‼️

በታንዛኒያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ምክትል ዋና ፀሐፊ ካዲ ማዚሁ የተመራ ልዑክ፤ የኬኒያ የሰላም ግንባታ እና የግጭት አስተዳደር ጸሀፊ ሙሐመድ ባሬ እና የህዝብ ግንኙነት ረዳት ዳይሬክተር ዲያና አካማ ሰላም ሚኒስቴር ያዘጋጀውን አህጉር አቀፍ ኮንፈረንስ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ።

ከ20 በላይ ሀገራት በኮንፈረንሱ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የተለያዩ ሀገራት ተሳታፊዎች  ከትናንት ጀምሮ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

በሄለን ወንድምነው

ህዳር 15 ቀን 2017 ዓም
👍7
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
🔥4👍2